መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ/ም
ቀሲስ አስተርአየ [email protected]
ለአድዋው የድል መታሰቢያ በሚረገው ድብሰባ ላይ ከቤተ ክርስቲያናችን አብነት መምህራን የሰማሁትን ለማካፈል ተጠይቄ ሳለ በቦታው ተገኜቼ ያዘጋጀሁትን ለማቅረብ ስላልተመቼኝ አላቀረብኩትም ነበር፡፡
ያዘጋጀሁት ጽሑፍ በእለቱ ለማቅረብ ባልችልም ይጠቅማል ብየ ስላሰብኩ ላንባቢ ይደርስ ዘንድ ለድረገጾች ለመላክ ስዘጋጅ ከድሉ በዐል ጋራ ተያይዘው ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው ስብሰባወች በተከታታዩ ተካሄዱ፡፡
1ኛ:-128ኛውን የአድዋው የመተሳቢያ በዐል የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም የተደረገ ስብሰባ
2ኛ:-የካቲት 24 ቀን 2016 ዓ/ም የታወሰውን የፓትርያርኩ 11ኛ በዐለ ሲመት፡
3ኛ: ካህናት የመሰሉ ጥቂት ሰዎች የነበሩበት መጋቢት 7 ቀን 2016 የተደረገው ስብሰባ
4ኛ:- በጠቅላይ ምንስቴሩ መሪነት ፓትርያርካችን የተገኙበት ስብሰባ
5ኛ፦የፕሮቴስታንቶች ስብሰብ
6ኛ፦የሙስሊም ወገኖቻችን ስብሰባ
በተከታታይ የተካሄዱትን ሰብሰባወችን በመቃኘት ላይ ሳለሁ “Quantum Physics and the Quest for the Elusive National Dialogue in Ethiopia” በሚል ርዕስ ዶክትር ዮናስ ብሩ March 19, 2024 ያቀረቡትን፦ የዘመናችን ምሑራን ስለ ሀገር በሚነጋገሩበት አውድ ላይ አቶ ጸሐይ ደመቀ ጠቅሰውት ባጋጣሚ ተመለከትኩ፡፡
የዘመኑ መምህሮቼ የሚነጋገሩበት “Quantum physics and the Quest for the Elusive National Dialogue in Ethiopia” የሚለው ይህ ጽንሰ ሐሳብ አጼ ምንይልክ ለድሉ የተጠቀሙበትን ማርያማዊ አዋጅ እንዳቀርበው የበለጠ ገፋፋኝ፡፡
ይህ ማርያማው መርሆ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክርስቶስን ስትጸንሰው “በክንዱ ኃይል አድርጓል ተቢተኞችን በተናቸው ግዠወችን ከዙፋናቸው አወረዳቸው የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዷቸውን ሰደዳቸው፡፡ ለአባቶቻችን ለአእብርሃምና ለዘሩ እንደተናገረ ”(ሉቃ 1፡51_54) ብላ ከተናገረችው የተወሰደ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ማርያማዊ መግለጫ እንዳይዘነጋ በጸሎት ሰይማ በየቀኑ በመድገም መመሪያችን እንድናደርገው በጭንቅላታችን እንድንቀርጸው በቃላችን ደጋግመን እንድንናገረው አድርጋናለች፡፡
ኃይል የሚጠይቅ አዲስ ነገር ለማድረግ ከመሰማራታችን በፊት በጥበብ በልምድ በትምህርትና ከኛ ወደ ላቁ አባቶች ሄደን በፊታቸው ተንበርክከን የምንሸኘው በጸሎተ ማርያም (በመቤታችን መግለጫ) ነው፡፡ በነአጼ ምንይልክ የተፈጸመውን ይህን ማርያማዊ መፈክርም ሆነ ሌሎችን ሁሉ ቅርሶች ጥንታውያን መሆናቸውንና ከነሱ በፊትም የነበሩ መሆናቸውን የምናውቀው እስካሁን ድረስ በመካሄዳቸው ነው፡፡
እመቤታችን ክርስቶስን ስትጸንሰው የተናገረችውን ከየት ወሰደችው? መሠረታዊ ታሪኩስ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ መነሳት አይቀርም፡፡ መቼ፡ ማን እንደጀመረውና እንዴት ወደኛ እንደተሻገረ መገለጽ ቢኖርበትም፤ ሰፊ ሐተታውን በዚህች አጭር ጦማር ማቅረብ ስለማይቻል፤ ከዚህች ጦማር በኋል ለማስከተል አዘግይቼ፤ ወቅቱን ወደ ሚያሳየው፡ ኢትዮጵያውነትን ሁለንተና ወደሚጠቁመው፡ በመናድ ላይ ያለውን ስርአት ወደ ተሸከመው ወደ ቅኔው ትምህርት እሻገራለሁ፡፡
ከአድዋው የመተሳቢያ በዐል ጀምሮ እስከ ሙስሊም ወገኖቻችን በጠቅላዩ እየተቃኙ በተከታታይ የተደረጉትን ስብሰባወች ስመለከት “ነገርን ነገር ያመጣዋል” እንዲሉ ከአድዋው ድል ሳይርቁ ተሰናስለው የቀጠሉ መሰለኝና አንድ ነገር መጣብኝ፡፡
ኬንያ Embu በሚባለው ቦታ St Andru College በነበርከበት ጊዜ
የAnthropology እና የsosiology ትምህርት መምህሮቻችን ይጠቀሙባቸው የነበሩት ዘዴወች ትዝ አሉኝ፡፡
ተማሪወች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከመጣሁት በቀር የቀሩት ሁሉም እንግሊዝ በቅኝ ትገዛቸው ከነበሩት በኋላ በኮመንዌልዝ ከተሳሰሩት አገሮች እየተመረጡ የመጡ ናቸው፡፡ መምህራኑ እንግሊዞች ናቸው፡፡ ተማሪወችን በቡድን ከፍለው በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ወንጌል ስበኩ ብለው በየደረስንበት የሚገጥመንን እንድንጽፍ ደብተርና በእር አሲዘው ይበትኑናል፡፡
