የኢትዮጵያ ጀስታፖ ኮሬ ነጌኛ!!! የኦህዴድ ብልፅግና ጀስታፖ!!! ETHIOPIA’S “GESTAPO”

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

Ethiopia’s secret “security committee” accused of murder and abductions/ Ethiopia’s GESTAPO torture extortion and murder.

(1) ኮሬ ነጌኛ (ጀስታፖ) የኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልፅግና ጀስታፖ (ኮሬ ነጌኛ) ናዚ ጀርመኒ በአውሮፓ  ወረው በያዙበት ጊዜ የመሠረቱት የናዚ ጀርመኒ ሚስጢራዊ ፖሊስ፣ በ1933 እኤአ በህርማን ጎሪንግ የተፈጠረ ሚስጢራዊ ድርጅት ነበር፡፡ The Geheime Staatspolizei, abbreviated Gestapo, was the official secret police of Nazi Germany and in German-occupied Europe. The force was created by Hermann Göring in 1933 by combining the various political police agencies of Prussia into one.   በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ ተዋህዶ  ኦርቶዶክስ ቤተ  ክርስቲያን ታሪካዊው ዝቆላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚያገለግሉ አራት ቄሶች ከታገቱ በኃላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል፡፡ በዚህ አረመኔ ሥራ የኦሮሙማው ኮሬ ነጌኛ ሚስጢራዊ ቡድን ስራ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡የኢትዮጵያ ተዋህዶ  ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ከሠላሳ ሁለት እስከ ሠላሳ ስድስት ሚሊዮን የእምነቱ ተከታዬች ያላት ስትሆን በዓለማችን ከራሽያ ቀጥላ ሁለተኛዋ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ናት፣ እሶን ማጥፋት የማይታሰብ ነው፡፡

ፓልኪ ሻርማ የፈርስት ፖስት (Firstpost) ዘጋቢ መሠረት የኢትዮጵያ ጀስታፖ Ethiopia’s GESTAPO ኮሬ ነጌኛ!!! የኦህዴድ ብልፅግና ጀስታፖ!!! የኦሮሙማ ‹‹ኮሬ ነጌኛ›› በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በፀጥታና ደህንነት ኮሚቴ ሽፋን የተቆቆመው የገዳዬች ቡድን ነው፡፡ “The Koree Nageenyaa:- it overreached its purpose by interfering in the justice system with widespread human rights violations. Ethiopia’s secret “security committee” accused of murder and abductions/ Ethiopia’s GESTAPO torture extortion and murder.” በኮነሬል አብይ አህመድ  የተቆቆመ ስውር ቡድን  ህገ-መንግስቱን በመጣስ ሰዎች በመግደል፣ በመሰወርና በማገት በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀሳል፡፡ የዓለም ሠላም ሎሬት በመንግሥት መር የሽብርተኛነት ሥራ ውስጥ ተጠምዶ የሥልጣን መንበሩን ለማስጠበቅ ተቃዋሚዎቹን ያለ ፍርድ በመግደል፣ በማሰርና በቶርቸር፣ በኃይል በመሰወር፣ ሴት በመድፈር፣ በማገት የኢትዮጵያ ህዝብን ቁም ስቅሉን አሳይተውታል፡፡ የኮሬ ነጌኛ መሥራቾቹ  ውስጥ ሽመልስ አብዲሳ፣ ፍቃዱ ተሰማ፣ አወሉ አብዲ፣ አራርሳ መርዳሳ፣ የስውር ቡድኑ አመራሮች በአደባባይ አሰራአምስት የከረዩ አባገዳዎች ገድለዋል፡፡ የአባገዳዎች  ፎቶግራፍ  ከላይ ይስተዋላል፡፡ የኢትዮጵያ ጀስታፖ (ኮሬ ነጌኛ) በኦነግ ሸኔ የዳቦ ስም በመንግስት መዋቅራዊና ሚስጢራዊ ስኮዶች የሚፈፀም የገዳዬች ቡድን መሆኑ ተረጋግጦል፡፡  Ethiopia’s Gestapo-like “security committee”? Is the Amhara region going to face the committee’s wrath as well? Palki Sharma tells you more………………………….…………..(1)

