ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
(ክፍል አንድ) ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
አዲስ አበባ ከተማ ያለ ጥንታዊ ታሪክ!!! A City Without Its Past ………. የሃገር ፍቅር ትያትር ቤት Demography Change
‹‹ምንሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ፣
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ!!!
ባትዋጋ እንኳ፣በል እንገፍ እንገፍ፣
የአባትህ ጋሻ ትኃኑ ይርገፍ!!!››
አብይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል!!! የተባለበት ዘመን ነው ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ በላይ ምን እስኪሆን ረስ ይጠብቃል፡፡ ከዳር ጀምረው ሲያፈርሱ እኛ ጋር አይደርስም ብለን ተቃውሞ በጊዜው አላሰማንም ዛሬ ከመኃል ደረሰ፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ነው፡፡ ደሀ ተኮር ፣ ማንነት ተኮር ማፈናቀል ነው፡፡ የግል ባለንብረቶች፣ ካርታ ያላቸው ሁሉ ቤታቸው ፈርሶል፡፡ ህብረተሰቡን ሳያማክሩና ጊዜ ሳይሰጡ ፣ እቃ ሳያወጡ ቤት ማፍረስ ትልቅ ጭካኔ ነው፣ ፋሽስቱ ጣልያንም አላረገው፡፡ ሰው ጤፉ ከበሻሻ ጎጆ ቤቱ ወጥቶ፣ የሰው ጎጆ እያፈረሰ ቤተ-መንግስት የሚያንፅ ጠንቆይ አዲስ አበባን አስለቀሳት፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት! ፒያሳ አካባቢ የአራዳ ህንፃዎችና እንዲሁም እየሩሳሌም መታሰቢያ ህንፃ ያለ አንዳች ምክንያት አፈረሱት፡፡ ዶሮ ማነቂያ ቀጣዩ ተረኛ ነው፣ የሃገር ፍቅር ቴያትር ቤትን ዋነኛውን የሃገሪቱን ቅርሰ ለማፍረስ ነው ትልእኮቸው፡፡ ኢትዮጵያን ያለታሪክ ለማስቀረት የተጠነሰሰ የኦህዴድ ብልፅግና ፕሮጀክት ነው፡፡ ቴድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ የሚገኘው አንበሳ መድኃኒት ቤትና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት ‹‹ሴጣን ቤት›› አፈረሱት፣ ብሔራዊ ትያትር አካባቢ መከላከያ ሚኒስትር ጎን ኢትዮጵያ ሆቴል አጠገብ የነበረውን ህንፃ አንበሳ ሻይ ቤት አፈረሱት፡፡ ብዙ ሽህ ሰዎች ተፈናቀሉ፣ የስራ ቦታቸውን ተነጠቁ፣ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩበትን ገቢ ተነጠቁ፡፡ ምንም ዓይነት ካሳና ተቀያሪ ቦታና መኖሪያ አልተሰጣቸውም፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና ማንነት ተኮር፣ ደሃ ተኮር ‹አደህይተህ ግዛ› ህጋዊ ዘረፋ ነው፡፡ ይሄ ካልገባህ ገና ህይወትህን ይነጥቁሃልና ለትግል ተሰናዳ፡፡ መጀመሪያ የሃገር ቅርስ ያጠፋሉ ቀጥሎ ወጣቱን ይጨርሳሉ!!! ኮነሬል አብይ አዲስ አበባ ከተማ ያፈናቀለውን ቦታ አምስት ሽህ ሜትር ካሬ ለእያንዳንዱ ኢንቨስተሮች በጨረታ በመሸጥ ጦርነቱን ለመግፋት ዶልቶል፣ ሃገር ወዳድ ባለሃብት ቦታው ቦታውን ባለመግዛት ተባበር እንላለን፡፡
የስልሣና ሰባዎቹ ወጣት ትውልድ ምንም ያጥፉ ምን፣ ህዝብ ሲጠቃና ሲዋረድ አይወድም ነበር፣ ፋሽስቱ መንግሥቱ ኃይማርያምን ሙሃሂቴን አስኝተውት ነበር፣ የደርግ አባሎቹን ቀኑን በሌት ሌቱን በቀን አድርገንባቸው በፍርሃት እንዲኖሩ የደረግናቸው፣ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እንደከርከሮ እያደኑ መግደል ሲጀምሩ፣ ይሄን ከምናይ ብንሞት መርጠን በጀግንነት ተሠዋን፡፡ ዛሬ የእኛን ትውልድ ጀግንነት አልገዛም ያሉ ነፃነቴንና መብቴን በክንዴ ያለ ትውልድ ተፈጥሮል፡፡ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት የሚፋለም ትውልድ!!! ‹‹በትግል መሞት ህይወት፣ በአመፃ መሞት ህይወት፣ ዳግም ትንሣኤ ልደት!!!›› እያሉ እየዘመሩ መሥዋት ይሆኑ ነበር፣ ሞትን የናቀ ትውልድ ነበሩ!!! ከሞት በኃላ ህይወት አለና፣ በታሪክ ሁሌ ይታወሳሉ!!! የአማን የወጣቶች ድርጅት ከምሽት ሦስትና አራት ሰዓት ላይ የኡኡታና የዕቃ ማንኳኳት ዘመቻ ማዘጋጀት እንዲሁም የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ መጥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሥነ-ህዝብ ለውጥ Demography Change ለማድረግ ሲባል የኦህዴድ ብልፅግና የሚቀጥለው ምርጫ ለመመረጥ የኦሮሞ ተወላጆችን እያሰፈረ፣ የአማራ ተወላጆች፣ የዶርዜ፣ የጉራጌ፣ የትግራይ ተወላጆችን እያፈናቀለና ከአዲስ አበባ እንዲወጡ በማድረግ እንዲሁም ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በመድረግ ታሪክ የማይረሳው አፓርታይዳዊ የኦሮሙማ ሥርዓት ዘርግቶል፡፡
በኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዬች (internally displaced) ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች በአለፉት አመታቶች ተከስተዋል፡፡ በደህንነትና ፀጥታ መታወክ ምክንያት በኦነግ ሸኔ ሽብርተኛ ድርጅት የተነሳ ከወለጋ ከምስራቅ ኦሮሚያ ቀያቸውን ለቀው የተፈናቀሉ ዜጎች ይገኛሉ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በጉሙዝ አማፅያን የተፈናቀሉ፣ በፌዴራል መንግሥትና በህወሓት አማፅያን በተከሰተ ጦርነት ከፍተኛ የማሀህበራዊና የምጣኔ ኃብት ቀውስ በሃገሪቱ ተንሰራፍቶል፡፡ በቅርብ ጊዜያት ከፍተኛ መፈናቀል የተፈጠረው ደግሞ አዲስ ከተማ ለመፍጠር፣ በሸገር ከተማ ምሥረታ ነው፡፡ ሸገር የአዲስ አበባ ሌላዋ መጠሪያ ነበር፡፡ Ethiopians have been internally displaced for a variety of reasons over the last couple of years. The security challenges posed by Shene, a group labeled a terrorist organization in Wolega, Western Oromia, or by Gumuz Militants in the State of Benishangul Gumuz, or during the war between the federal government and the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), have all shown Ethiopians the height of social and economic challenges. The most recent reason for displacement, however, is related to the establishment of a city- Sheger, a name previously used to refer to the capital Addis Ababa. In this article, EBR’s Trualem Asmare tries to depict the plight of citizens who are displaced following the plan to establish the new city………………………..(1)
በ2022 እኤአ ከሸገር ከተማ ምስረታ በፊት 2.75 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሽህ) የአገር ውስጥ ተፈናቃዬች ሪፖርት ተደርጎ ነበር፡፡ ተፈናቃዬቹ በአስራ አንድ ክልላዊ መንግሥቶች ውስጥ 2,158 (በሁለት ሽህ አነድ መቶ ሃመሳ ስምንት) መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው ይገኙ ነበር፡፡ በትግራይ የሚገኙትን ተፈናቃዬች መረጃው አይጨምርም ነበር፡፡ በማርች 31 ቀን 2023እኤአ የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ‹‹የሸገር ከተማ ንዋሪዎች የቤት ፈረሳና አስገድዶ ማፈናቀል ሚሊዮኖችን ቤት አልባ አደረገ፣ ደንቡና ህጉ ግን አይፈቅድም ነበር፡፡›› በህገወጥ መንገድ በሠፈሩ ሰዎችን አስገድዶ ማፈናቀል በስብዓዊ መብቶችን እንደመጋፋት ተደርጎ ይቆጠራልና፡፡ Even before the displacement resulting from the establishment of Sheger City, a total 2.75 million internally displaced people (IDPs) are reported to have lived in 2,158 accessible locations spread across 11 states of Ethiopia in 2022. The figure at the time did not include those in the State of Tigray. “Procedural and legal irregularities in Sheger city house demolitions and forced evictions leave several homeless,” Daniel Bekele, chief commissioner at the Ethiopian Human Rights Commission, said on March 31, 2023. “Forced evictions, even from unlawful occupations, should comply with minimum human rights standards.”