መምህራኑ የጻፍነውን ይሰበስቡና “epilog” የሚል ሰአት ተዘጋጅቶለት እየተነበበ ይተቻል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋል እያንዳንዱ ተማሪ ቢያንስ በአንድ ገጽ የተጠቃለለ የራሱን ሀሳብ እንዲጽፍ ይገደዳል፡፡ ሁሉት ጥቅም ይኖረዋል፡፡ አንደኛው መምህራኑ ከቤታቸው ሳይወጡ ተማሪወች ለፍተው በሚያቀርቡት አማካይነት የሕብረተ ሰቡን ሁኔታ አዳዲስ ሐሳብ ይማሩበታል፡፡ የነበራቸውን እውቀት ያጠነክራሉ ያድሳሉ፡፡ ምክንያቱን ለወንጌል ስብከት ይበሉት እንጅ ዘግይቼ እንደተረዳሁት ህብረተ ሰቡን ለማጥናት ነበር፡፡
ይህ ዘዴ በባእድ አገርና ቋንቋ ስለገጠመኝ እንጅ በቅኔ ትምህርት ቤት ሳለሁ ሳደርገው ከነበረው የተለየ አልነበረም፡፡ የቅኔው መምህር ለተማሪወቻቸው አቅጣጫ ጠቋሚ (sample) አዲስ ቅኔ ለተማሪወቻቸው ይዘርፋሉ፡፡ የዘረፉትን ቅኔ ይዘቱን ቅርጹን ከቀጸልን በኋላ ወደ ሕብረተ ሰቡ በመሄድ በየጫካውም በመበትን የየራሳችን ቅኔ በመቀመር ባንዲት ነገር ላይ የማይመሳሰል ሐሳብ ይዘን እንቀርባለን፡፡ መምህሩ ተማሪወች ከህብረተ ሰቡ ባየትና በሰሙት ላይ መስርተው ቆጥረው ቢሚያቀርቡላቸው ቅኔወች አዳዲሲ ነገሮችን ይማሩባቸዋል፡፡ በሚቀጥለው አፍሰው ለሚዘርፉት ቅኔ የታመቀ ሀሳብ ያገኙበታል፡፡
ጠቅላዩ በዚህ ሳምንታት ውስጥ በተከታታይ የመሯቸው ስብሰባወች በቅኔ ትምህርት ቤትና በኮሌጅ ሳለሁ ሳደርጋቸው ከነበሩት ልምዶች ጋራ ተመሳሳይ ሆነው አገኘኋቸው፡፡
ጠቅላዩ አገር ሲመሩበት የነበረው ፈሊጥ አርጅቶባቸው ሊወድቅ አፋፍ ላይ ሲደርስ ለማፍረስ የፈለጉትን ለማፍረስ ለመገንባት የፈለጉትን ለመገንባት ኃይላቸውንና አቅማቸውን በአዲስ ዘዴ አጥናክረው ለመቀጠል የተማሩበት መሰለኝ፡፡
የአድዋውን ድል መርሆ ያዘጋጀችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን በመምራት ያሉትን የተረዳሁት እየተጎተቱ ሄደው ሲኖዶስ የሚባለውን አንቀው ገለው ከዓቢይ ጠረጴዛ ስር ቀብረውት የተመለሱና በነሱ ላይ የነበረውን የህዝበ ክርስቲያኑ የተስፋ ጫላንጭል ያደፈኑበት ሆኖ ነው ያየሁት፡፡
በጠቅላይ ምንስቴሩ ሰብሳቢነት የተካሄዱት ሁሉ አገር አቀፍ ስብሰባወች በመላ ኢትዮጵያ የፈሰሰውን የኢትዮጵያውያንን ደም የተቃጠሉትን አብያተ ክጽቲያን ባለማንሳታቸው፤ የምናየው ምስል የምንሰማው መርዶ ቅዠት ነው ካልተባለ በቀር፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን በመቅበራቸው የተስማሙ ይመስላሉ፡፡
በፕሮቴስታንቱ ስብሰባ ላይ ጥቅላይ ምንስቴሩ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በመገንባት መንግሥትን አለመጠየቋን በጥሩ ምሳሌነት ኦርትሆዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ከመጥቀሳቸው በቀር፡ ስለተቃጠሉት ስለታረዱት ስለተፈናቀሉት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የተናገረ ወይም ያነሳ አንድ ሰው አልነበርም፡፡
እንዲያውም ጭራሽ ይህ ሁሉ እልቂትና ቃጠሎ በሚካሄድባት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉም አይመስሉም፡፡ ሁሉም በጠቅላዩ ስለተደረገላቸው ውለታ በማመስገን ቀረን የሚሉትን የቅንጦት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በቤተክርስቲያናችን ላይ ለደረሰባት ሁሉ ግፍና በደል የሕሊና ጸሎት ሲጠበቅባቸው ያቀረቡት የይሟላልን ጥያቄ እንኳን ደረሰብሽ የሚል ሽርደዳ የሚመስል ነበር፡፡
እንዲያውም ጠቅላይ ምንስቴሩ በየስብሰባወች ባደረጓቸው ንግግሮች ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ በማድረግ ግድያውን ቃጠሎውን ጥፋቱን ሁሉ ሰብበው በዘመናችን ባሉት ፓትርያርክና ጠቅላይ ስራአስኪያጁ በማሸከም በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ እጽፍ ድርብ በደልና ግፍ የፈጸሙባት መሰለኝ፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ጥለዋት ወደ ሌላ ቤተ እምነቶች የሸሺ ሁሉ፡ የሸሹት እውነት ክርስቶስን ፍለጋ ከሆነ ይህን ሸርና ደባ ሲመለከቱ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናቸው የሚመለሱ ይመስለኛል፡፡