(2) የተባበሩት መንግሥታት (United Nations Human Rights Council)፡- የተባበሩት መንግሥታት በአማራ ክልል ወንጀሎችና ስብዓዊ ቀውስ መጨመር በሰው ዓልባ አውሮፕላን (ድሮውን)ና በነፃ እርምጃ ንፁሃን ዜጎች መጨፍጨፍ በተመለከተ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲቆቆምና በፊት የነበረው ኮሚሽን ደግም እንዲሰራ ወንጀለኞቹ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተወስኖል፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በየሃገሩ ገለልተኛው አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአስቸኳይ እንዲጀምር ድጋፋችሁን ማሰማት ይጠበቅባችኃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በአማራ ክልል እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፍ (ጀኖሳይድ) በድሮውን ጥቃት 70 ንጹሃን ዜጎች በፍኖተሰላም መፈፀሙን፣ በደብረ ብርሃን ከተማ በከባድ መሣሪያ ንፁሃን ዜጎች መገደልና በተሸሸጉበት ስፍራ ሆስፒታል፣ ቤተክርስቲያነ ፣ ትምህርት ቤት ውስጥ በግፍ መገደል፣ ባህር ዳር ከተማን በተወንጫፊ ከባድ መሳሪያ መደብደብ የተነሳ በመቶ የሚቆጠሩ ንፁሃን አማራዎች ተገድለዋል፣በጎንደር የተነሳ ጦርነት ከሃያ ንፁሃን አማራዎች ተገለዋል፣ሁለት መቶ ቆስለዋል፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ንፁሃን ዜጎች መታገትና በኃይል መሠወር በተባበሩት መንግሥታት የአማራ ጀኖሳይድ ሪፖርት  ላይ በሰፊው ተገልፆል፡፡ ሙሉውን ከድረገፁ ያንብቡት፡፡ The international community’s swift and resolute action is crucial to addressing the deteriorating Amhara genocide in Amhara Region of Ethiopia: The atrocities being committed against the Amhara people in the Amhara region of Ethiopia are deeply concerning and require immediate attention. The following incidents provide a glimpse into the severity of the ongoing crisis:…………………………..(2)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሞ ጠባብ ብሔርተኞች ለኦሮሞ ሕዝብ ያላቸው ጥያቄ ምንድ ነው? - በፈቃዱ ኃይሉ

የኮነሬል አብይ አንባገነን መንግስት በዘር ማጥፋት (ጅኖሳይድ)፣ የጦር ወንጀልና የሰው አልባ አይሮፕላን (ድሮውን) ጥቃት በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት (ICC) ለማቅረብ የክስ ዶሴዎቹ በየአለበት እየተጠናቀረ ይገኛል፡፡

(3) የተባበሩት መንግሥታት የስብዓዊ ጉዳዬች ቢሮ፡-  United Nations Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (OCHA), የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማርች አንድ ቀን 2024 እኤአ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ Ethiopia – Situation Report, 1 Mar 2024.  በ2024 እኤአ በኢትዮጵያ ለ15.5 (አስራአምስት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን ህዝብ  ሁለገብ ስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ 3.2 (ሦስት ነጥብ ሁለት)ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መንግሥትና የስብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በጋራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡US$3.2 billion required in 2024 to provide multisectoral humanitarian assistance to 15.5 million Ethiopians – Government of Ethiopia, humanitarian community joint appeal.

ከኢትዮጵያ ህዝብ 4.4 (አራት ነጥብ አራት) ሚሊዮን ህዝብ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች በግጭት፣ በጦርነት፣ ጥላቻና የዓየር ለውጥ ቀውስ የተነሳ ሁለገብ ድጋፍ ይሻሉ፡፡ 4.4 million internally displaced people severely impacted by conflict, hostilities and climate shocks require scaled up multi-sectoral assistance.