የተባበሩት መንግሥታት የስብዓዊ ጉዳዬች ቢሮ፡- United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (OCHA), የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማርች አንድ ቀን 2024 እኤአ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በ2024 እኤአ በኢትዮጵያ ለ15.5 (አስራአምስት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን ህዝብ ሁለገብ ስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ 3.2 (ሦስት ነጥብ ሁለት)ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መንግሥትና የስብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በጋራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡US$3.2 billion required in 2024 to provide multisectoral humanitarian assistance to 15.5 million Ethiopians – Government of Ethiopia, humanitarian community joint appeal. ከኢትዮጵያ ህዝብ 4.4 (አራት ነጥብ አራት) ሚሊዮን ህዝብ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች በግጭት፣ በጦርነት፣ ጥላቻና የዓየር ለውጥ ቀውስ የተነሳ ሁለገብ ድጋፍ ይሻሉ፡፡ 4.4 million internally displaced people severely impacted by conflict, hostilities and climate shocks require scaled up multi-sectoral assistance………………………(2)
የተፈናቃች ህይወት በአዲስ አበባ ጎዳና
የወይዘሮ አበባ ከበደን (ስሞ ለደህንነቶ የተቀየረ) የአርባ አምስት አመት እድሜ ያላት ስትሆን የአራት ልጆች እናት ናት፡፡ አበባ ከመፈናቀሎ በፊት ከነልጆቾ የምትኖረው በጣፎ ከተማ በቶ ውስጥ ነበር፡፡ አበባ ከሶስት አመት በፊት ባለቤቶን በሞት የተነጠቀች ስትሆን ልጆቾን ሽንኩርትና ድንች መንገድ ላይ በመሸጥ ታስተዳድር ነበር፡፡ አበባ በምታገኘው ገቢ፣ ልጆቾን ትምህርት ቤት ትልክ ነበር፡፡ ቤታቸው የፈረሰው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሲሆን ምንም ነገር ይዘው መውጣት አልቻሉም፣ ቤታቸው ከፈረሰ በኃላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ጎዳና ላይ መተዳደር ጀመሩ፡፡ አበባ ማንም የሚረዳት ዘመድና ወገን ስለሌላት የጎዳና ህይወት መግፋት ግድ ሆነባት፡፡ አበባ በመገኛኛ አካባቢ በመለመን መተዳደር ጀምራለች፣ ጎዳናው ከጣፎና ከሌሎች አካባቢ በተፈናቀሉ ተጥለቅልቆል፡፡ የአዲስ አበባ ሰዎች በደግነት እጃቸውን ይዘረጉልናል፡፡ አበባ ሁሉም ልጆቾ ሴቶቸ በመሆናቸው በሌሊት የመደፈር አደጋ እንዳያጋጥማቸው ፍርሃቶን ለጥናት ቡድኑ ገልፃለች፡፡
የሸገር ከተማ ፕሮጀክት፡- የኮነሬል አብይ የኦሮሙማ የእጅ አዙር አገዛዝ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ተቆርሷ የተሠጠ የሸገር ከተማ 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ወይም 1600 000 000 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን) ካሬ ሜትር ቦታ ህገ-መንግሥቱን በጣሰ መንገድ ተዘርፎል፣ ህዝብ ያላማከረና 600000 (ስድስት መቶ ሽህ) ሰዎችን በግፍ ያፈናቀለ የኦሮሙማ አገዛዝ ያለአንዳች ማስተር ፕላን ጥናት በኦህዴድ ብልጽግና ዘረኛና ተረኛ የኦሮሙማ ሥርዓት የከተማ ህዝብ ንቅለ ተከላ የተከናወነበት ዘመን ነው፡፡ ማንነት ተኮር በአማራነታቸው ምክንያት የተፈላቀሉ ነበሩ፣ ከኦሮሞ ገበሬዎች በማፈናቀሉ የተነሳ ኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ ተቃውሞ ገጥሞቸው ነበር፡፡ ኦሮሞ ያልሆኑ ንዋሪዎችም በተለይ አማራዎች የኦሮሞ አስተዳደር ድብቅ አጀንዳ የአዲስ አበባን ከተማ ወደ ኦሮሚያ ለማካተትና ለመሰልቀጥ የተወጠነ መሆኑን