ወልቃይት ተጀምሯል | እነኮሎኔል ደመቀ ወዴት…? “ከሞት ያመለጥኩት ለጥቂት ነው” አበባው | ጎንደር ፋኖ 2 ከተማ ተቆጣጠረ | ወልቃይት ውጥረት ነግሷል ደ | ኤፌሳር ሙሉ የጁላ ሰራዊት ተደመሰሰ | ከመቀሌ እስከ ሰቆጣ ከፍተኛ የአብይ የጦርነት ዕቅድ |

March 18, 2024

 

 

 

https://youtu.be/MjEgRq574cE?si=Mrnhynq7i9ejG-1w

https://youtu.be/Ci7yh9H05wI?si=MXhQxgC8_mOiU1sX

 

https://youtu.be/VtV7l2PeRBo?si=bAca3cpvoJFU5E3E

 

 

3 Comments

 1. ኢትዮጵያ እጅግ ውስብስብ የፓለቲካ ሴራ ውስጥ ናት። የአሜሪካው ጉደኛ የስለላና መንግስት አፍራሽ ክፍል በቅርቡ በትግራይና በአማራ ጦርነት እንደገና ሊፈነዳ ይችላል በማለት ወሬውን ካናፈሰ ቀናታት አለፉ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ የመከላከያ ቁንጮ ስለ ወልቃይትና ሌሎችም አወዛጋቢ ጉዳይ የፕሪቶሪያውን ውል አስመልክቶ የተናገረው ጉድ የሚያስብል ነው። አሁን በወልቃይትም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ትጥቅ የሚፈታ ማንም እንደማይኖር እየታወቀ ሰውን ለማስጨረስ ጠ/ሚሩ ነገሩን አቃሎ በማየት ከመከላከያ ውጭ ማንም ታጣቂ አይኖርም ማለት ምን ማለት ነው? 250 ሺ ሰራዊት አስቀምጦ ወያኔ የሚቀልበው ስንዴ እንዲያመርቱለት ነው እንዴ? ይመለሱ የሚባሉትስ የትግራይ ሰዎች እነማን ናቸው። ሰው በቆንጨራ ጨፍጭፎ፤ ሰራዊቱን በተኛበት አርዶና አሳርዶ እንደገና በሰላም ስም እሳት ለመለኮስ ነው ወይስ በእርግጥ ምድሪቱ የሁሉ ናት ተብሎ ሁሉም አርፎ ሊኖርባት ነው? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር!
  ጠ/ሚሩ የተማታበት ሰው ነው። የሶማሊያ ክልል ፕሬዚደንት የነበረውን የወያኔ አገልጋይና ጨካኝ ከሥር የፈታው ለማን አስቦ ነው? የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት የመዘበረውንና መርከብ ሳይቀር የሸጠውን ጄኔራል መፍታቱ ለምን ተብሎ ነው ጄ/ ጻድቃንን ስጡኝ ብላቸው እምቢኝ አሉኝ የሚለው ጄኔራሉ ከወያኔ እባቦች መርዘኛውና አደገኛው መሆኑ ጠፍቶት ነው? ኢትዮጵያን ለማጥቃት አሁን ነው ብለው ኤርትራና ሱማሊያ እየመከሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሌላ ግጭትና ጦርነት በሃገር ውስጥ የሚቀሰቅሱና እጃቸው በደም የተነከረ ሰዎችን ከእስር መፍታት ምን የሚሉት ሰላም ነው? ግን የተሳከረ ፓለቲካ ሁሌ ማደፍረስ እንጂ የጠራ ጉዳይ ላይ አተኩሮ አያውቅም። የማይታሰረውን ማሰር፤ መታሰር ያለበትን መፍታት። እንዲህ ያለ ጉድ በሃበሻ ምድር ዝንተ ዓለም ይፈጸማል። አሁንም በአሜሪካ አይዞህ ባይነትና መሪነት ድጋሜ በወልቃይትና በሌሎችም ጉዳይ ሰበብ ጦርነት እንዲጫር በዚህ በዚያም የውስጥና የውጭ ሃይሎች እየጣሩ ነው። እሳቱም ይነዳል። የሚበላውንም ይበላል። የሱማሊያው መሪ በተደጋጋሚ ወደ አስመራ የሚያቀኑት የዳቦ ድቄት ፍለጋ አይደለም። የኤርትራው መሪ ካይሮን ደጀ ሰላም ያደረገው ለህዝቡና ለምስራቅ አፍሪቃ ሰላም ሽቶ አይደለም። ሴራው በሶስት ገመድ የተገመደ ነው። በቅርቡም ይህ ሁኔታ ግልጽ ይሆናል!