የተደረጉት ሁሉ ስብሰባወች ቤተ ክርስቲያናችንን በጠርጴዛቸው ስር ቀብረዋት በተመለሱት ጳጳሳት ላይ የከረረ ጥላቻ እንድንፈጠርና በመካከላችንም ጳጳሳቱን በመደገፍና በቃወም ጎራ ተሰልፈን በመከፋፈል በእርስ በርስ ጭቅጭቅ እንድንጠመድ ለማድረግ የተሰራ ደባ መሆኑን መረዳት ያለበን ይመስለኛል፡፡
በሌ በኩል በሁሉም ስብሰባወች ጠቅላይ ምኒስቴሩ ራሳቸውን ፊደል አስቆጣሪ መምህር ለዓድዋው ድል መራሂት የነበረችውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በመምራት ላይ ያሉትን ጳጳሳት ፊደል ቆጣሪወች በማስመሰል ቤተ ክርስቲያናችን ኢትይጵያን ስታንጽና ስትገነባባቸው የነበሩትን ስርአቶች የጨው ካብ አደረጓቸው፡፡
“የጨው ካብ ሲናድ ሞኝ ይልሳል ብልህ ያለቅሳል” የሚለው አብባል ትዝ አለኝ፡፡ ዛሬ የጨው ካብ ላደረጓት ቤተክርስቲያናችን ለኢትዮጵያ መሠራትና መገንባት ባለቤት በመሆኗ አገር ናት እያሉ ተናግረውላት ነበር፡ የሚንዷትንና የሚልሷትን እየታዘብኩ ከሚያለቅሱት ጋር በመሰለፌ ለእውነተኛ ኢትዮጵያዊነቴ ማረጋገጫ ስለሆነኝ የሕሊና እርካታ አግኝቸበታለሁ፡፡
ከዚህ በመቀጠል እነ ዶክተር ዮናስ ብሩ መነጋገሪያ አድረገው ያቀሩቡት “Quantum physics and the Quest for the Elusive National Dialogue in Ethiopia” የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ወደገፋፋኝ ወደ አጼምን ይልክ ማርያማዊ ምርሆ እሻገራለሁ፡፡
የአጼ ምንይልክ ማርያማዊ መርሆ
ፊታውራሪ ወልደ ሐዋርያት ስለ አድዋው ድል የውጤቱን ድምር በሕይወት ታሪካቸው በገለጹበት 75ኛው ገጽ ላይ “የሴቶችን አገልግሎት ስገምት የበቅሎወች አገልግሎት ይታወሰኛል፡፡ በመጨreሻ የአድዋ ድል ድምር ስገምተው የተገኘው በሴቶች አገልግሎትና በበቅሎወች ብርታት መሆኑን ይታወቀኛል”(57)፡፡ አሉ፡፡
አገርና ዐለም አቀፍ የሰፊና ጥልቅ ባህርይ ጥንቅር ያለው የአድዋን ድል የመሰለ ትንግርት ቀርቶ፦ ባንድ ዘመን ባንድ ትውልድ ባንዲት ወረዳ የምትፈጸም ክስተት በብዙ ዘርፎች ትገለጻለች፡፡
የአድዋው ድል የምትገለጽባቸውን ብዙ ዘርፎችን ለሚመለከታቸው ሊቃውንት ትቼ በወቅቱ የነበሩት መንፈሳውያን አባቶቻችን በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ላይ በቀረጹት በማርያማዊው መርኋቸው ላይ ብቻ ላተኩር እወዳለሁ፡፡
አጼ ምንይልክ የተከተሉትን ማርያማዊ መርሆ ከየት አገኙት?
አጼ ምንይልክ ማርያማዊ መርኋቸውን ከየት አመጡት? እንዴትስ ከብሔራዊው አረበኛነትና ነጻነት ጋራ በማገናኘት ለሕዝብ መቀስቀሻ ተጠቀሙበት? በሰፊው ህዝብ አዕምሮ ላይ የቀረጹት በዚያ ዘመኑ የነበሩት የካህናቱን ሚና ምን ይመስል ነበር? በዚያ ዘመን የነበሩት ካህናት ይህን ማርያማዊ የድል መርሆ ከየት አመጡት?
ለእነዚህ ጥያቄወች መለሱን ለማግኘት “ማርያማዊ መርሆ” ከዚያም በፊትም ሲካሄድ ኖሮ በቅብብሎሽ የመጣ እንጅ በአጼ ምንይልክ ዘመን ብቻ ድንገት የተከሰተ ስላልነበረ ወደ ዝክረ ሊቃውንቱ ቅኔወች መዝለቅ ግድ ይሆናል፡፡ በአጼ ምንይልክ ዙሪያ ለነበሩት የጦር መሪወችና ለሕዝቡ አዲስ ባለመሆኑ የነበረው ህዝብ በካህናቱ የተሰበከውን ማርያማዊውን መፈክር አጼ ምንይልክ በአዋጅ መልክ ሲያቀርቡት ወዲያውኑ በመቀበል ወደ ተግባር ለውጦታል፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩት ካህናት “በክንዱ ኃይል አድርጓል ተቢተኞችን በተናቸው ግዠወችን ከዙፋናቸው አወረዳቸው የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዷቸውን ሰደዳቸው፡፡ ለአባቶቻችን ለአእብርሃምና ለዘሩ እንደተናገረ ”(ሉቃ 1፡51_54) ብላ ቅድስት ድንግል ክርስቶስን ስትጸንሰው ከተናገረችው ወስደው በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ቀርጸውታል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ማርያማዊ መግለጫ እንዳይዘነጋ በጸሎት ሰይማ በየቀኑ በመድገም መመሪያችን እንድናደርገው በጭንቅላታችን እንድንቀርጸው በቃላችን ደጋግመን እንድንናገረው አድርጋናለች፡፡
ኃይል የሚጠይቅ አዲስ ነገር ለማድረግ ከመሰማራታችን በፊት በጥበብ በልምድ በትምህርትና ከኛ ወደ ላቁ አባቶች ሄደን በፊታቸው ተንበርክከን የምንሸኘው በጸሎተ ማርያም (በመቤታችን መግለጫ) ነው፡፡ በነአጼ ምንይልክ የተፈጸመውን ይህን ማርያማዊ መፈክርም ሆነ ሌሎችን ሁሉ ቅርሶች ጥንታውያን መሆናቸውንና ከነሱ በፊትም የነበሩ መሆናቸውን የምናውቀው እስካሁን ድረስ በመካሄዳቸው ነው፡፡