በሸገር ከተማ ምስረታ ማግስት ህገወጥ ተብለው የፈረሱት የአማራ ቤቶች በመሆናቸው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ህዝብን ሳያማክር በኦክቶበር 2022 እኤአ የሸገር ከተማ መሠረተ አዲስ የከተማ ማዕከል ስትሆን የአዲስ አበባን ዙሪያ ገባ ተከትላ የተዋቀረች ከተማ ናት፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ስፍት አላት፡፡ Covering an area of over 1,600 square kilometers, Sheger City encompasses six Oromia towns. የሸገር ከተማ በስድስት ክፍለ ከተሞች የተመሠረተች ስትሆን እነሱም ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ያካትታሉ፡፡ የሸገር ከተማ አዲስ አበባን ዙሪያዎን ከበዋታል፡፡
ሽመልስ አብዲሳ በማህይመነት ‹‹በሸገር ከተማ ሠላሳ ሚሊዮን ህዝብ አሰፍራለሁ›› ብሎል በአለማችን ትላልቅ ከተሞች የህዝብ ብዛት ቶክዬ Tokyo (Population: 37,435,191)፣ዴልሂ Delhi (Population: 29,399,141)፣ሻንጋይ Shanghai (Population: 26,317,104)፣ ሳኦ ፖሎ Sao Paulo (Population: 21,846,507)፣ ሜክሲኮ Mexico City (Population: 21,671,908)፣ ካይሮ Cairo (Population: 20,484,965)፣ ዳካር Dhaka (Population: 20,283,552)፣ ሙምባይ Mumbai (Population: 20,185,064) ከሠላሳ ሰባት እስከ ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ይኖርባቸዋል፡፡
የሸገር ከተማ ምሥረታ የተረጋገጠው ከኦግስት 2022 አኤአ በኃላ የአዲስ አበባ ከተማና በፍንፍኔ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን በተካለለ ጊዜ ነበር፡፡ ወሰኑ ግልጽ ባለመሆኑ ምክንያት ግጭትና አለመረጋጋት አስከትሎ ነበር፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር የግንባታ ወጪና በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ የሸገር ከተማ ለመመሥረት የሚወጣ ሌላ ትሪሊዮን ብር በአስቸኳይ እንዲቆም በማስደረግ ለሚሊዮን ተፈናቃዬች ህይወትን መታደግ፣ በትግራይ በአማራና አፋር ክልሎች የወደሙ መሠረተ-ልማቶች በተለይ የጤና፣ የትምህርት፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ አገልግሎቶች ቅድሚያ እንዲሠጣቸው ማድረግና በህዝቡ ላይ የደረሰውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥታዊ ድጎማዎች ማድረግ፣ ግብርና ታክስ መቀነስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ማፍረስ ማስቆም አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄ ናቸው፡፡
የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መስፋፋት በሁሉም ክልሎች ድንበር በኩል የድንበር ግጪት አስከትሎል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከሱማሌ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ህዝቦች፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዎ ወዘተ ህዝብ ጋር ጦርነት በመጫር ላይ ይገኛል፡ የኦሮሞ ምሁራን ይሄንን የግዛት የመስፋፋት ጥያቄ የአስራስድስተኛውና የአስራሰበተኛው ዘመን ጥያቄ መሆኑን በማጤን ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት አታብዙበት እንላለን፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በሠላምና በህብረት እንዲኖር ማድረግ የስልጣኔ መንገድ በመሆኑ መምከር ይጠበቅባችሆል፡፡
ምንጭ
(1) The Tale of Sheger/New City Displaces Thousands /Hemen Asmare /EBR 11th Year • May 2023 • No. 117
(2) Ethiopia – Situation Report, 1 Mar 2024