“የልጄን አስከሬን ትቸ ከምወጣ እኔ ልሰዋ!” ~ አርበኛ አረጋ አለባቸዉ

ሞቷል የተባለውን ልጁን ከነ ህይወቱ ከጠላት መንጋጋ መንጭቆ አውጥቶታል

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እሸቴ ሞገስ የተባለ አርበኛ ልጁ ይታገሱ እሸቴ ስለቆሰለበት የልጀን እስከሬን ትቸ አልሄድም “ሚካሄልን ይታገሱን ትቸ አልወጣም” በማለት የአማራን ህዝብ የአባትነት ታሪክ በዚህ ዘመንም ያለ እውነታ መሆኑን ሰምተን አንብተናል: ክብር ለአባታለም ብለናል::

በትላንትናው እለት በደቡባዊ ጎንደር ክፍለ ሃገር እብናት ግንባር ይህ ታሪክ ተደግሟል:: በጎንደር ክፍለ ሃገር ስመጥሩ አርበኛ ኮማንደር አረጋ አለባቸው ሁለቱ ልጆቹ ማለትም ጌታው አረጋና ክንድየ አረጋ አብረውት ይታገላሉ::

በትላንትናው እለት ጌታው አረጋ እብናት ከተማን ለመያዝ በተደረገ አወደ ውጊያ ይቆስልና ይወድቃል: በወቅቱ የትግል ጏዶቹ ተስውቷል ብለው ለጊዜው የጠላት ትጽህኖ ስለነበር ወደ ውጊያው ያተኩራሉ:: በሌላ አቅጣጫ ሲዋጋ የነበረው አርበኛው አባቱ ኮማንደር አረጋ አለባቸው ልጁ እንደተመታ ይነገረውና ልጀን ትቸ ከምወጣ ሽህ ጊዜ ልሰዋ ብሎ ዘሎ ወደ ውጊያ በመግባት ከአንድ ሰዓት በላይ እልህ አስጨራሽ በሆነ ውጊያ ተዋግቶ ለጁን ከእነ ህይወቱ ተሽክሞ ለማውጣት ችሏል::

ተስውቷል የተባለው ልጁም በአሁኑ ሰዓት ህክምና እየተደረገለት በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛል:: ጀግናው ኮማንደር አረጋ አለባቸውን ቃለ መጠይቅ አድርጌ ዝርዝር ይዠ እመለሳለሁ!!!

በጎንደር ምድር የአባትና የልጅን ፍቅር በዚህ መልኩ በተግባር ላሳየኸው የስሜነኛው አርበኛ ኮማንደር

አረጋ አለባቸው ክበርልን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ደመቀ መኮንን የተባረ | ፋኖ አቡነ ሉቃስን አመሰገነ | የፋኖ አስደናቂ ግስጋሴ | የወልድያ ሆስፒታል በቁስለኛ ወታደሮች ተጨናንቋል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share