እመቤታችን ክርስቶስን ስትጸንሰው የተናገረችውን ከየት ወሰደችው? መሠረታዊ ታሪኩስ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ መነሳት አይቀርም፡፡ መቼ፡ ማን እንደጀመረውና እንዴት ወደኛ እንደተሻገረ መገለጽ ቢኖርበትም፤ ሰፊ ሐተታውን በዚህች አጭር ጦማር ማቅረብ ስለማይቻል፤ ከዚህች ጦማር በኋል ለማስከተል አዘግይቼ፤ ወቅቱን ወደ ሚያሳየው፡ ኢትዮጵያውነትን ሁለንተና ወደሚጠቁመው፡ በመናድ ላይ ያለውን ስርአት ወደ ተሸከመው ወደ ቅኔው ትምህርት እሻገራለሁ፡፡
የቅኔው ትምህርት
የቅኔውን ትምህርት የጠቀስኩ አዳዲስ ሐሳብ በማመንጨት ስለሚረዳ ነው፡፡ የቅኔው ትምህርት እንደ ዜማው ትምህርት በምልክት የተቀየደ አይደለም፡፡ በተፈጥሮና ባካባቢው የሚከሰቱትን አዳዲስ ክስተቶችን ለማሳየት የሚረዳው የቅኔው ሥርአተ ትምህርት በመሆኑ እንጅ ዜማውም ለኢትዮጵያ ውበት ከሰጡት ኪነታት አንዱ መሆኑን በመዘንጋት አይደለም፡፡
መንፈሳዊያን አባቶቻችን በአጼ ምን ይልክ ጭንቅላት ላይ የቀረጹት “ማርያማዊ መርሆ” ቅድስት ድንግል ማርያም ክርስቶስን ስትጸንሰው ካሰማቸው መግለጫ ወስደው ነው፡፡ መርሆውን በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ላይ መቅረጽ ብቻ አይደለም፡፡ በዘመኑ የነበረው መገናኛ ያብነቱ ተማሪወች ነበሩ፡፡ ባላአገር አዳዲስ ሀሳብ የሚያገኘው ርስበርሱ የሚናበበው የጉባኤውን ትምህርት ለመማር አበባ እንደሚቀስሙ ንቦች ከደብር ወደ ሌላ ደብር ከአገር ወደ ሌላ አገር በሚዘዋወሩት የቅኔ ተማሪወች አማካይነት ነበር፡፡ በጠላትም አስቀድመው የሚገደሉት እነሱ ነበሩ፦
“ካህን ሞተ ተብሎ አይነግሩም አዋጂ
እንዲያው በየደብሩ መላክ ነበር እንጂ” ተብሎላቸዋል፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም መፈከር (መግለጫ) የተወሰደው ማርያማዊው መርሆ ከአርባኛነተቻን (40ኛ) ጋራ የተያያዘ በመሆኑ ቦበታው ለመገጽ አሁን አልፈዋለሁ፡፡
በዚህች ጦማር ከኢትዮጵያዊው አርባኛነት ጋራ ተዛምዶ በቅኔያችን ሲነገር የሰማሁትን ከዚህ ቀደም ባቀርበውም ከቅኔው ትምህርት ጋራ ንክኪ ያላቸው ኮፌዳውንና ከየመንደሩ እየዞርን የምንሰበስበው ምግቡ ሁሉ የተያያዘ ነውና አሁንም አቀረበዋለሁ፡፡
ኮፌዳዋ
ወደ ቅኔው ትምህርት በጥለቀት ከመግባቴ በፊት ላስኳላው ተማሪወች መምህሮች ላስታውሳችሁ የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡ ይኸውም ስለ ሕዝባዊ ግንባታ በምትነጋገሩበት አውድ ላይ “Quantum physics and the Quest for the Elusive National Dialogue in Ethiopia” በሚል በአቶ ጸሐይ ደመቀ የቀረበው ነው፡፡
በአቶ ጸሐይ ደመቀ የቀረበውን የQuantum physicsን ትንታኔ በአዕምሯችሁ ቋጥራችሁ አባቶቻችን የኢትዮጵያዊነትን ሁለንተና የሰሩባቸውንንና የገነቡበባቸውን ከዚህ በታች የማቀርባቸውን ስልቶች ብትመለከቱ ራሳችሁን የምትታዘቡ ይመስለኛል፡፡
ከኮፌዳዋ እጀምራለሁ፡፡ ከየቤቱ የምንሰበስበውን ምግብ የምንይዝባት ኮፌዳችን ከቄጠማ ወይም ከሰሌን እንሠራታለን፡፡ ኮፌዳችንና ከየቤቱ የምንለምነው ምግብ ለሰምና ወርቅ ቅኔ ትምህርታችን የሚሰጡን ቅድመ ዝግጅት (orientation training) ነው፡፡
ኮፌዳችን ለኢትዮጵያ መግለጫ ሰም በመሆን ታገለግላለች፡፡ ኢትዮጵያ ለኮፌዳዋ ወርቅ ትሆናለች፡፡ ኢትዮጵያን ወርቅ ኮፌዳዋን ሰም በማድረግ የቅኔውን ትምህርት እንጀምራለን፡፡ ኢትዮጵያን የምትወክለው ኮፌዳችን በሰበነክ አይጦች ከተደፈረች ኢትይዮጵያውያን ይበተናሉ፡፡ ይላሉ፡፡ ቅኒያችን ወራራወችን በሰበነክ አይጦች ይገልጻቸዋል፡፡
ባዶ ኮፌዳ ተሸክመን ከጎጇችን ስንወጣ ባዶነት አይሰማንም፡፡ በየደጃፉ ቆመን በእንተስማ ለማርያም ስለ እማምላክ ብለው” እያልን የምናሰመውን የእመቤታችንን ስም ስንቅ በማደረግ ነው፡፡ “ስሟ ስንቅ ነው የእመቤቴ” የሚለው የአድዋው ጦርነት የታጀበት የናቶች እንጉርጉሮ የተወሰደው ካብነቱ ተማሪወች ነው፡፡
ከየቤቱ በስሟ የምንሰበስበው ምግብ ወደ ኮፌዳችን ሲገባ ስሙ ይቀየራል፡፡ ውጥንቅጥ ይሆናል፡፡ ኮፌዳችንን ኢትዮጵያን የምትወክል ሰም እናደርጋታለን፡፡ በኮፌዳችን ሰብስበን የያዝነውን ውጥንቅጥ ህዝቡን የሚወክል ወርቅ እናደርገዋለን፡፡ ኢትዮጵያን በሰምነት የምታገለግለን ኮፌዳችን እንዳትቀደድ አይጥ በማትደርስበት ቦታ እናስቀምጣታለን፡፡ ኮፌዳችን በሰምነት የምትገልጻት ወርቂቱ ኢትዮጵያ ዳርድንበሯ እንዳይቀደድ እንድንጠነቀቅ መምህሮቻችን ያስጥነቅቁናል፡፡