  ባጭሩ ምድሪቱ አስፈሪ ጊዜ ላይ ናት። ገዳይና አስገዳይን እየፈቱና እያስታጠቁ፤ ዞሮ ተመልሶ ሰላም ጠፋ ማለት ቧልት ነው። ወያኔ እያለ የትግራይ ህዝብ ሰላም አያገኝም። ራሱ ጠ/ሚሩ 200 ሚሊዪን ብር ለት/ቤት ማሰሪያ ከባለቤቱ በኩል ወደ ትግራይ ተልኮ ወይ ት/ቤቱ አልተሰራ ወይ ብሩ አልተመለሰ መጽሃፉም ቄሱም ዝም መሆኑን በአደባባይ ነግሮናል። ወያኔ ያኔም ሌባ አሁንም ሌባ ወደፊትም ሌባ ነው። የሚለወጥ ባህሪ የላቸውም። 50 ቀን ሙሉ ተሰብስበው ፍሬ ብለው የነገሩን ሁለት ሴት ጓዶቻቸውን ከፓርቲ ማባረራቸውን ነው። አሁን ማን ይሙት ወንድ አባላት ከሴቶቹ በበለጠ ሁኔታ ያጠፉ የሉም። ግን በትግራይ ባጠቃላይ በሃበሻዋ ምድር ሴቶች ላይ ወንዶች የሚያደርሱት ግፍ አንድ ማሳያ ይህ የወያኔ ፍርድ ነው። ስንቶች ነው ትግራይ ውስጥ የሚያለቅሱት? ስንቶች ነው በረሃብ የሚንገላቱት። አሁን የጌታቸውን መድለብ፤ የደብረጽዪን ሰውነትን ማብረቅረቅ የተመለከተ የትግራይ ህዝብ ይራባል ቢባል ያምናል? ግን በስሙ ግማሽ ምዕተ ዓመት የተነገደበት የትግራይ ድሃና ገበሬ ህዝብ ዛሬም ይራባል፤ ይሰደዳል፤ ይሞታል፤ ግደል ሲሉት ይገድላል። ነጻነቱ ይሉሃል ይሄ ነው። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ።
  6 ቢሊዪን ብር የተዘረፈበት አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሌቦቹ ከውስጡ መሆናቸውን የተረዳ አይመስልም። ዝርፊያው ረቂቅና በውጭ ቴክኖሎጂ የታገዘ ነው። ይህን ያህል ብር ሲዘረፍ ያልነቃ ባንክ ከውጭ ዘብ ቢያቆም ከውስጥ የስለላ መረብ ቢዘረጋ ዋጋቢስ ነው። ሃገሪቱን ለማሽመድመድ ከሚሰሩ ሴራዎች አንድ ገቢያውን ማናጋትና ሰው በባንክ አገልግሎት አሜኔታ እንዳይኖረው ማድረግ ነው። እንግዲህ በዚህ ክፈኞች በሚቀባበሏት የሃበሻ ምድር ባለፈው ያየነውና የሰማነው ሊመጣ ካለው ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ነው። ገና ብዙ ፈተና ከፊታችን አለ? መንደር ቆጣሪውና በዘሩና በቋንቋው የሰከረው ታጣቂና ቆንጨራ ተሸካሚ ከተማና ገጠሩን ማበራየቱ አይቀሬ ነው። ይህ ግፍና ሥርዓት አልበኝነት ግን ማቆሚያው መቼ ነው? እንደገና በወልቃይት፤ በራያና በሌሎችም ወያኔ የእኔ መሬቶች ናቸው በሚላቸው ስፍራዎች ግጭቱ ይቀጣጠል ይሆን? ወይስ ጠ/ሚሩና በዙሪያው ያሉ እንደሚሉት መከላከያ ሰላም አስፍኖ፤ ምርጫ ተደርጎ ሰው ወደሚፈልገው ወገን ይጠቃለላል? ገዳይና ሟች/የሟች ቤተሰብ አንድ ላይ ተዝካር ላይ አይቆሙም። ጎረቤቱን አርዶ ወደ ሱዳንና ትግራይ የተሰደደ የወያኔ ቅጥር ዳግም ወልቃይት ገብቶ በሰላም ይኖራል ብዬ አላምንም። የሰው ደም ያፈሰሰ ሁሉ ደሙ ይፈሳልና! ግን ጠ/ሚሩ የሚያሽከረክሯቸው አሜሪካኖች በነፍሱ ገበጣ እየተጫወቱበት እንደሆነ አልገባውም። አሜሪካን ያመነ ውሃ የዘገነ! በቃኝ!

 2. ይቕረታ እርማት፣
  ብፀፋፍ ኣፍ ከይኮነስ ብፅሩይ ትግርኛ ከምነድምፆ:
  ሑመራ፣ ዓዲ ረመፅ፣ ፀገደ፣ ሽረ፣ ፀለምቲ፣ ኣኽሱም፣ ዓድዋ፣ ዓዲ ግራት፣ መቐለ፣ ዓቢይ ዓዲ፣ ተንቤን፣

 3. በዚህ እብድ ሰውዬ እልህ አገርን አብረን እያጠፋን ነው፡፡ እሱም ተንኮለኛ ነው እኛም ግፉና ሰቆቃው ባሰብን ሆደ አደር ምሁራን በዙ አገር ወደ መቀመቅ ገባች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

189361
Previous Story

ምስራቅ ወለጋ ሌላኛው የጦር ግምባር!የወለጋ አማራዎች እየተዋደቁ ነው | ህርዳር እና ጎንደር ሊሞሸሩ ነው | ባኮንኮች ውስጥ ያደፈጠው ኃይል

Eskinder Nega
Next Story

እስክንድር ነጋ እመራዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት የሚባል አለ ወይ?

Go toTop