ጥቁር ቀን: የከሸፈው የበአለ ሲመት ዕቅድ…

1፦ ከመጋቢት 7 ጀምሮ በዐማራ ፋኖ ላይ ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት በአለ ሲመቱን በድል አሸብርቆ ለማክበር አቅዶ ወደ ሥራ ለመግባት ሲሰናዳ አባደፋር ፋኖም ይቺን ተረድቶ ከመጋቢት 5 ጀምሮ የአራጁን ሠራዊት ኢሬቻውን አብልቶት አረፈው። በዚህ ላይ ሜጀር ጀነራል ውባንተ ተሰዋና የባሰ የዐማራ 4ቱም ክፍላተ ሀገራት ተጣምረው አንድ ሆነው አፈር ደቼ አስግጠው አዋረዱት። ዐማራን በድሮን ጨፍጭፎ በአለ ሲመቱን ኦሮሞን እያስጨፈረ ሊውል የነበረው ዕቅድ በዘመቻ ውብአንተ ውኃ በላበት

2፦ እንደ ኢትዮጵያ መሪ አክት በማድረግ ከቢሮው ወጥቶ በየክልሉ እየሄደ በሕዝባዊ ውይይት ስም ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ የጉም ተስፋ ለማስጨበጥም አሁን የሚመራው ክልል አዲስ አበባ ብቻ በመቅረቱ አልተመቸውም። እንዲያም ሆኖ በቤተ መንግሥቱ መሰብሰቡ አልቀረም። ጴንጤ፣ እስላሞች፣ ሴቶች፣ የክልል ተወካዮች፣ ባለሀብቶች ሁሉም ተመርጠው ሄደው እሱ እንደሚፈልገው ቢሆኑለትም በመሃል ኦርቶዶክስ ጣልቃ ገብታ እስኪሳደብ ድረስ  አስነቀለችው። ከሸፈበት።

3ኛ፦ መጋቢት 7 ዐማራን ዱቄት አድርጌ ትግሬና ኦሮሞን አስደስቼ ከጎኔ በማሰለፍ በአለ ሲመቴን በተለየ መልኩ አከብራለሁ ብሎ የነበረው እቅዱም መና ሲቀር በተለዋጭ ከ20/7/2016 ጀምሮ ቢልም ይኸው ወፍ የለም።

4፦ በአለ ሲመቱን ኦሮሞ ሁሉ ሆ ብሎ እንዲወጣለት በሽመልስ በኩል ብዙ ተስፋ አስነገረ። ጭራሽ ኦሮሞ እነ ሽመልስን ታዘበ፣ አገታቸውም ላይ ገመድ ከተተ እንጂ ጠብ የሚል ነገር ጠፋ።

5፦ አሁን ያለው አማራጭ አዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ሲቲ ያሉትን ኦሮሞዎችና በኦሮሚያ ክልል አናታችሁ ወይም ቤታችሁ ከሚፈርስ በማለት የተረሳውን የሕዳሴ ግድብ ሩጫ በማለት የአቢይን ፎቶ አስይዞ በመውጣት ኦሮሞ ከአቢይ ጎንን ነው ማለት ብቻ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ አበባ ተቀወጠች የቦንብ ጥቃት ተሰነዘረ | ጀግኖቹ 4 መኪና ሰራዊት ደመሰሱ ሻለቃ ሀብቴ ታሪክ ሰራ አዋጊው ተገደለ

ዘመዴ

1 Comment

 1. በዓለ ሺ ሞት
  መቼም አይካድም
  የቅርቡ ትዝታ
  ፈጥሮብን ነበረ
  ዐቢይ ያኔ እፎይታ
  የማእበል ምርቃና
  ሞገደኛ ደስታ
  ሳይውል ሳያድር ግን
  የደሃ እንባ ጎርፉ
  ዋጠን የደም ጎርፉ
  ሺህ ሬሳ ከፊቱ
  ሺህ ሬሳ ከኋላው
  ይህን ሳታይ ሞተች
  ትነግሳለህ ብላው
  ሺህ ሬሳ ከቀኙ
  ሺህ ሬሳ ከግራው
  ኦሮሞና ትግሬ
  ኮንሶና አማራው
  ጌዴኦ ወላይታ
  ሌላውም በተራው
  ጉበቱ ተበልቶ
  ሲጠጣ ሐሞቱ
  የሚያገዳድለን
  ሊጸና ሥርዐቱ
  ይከበራል አሉ
  በዓለ ሺሞቱ
  2021 G.C.

  Written on the third anniversary.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share