ከላይ እንዳልኩት ከተለያዩ ቤቶች ሰብስበን በውስጧ የከተተነው ምግብ አንድ አይነት አይደለም፡፡ ወደ ኮፌዳችን ሲገባ ስሙ ተቀይሮ ውጥንቅጥ እንለዋለን፡፡ ውጥንቅጥ የሚለውን ቃሉን ለሁለት በመሰንጠቅ ሰምና ወርቅ በማድረግ እንቀኝበታለን፡፡ “ውጥን” ማለት ጅምር ሲሆን “ቅጥ” ማለት ደግሞ ቅርጽ ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ሲደመሩ “embryo” ማለትም የጅምር ቅርጽ ማለት ነው፡፡ “ወጥቅጥ” ማለትም ይሆናል፡፡
በየቤቱ እየዞርን የምናሰማው የልመና ድምጽ “በእንተ ስማ ለማርያም፡ ስለ እመአምላክ ብለው” የሚለው ነው፡፡ በዚህ የልመና ጥሪ ድምጽ ከተለያየ ቤት የምነሰበስበውን የተለያየ ምግብ “ውጥንቅጥ” የሚለው የምግቡ ስም ከነጠላው ሰምና ወርቅ ቅኔ ትምህርታችን ሌላ ሠረዝ ለሚባለው ቅኔ መሠረትነት አለው፡፡ “ ውጥንቅጥ” ማለትም “ድብልቅልቅ” (ቅልቅል) የሚል ትርጉም አለው፡ ከነጠላ ሰምና ወርቅ በላይ እንደቀይ ሽንኩርት የተደራረቡና የተነባበሩ ብዙ ወርቆችና ብዙ ሰሞች ማለት ነው፡፡ ይህም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመላ ኢትዮጵያውያንን ሰውነት የተሸክመ መሆኑን ያሳያል፡፡
ውጥንቅጥ የሚለው ከሁለት ቃላት የተጣመረ ይሆንና ሌላም ትርጉም አለው፡፡ “ውጥን” ማለት ጅምር ሲሆን “ቅጥ” ማለት ቅርጽ ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ሲደመሩ በቀጥታ የተጀመረ ማለት ሲሆን የቅኔያችን ቅርጽ ኢትዮጵያዊነት በቀጥታ የተጀመረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥየ የቅኔውን ውስጣዊ ይዘት እዳስሣለሁ፡፡
የቅኔው ይዘት
የቅኔ መጀመሪያ መቁጠሪያችን ፊደል ጉባዔቃና ትባላለች፡፡ የሕብረተ ሰብ ጅምር የሆነችውን አንዲትን ትዳር እንገልጽባታለን፡፡ በሰውነታችን አንዲት nucles የምትባለው ሕዋስ “structures that contain the hereditary information” እንደ ምትባለው ጉባዔቃናም የህብረተ ሰቡ ስሪት ለሚገለጽበት ማሕበራዊ ቅኔ መነሻ ናት፡፡
ጉባዔቃና አራት ሐረጎች ሁለት ቤት መምቻ ግጥሞች አሏት፡፡ አንዲት ማሰሪያ ግሥ (verve) አላት፡፡ በባልና በሚስትነት የተዋቀረችውን አንዲት ትዳር ትወክላለች፡፡
ባል ካንድ ቤት መጥቶ፤ ሚስት ከሌላ ቤት መጥታ በመጣመር የሚመሠረቱትን ትዳር ያሳያል፡፡ ባልም ሚስትም ከወንዱና ከሴት አያቶቻቸው የተገኙ ናቸው ፡፡ ይህም ማለት አራት ትውልዳውያን ሐረጎች መጥተው በመጋባት ባንዲት ጎጆ ከሚኖሩ ባልና ሚስት የተወለደው አንድ ኢትዮጵያዊ ለአካላዊ መራራቅ መሰብሰቢያና ማሰሪያ ግስ ነው ማለት ነው፡
በግእዝ ቋንቋ የምንማረው የቅኔው ስልት ከአማረኛው ስነ ጽሑፍ ይልቅ እጅግ የጠለቀ ነው፡፡ የአማረኛው ስነ ጽሑፋችንም ቢሆን ሆን ተብሎ ስለተዘመተበት ዛሬ ይዳከም እንጅ ከግእዙ traditional grammar ጋራ እየተወዳደረ በመገስገስ ላይ ነበር፡፡
በአማርኛ ሰዋሰዋችን በተመሳሳይ ፊደላት የሚገጠሙትን ብንሰርዛቸው ስድ ንባብ ይሆናል፡፡ በግጥም የተዘጋጀውን ሀሳብ ቤት መታ ሲባል ያልገጠመውን ስድ እንለዋለን፡፡ ቤት በመታ ግጥም በሕገ ተፈጥሮ በትዳር መስመር የተሰለፈውን ዜጋ እንገልጸዋለን፡፡ በግጥም ቤት ባልመታ ስድ በሚባለው ሀሳብ ትዳር ያልያዘውን ዜጋ እንገልጸዋለን፡፡
በጉባኤ ቃናዋ ያሉት አራቱ ሐረጎች ባባትና በእናት በኩል ያሉትን የወንድና የሴት አራቱን አያቶች የወክላሉ፡፡ ያንድ ኢትዮጵያዊ አያቶች ካንድ ነገድ ወይም ጎሳ ብቻ የተቀዱ ሳይሆኑ በግድም ሆነ በውድ በማወቅም ሆነ ባለመወቅ ከየቤቱ እንደምንሰበስበው ምግብ እየተቀላቀልንና እየተወናቀጥን የመጣን መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡
በዚህ ስሌት የሚያድገው የመጨረሻው ቅኔያችን በስምንት ቤት ግጥም የተዋቀረው መወድስ የሚባለው ነው፡፡ በጉባኤ ቃናችን አራት የወንድና የሴት አያቶችን ዘር ስንከተል ወደ ስምንት ቤት የሚደርሰውን የዘር ስርጭት ይወክላል፡፡ ይህም ማለት ከስምንት ቤት በኋላ የትውልዳችንን የዘር ግንድ መሰብሰብ ወደ ማንችልበት ሐርግ መገባታችንን የሚጠቁም ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን በቋንቋ፡ በባህል፡ በሃይማኖት፡ በወንዝና በሸንተረር ተበታትነን ብንኖረም በደምና ባጥንት ግኙነት የተሳሰርን እንደ ቀይ ሽንኩርት የተነባበርን ሠረዞች መሆናችንን የሚያሳይ ነው ይላሉ፡፡
የተደራረቡ የሰምና የውርቅ ጥንቅሮች ዋና ማሰሪያቸው አንዲት ቃል ግስ ወይም verbe መሆኗን በጉባዔ ቃና እንዳየነው፡ መወድስ በምንለው ሰፊ ሠረዝ ቅኔ ሰፊውን አካላት በእኩል ደረጃ የምትገልጽው አንዲት ግስ ናት፡፡ ይህችን ግሥ “dichotomy” የምትለው ቃል ከሞላ ጎደል የሚገልጻት ይመስለኛል፡፡ እጽፍ ድርብ “dichotomy” የሆነችው ቃል እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የምትወክልና የምትገልጽ ናት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ dichotomized (ሕብር) ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ራሱን dichotomized እያደረገ ኢትዮጵያዊውን ሕብረተ ሰብ ሲገነባ ኖሯል ይላሉ፡፡
እንደ ቀይ ሽንኩርት የተደራረበ ሕብረተ ሰብ (ሕብረተ ሰባዊ ግንባታ)
በግእዝ ቋንቋ የምንማረው ቅኔ የሕብረተ ሰቡን ስሪት በጥልቀት እንደሚገልጸው አይተናል፡፡ የአማረኛው ስነ ጽሑፋችን የሕብረ ሰባዊነታችንን ሠረዛዊ ድርብርብነት በአቶ ጸሐይ ደመቀ ከቀረበው ከ Quantum physics ትንታኔ ባላነሰ ፈሊጥ ይገልጸዋል፡፡
የQuantum physics ትንታኔ በአዕምሯችሁ ቋጥራችሁ አባቶቻችን የኢትዮጵያዊነትን ሁለንተና የሰሩባቸውንና የገነቡበባቸውን ከዚህ በታች የማቀርባቸውን ስልቶች ብትመለከቱ ራሳችሁን የምትታዘቡ ይመስለኛል፡፡
ከዚህ በታች በስድስት ዝርዋን ቃላት በሚጠናቀሩ አገባቦች ሕብረሰባዊነታችንን አማረኛ ሰዋሰዋችን እንዲት እንደሚገልጸው እንመልከት፡፡
1ኛ ባለ፡ 2ኛ፦ጋራ፡ 3ኛ፦አምጣ፡ 4ኛ፦ደም፡ 5ኛ፦አገር፡ 6ኛ፦ቤት ናቸው ፡፡ በጥንቃቄ ትኩረት ተራ በተራ እንያቸው፡፡
1ኛ ባለ፦ባለ የምንላት ሁለት ፊደላት ከቀሩት 5ቱ ቃላት ጋር እየተደመረች የሕብረተሰቡን ጥንቅር ትገልጻለች፡፡
2ኛ ባለ_ጋራ፦ የምትለው ሁለት ፊደል ከጋራ ጋራ ስትደመር፡ አንድ ቃል ባለጋራ ትሆናለች ይህም ማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከሰውነቱ ከደሙ ካጥንቱ ጀምሮ ከሰውነቱ ውጭ በኢትዮጵያ ምድር እስካለው ቆስቁስ ድረስ የማይጋራው የግሉ የሆነ ነገር የለውም፡፡ ማለት ነው፡፡
3ኛ ባለ_አምጣ (አንጣ) ማለትም ፦ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የማይወራረሰው የማይወሳሰደውና ማይቀባበለው አምጣልኝ ላምጣልህ የማይባባለው የለም፡፡
4ኛ ባለ_ደም፦ኢትዮጵያው ከሌላ ጋራ የማይጋራው ንጹህ ወጥ የሆነ ደም የለውም፡፡ ሁሉም ለሁሉ የደም ባለቤት ነው፡፡
5ኛ ባለ_አገር፦እየንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ለተዘረጋቸው ኢትዮጵያ ባለ አገር ነው፡፡ ኢትዮጵያ አገሩ ናት፡፡ በተለይም የዘመኑ ትምህርት ሲገባ ከተማነት እያየለ ሲሄድ ባላገርነት ያለመሰልጠን የኋላ ቀርነት መገለጫ መሰደቢያ እየሆነ መጣ፡፡
6ኛ ባለ_ቤት፦ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጠረፍ እስከጠረፍ በተዘረጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰበት ባለቤት ነው፡፡ የአማረኛችን ስነ ጽሑፍ እንደሚያመለክትን ሁለት ባህርያት ስድና ግጥም የምንላቸው አሉን፡፡ ስድ ማለት በትዳር ግጥምጥም ያልተወሰነውን ሰው ሲያሳይ ግጥሙ ደግሞ ከተለያዩ ቤቶች የተወለዱ ዜጎች ተጋጥመው የሚኖሩትን ጋብቻ ያመለክታል፡፡ ቤታ መታ ይባላል፡፡
ጠላቶች በየዘመናት ኢትዮጵያን ሲያፈርሱና ሕዝቡን ሲበታትኑት በየዘመናት የነበሩ ሊቃውንት ኢትዮጵያውያን ደግሞ መልሰው ህዝቡን የሚያስተሳሩባቸውና ኢትዮጵያን የሚገነቡባቸው እስካሁን የተገለጹትን ሕዝቡ ወደ ተግባር የሚለውጡባቸው እሴቶች የሰንበቴና የጽዋዕ ማኅበራትም ነበሩ፡፡ በዚህ አጋጣሚ እነዚህንም እሴቶች ልንዳሣቸው ይገባል፡፡
በቅኔው በሰዋሰው የተሠራው ሕዝባዊ ስሪት የተገነባበት ሌላው ዘዴ ሰንበቴና የጽዋዕ ማህበራት
ሕብረተ ሰቡ በየወሩ የሚገናኙባቸው የጽዋዕ ማሕበራት በየሳምንቱ የሚገናኙባቸው ሰንበቴወች አሉ፡፡ በማርያም በጻድቃን በሰማእታትና በመላእክት ስም በ12 ቁጥር ተወስነው በየሳምንቱ የሚገናኙባቸው የጽዋ ማህበራት አሉ፡፡ ማሕበራቱ በቀኑ ሰአት በአመቱ ወራት በሐዋርያትና በ12 ነገደ እስራኤል ቁጥር ልክ በሙሴ ስም የተዋቀሩ ናቸው፡፡
የቀኑን ሰአት የአመቱን ወራት የሐዋርያትንና የነገደ እስራኤልን ቁጥር ለመግለጽ ብቻ አይደለም፡፡ ሶስቱ ስላሴንና አርባእቱ እንስሣን እያስታወሰን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ እያልን ከምንጸልይባቸው በአራቱ ጣቶቻችን ላይ ካሉት 12 አጽቆቻችን ጋራ የተሳሰሩ ናቸው፡፡
በአራቱ ጣቶቻችን ላይ ያሉት 12 አጽቆች ባንዲት ጣታችን ላይ ላሉት ለ3 አጽቆች ሲካፈሉ አራት አጽቆች ይደርሳሉ፡፡ ጸወርተ መንበሩን አራቱን እንስሦች ያመለከታሉ፡፡ እንደገና በአራቱ ጣቶቻችን ላይ ያሉትን 12 አጽቆች ለአራት ጣቶቻችን ሲካፈሉ በመንበረ ጸባዖት ላይ ያሉትን ስላሴወችን ያመለክታሉ፡፡
“በእንተ ማርያም መሐረን ክርስቶስ” ብለን ጸሎታችን የምንዘጋው በሙሴ ሊቀመንበርነት በሚመራው በጽዋ ማህበራት አባላት ቁጥር፡ በሰአተ መአልቱና በሰአተሌሊቱ ቀመር ባመቱ 12 ወራቶች፡ በሐዋርያትና በ 12 ነገደ እስራኤል ቁጥር ልክ ነው፡፡ ለምን ከሙሴ ጋራ ተያያዘ ለሚለው ከላይ እንዳልኩት ሐተታው ሰፊ ስልሆነ በሚቀጥለው ጦማር ለመግለጽ በማለፍ እስካሁን የተገለጹት ስርአታት መቼና እንዴት እንደፈረሱ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡
መቼና እንዴት ፈረሱ?
መቼ ፈረሱ፦ያስኳላውን ትምህርት ይዘውት የገቡ ፈረንጆች ትምህርቱን በመጀመሪያ በተማሪወቻቸው ጭንቅላት ማስረጽ በጀመሩበት ወቅት መፍረሱ ተጀመረ፡፡ በዶክተር ክነፈርግብ ዘለቀ ሰብሳቢነት በተዋቀረው በጊዜአዊ ተሐድሶ ጉባኤ መሳሪያነት የካቲት 10 ቀን 1968 የደርግ መንግሥት በገሀድ አፈረሳቸው፡፡
ዶክተር አረጋዊ በርሔ “A Political History of the Tigray people’s Liberation Front (1975-1991)” በሚል ርእስ ለDoctoral dissertation (page 300) ባሳተሙት መጽሀፋቸው (page 246) ላይ እንደተገለጸው የማፍረሱ ተግባር በወያኔወች ተፈጸመ ፡፡
“Thirdly, the TPLF launched a series of conferences or ‘seminars’ for selected parish priests in 1979 to win them over The underling motive of the seminars was to isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian church in order to foster Tigrian nationalism along the line of the TPLF’s strategic objective. Suppressed Tigrian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial woreda seminars for priests were conducted by an eloquent TPLF fighter, Gebre Kidan Desta., a graduate of The Theological College at Addis Ababa University The themes of the seminar were to replace the Ethiopian Church’s authority by a TPLF- minded church and the language in the church with Tigrigna and, ultimately to further Tigrian nationalism and identity. This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church’s national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the well-established monasteries in Tigrai such as Debre Damo, by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of the TPLF. . In 1987 and 1989, regional and national conferences for priests were organized by the TPLF in the liberated territories to reshape the Tigrai church in line with the TPLF programme.” A separate secretariat of the Orthodox Church was formed in the liberated areas of Tigrai and was supposed to operate under the TPLF guidelines. Practically, the Ethiopian Church was divided in to two separate secretariats, one under the regime and the other under TPLF. Both worked in Tigrai until 1990, when the TPLF overran Meqele, the capital of Tigrai. The regime’s secretariat fled Meqele for Dessie and the secretariat in the liberated territories entered Meqele and operated until the TPLF seized power in1991.”
ወደ አማሪኛ ሲተረጎም
የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በ1979 አመተ ምህረት አስተሳሰብ ለዋጭ የፕሮፓጋንዳ መርሀ ግብር ለሚመለምላቸው ቀሳውስት ዘረጋ። የማሰልጠኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኗን ከህዝብ ለይቶ በመምታት ስፋቷን ማጥበብና በትግሬአዊነት ላይ ብቻ የተመሰረተ ስሜት በትግራይ ተወላጆች ጭንቅላት መክተት ነው።
ቤተክርስቲያኗ ለረዥም ዘመናት በህዝቡ አዕምሮ ላይ ስትተቀርጸው የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያነትን ስሜት ከትግራይ ህዝብ አዕምሮ ጠራርጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው።
የወረዳ ስልጠና የተጀመረው በጠንካራ ትግሉ የታወቀው ካዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገረ መለኮት ትምህርት የተመረቀው ገብረ ኪዳን ደስታ ነው። የስልጠናውም ይዘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላላ መዋቅራዊ አስተዳደር በትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ባለሟሎች መተካትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አካባቢ የትግርኛ ቋንቋ እንዲሰፍን ማድረግ ነው።
በዚህ መንፈስ ተቀረጾ የተዘረጋው እቅድ በየሰበካውና አጥቢያው ያሉትን ቄሶችና ምእመናኑን ቤተ ክርስቲያኒቱ ጠብቃ ካቆየችው ታሪክና ብሄራዊ መዋቅር እየገነጠሉ በመስኮብለል ወደ ነጻ አውጭው አምባ መሰብሰብ ነው። መነኮሳት በመምሰል ደብረ ዳሞ ወደ መሳሰሉት ገዳማት ሰርጎ በመግባት የድርጅቱን እቅድ በማስተጋባት የሚያዳክም አጥኝ ኃይል በስብሀት ነጋ መሪነት ተመሰረተ። የማሰልጠኑ ተግባር ከተፈጸመ በኋላ፤ የሰለጠኑት አስመሳይ መነኮሳት በትግራይ ምድር ዙሪያ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ከዋናው ጽፈት ቤት መገንጠልን በ1987 እና በ1989ተግባራዊ እንዲያደርጉት አደረገ።
ከነጻ አውጭው አመራር የሚቀበለው መነኮሳት እየመሰለ ሰርጎ የገባውአስመሳይ ቡድን፡ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መዋቅር ተገንጥሎ ከነጻ አውጭው ጋራ ጎን ለጎን የማካሄ ስራውን ቢሮ ከፍቶ ጀመረ። በዚህ ጊዜ ከዋናው ጽ ቤትና ከነጻ አውጭው ትእዛዝ በሚቀበሉት ቡድኖች መካከል የጎላ ልዩነት በግልጽ መታየት ጀመረ። እስከ 1990 ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ፤ ነጻ አውጭው መቀሌን ሲቆጣጠር፡ ከዋናው ጽ ቤት አመራር ይቀበል የነበረው መቀሌን ለቆ በ1991 ወደ ደሴ ሲሄድ፡ በነጻ አውጭው ስር ይመራ የነበረው ቡድን መቀሌውን እንዳለ ተረክቦ ተቆጣጠረ”፡፡
አጼ ምንይልክ በአድዋ ድል የተቀዳጁበትን ማርያማዊ መርኋቸውን መነሻ በማድረግ በተከታታይ ሳምንታት በጠቅላዩ መሪነት የተደረጉትን ስብሰባወች በዚህች ጦማር ዳሰስኳቸው ተመለከትኳቸው፡፡
ማርያማዊ መርሆውን በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ያሰረጹት ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት ኢትዮጵያን ያነጹባቸውንና የገነቡባቸውን ስርአቶች ፈተሽኩ፡፡ በዚህ ዘመን ላይ ያለነውን ካህናት በተለይም ሲኖዶስ በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ላይ ማርያማዊ መርሆውን ከቀረጹት ሊቃውንት መንፈሳውያን አባቶች ጋራ አነጻጸርኩ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዚህ ዘመን ያለነውን ካህናት ባዶነት ተገነዘብኩ፡፡
የዘመናችን ምሑራን ስለ ሀገር በሚነጋገሩበት አውድ ላይ “Quantum physics and the Quest for the Elusive National Dialogue in Ethiopia” በሚል ርእስ በአቶ ጸሐይ ደመቀ ቀርቦ፡ ባጋጣሚ ያየሁትን የዘመናችን ፍልስፍና ጥንታውያን አባቶቻችን ኢትዮጵያን ካነጹባቸውና ከገነቡባቸው ስልቶች ጋራ አወዳደርኳቸው፡፡ በዚህ ዘመን ተማርን የምንል ሁሉ ያስኳላ ተማሪወች ከጥንታውያን ሊቃውንት አባቶቻችን ልንሻል ቀርቶ ከደረሱበት መድረስ ያልቻልን ኋላ ቀሮች መሆናችንን ተረዳሁ፡፡
በጠቅላዩ በተቃኙ ከአድዋው የመተሳቢያ በዐል ጀምሮ እስከ ሙስሊም ወገኖቻችን ተከታታይ ስብሰባወች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተዘመተባት ከዚህ በላይ በተገለጹት ስርአቶች የኢትዮጵያን ሕብረተ ሰብ ስትገነባና ኢትዮጵያን ከወራሪወች ስትጠብቅ በኖረችው ኦርቶድክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ አይደለምን? ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት በአጼ ምንይልክ ጭንቅላት ከቀርጹት ኢትዮጵያ ድል ከተቀዳጀችበት ከማርያማዊ መርሆ ሌላ ምን የፈረሰ ነገር አለ?
ለመቀጠል እዚህ ላይ ይቆየን፡፡