የተባበሩት መንግሥታት የስብዓዊ ጉዳዬች ቢሮ(OCHA) አስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ለአስቸኳይ ስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በጅቶል፡፡ በሃገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረትን ለማሻሻል ተጨማሪ ኃብት ማሰባሰብ ይጠይቃል፡፡ $17 million allocated from the OCHA Central Emergency Response Fund to respond to worsening food insecurity; additional funding and resources needed to avert worst impact……………….………(3)

(4) አራት ሽህ ሴቶችን አስገድዶ መድፈር ወንጀል፡- በአማራ ክልል ጦርነት የኮነሬል አብይ መከላከያ ሠራዊት  በአማራ ህዝብ ላይ በፀጥታና ደህንነት ኮሚቴ ሽፋን የተቆቆመው  የኦሮሙማ ‹‹ኮሬ ነጌኛ›› የገዳዬች ቡድን  4000 (አራት ሽህ ሴቶችን) አስገድደው እንደደፈሩ የአማራ ሴቶች ማህበር ፅህፈት ቤት አስታውቆል፡፡ በአማራ ክልል ሪፖርት ያላደረጉ ብዙ ሴቶች እንደሚኖሩ ይታመናል፡፡ በትግራይ ጦርነት የተደፈሩት ብዙ ሽህ ሴቶች እህቶቻችን ፍርድ እንዳላገኙ ይታወቃል፡፡ የኮነሬል አብይ የገማ ሥርዓት ሴቶችን በመድፈር ታሪክ የማይረሳው ወንጀለኛ አንድ ቀን ለፍርድ እንደሚቀርብና የኢትዮጵያ እናቶች እንባ እንደሚታበስ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

(5) በአማራ ክልል ጦርነት 3.6 (ሦስት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ላይ እንደሌሉና በክልሉ 3000 (ሦስት ሽህ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ አስታውቆል፡፡ የመምህራን ደሞዝ እንደማይከፈልና የአማራ ክልል መንግሥታዊ መዋቅር በመፍረሱ የብአዴን/አዴፓ ብልፅግና  ፓርቲ ህልውና አክትሞል፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጦርነት እሳት ለተለበለቡ የአማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች ለፈረሱት ትምህርት ቤቶች ሳይገነቡ፣ የተጎዳው ሥነ-ልቦናቸው ሳይታደስ፣ በወጣት ተማሪዎች ሞራል ላይ የቀለደው አንድ ቀን ለፍርድ ያበቃዋል፡፡  የ2016ዓ/ም ዓመታዊ በጀት ለትምህርት ሚኒስቴር 55.8 (ሃምሳ ስድስት) ቢሊዮን ብር በጀት ያፀደቀ ሲሆን በጦርነቱ የወደሙት ትምህርት ቤቶች እንዳልተገነቡና የመምህራን ደሞዝ እንደማይከፈል ፕሮፌሰሩ ያውቃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በወለጋ በተከታታይ ለሚካሄደው የአማራ ሕዝብ እልቂት ተጠያቂዎች የኢትዮጵያ ፌደራል መንንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው  - አክሎግ ቢራራ (ዶር)

(6) የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት፡- ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት መሪ በኢትዮጵያ አማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ መቶ የጤና ተቆማቶች መሠረተ-ልማቶች ውስጥ ስልሳ አንዱ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ እንዲሁም ሰላሳ ዘጠኙ በከፊል የወደሙ መሆኑንና የጤና ባለሙያዎች ለአደጋ መጋለጣቸውን ሪፖርት አድርገዋል፡፡ “Now to Ethiopia, where WHO is gravely concerned about the worsening health crisis in parts of the county. The north-western region of Amhara has been badly affected by conflict since April 2023. The internet is still cut off in the region, severely impeding communication with health partner and authorities. Restrictions on movement are impeding the provision of humanitarian assistance. Fighting is affecting access to health facilities, either through damage or destruction, roadblocks and other obstacles. According to a multiagency report, 61 health facilities have been damaged and 39 partially damaged as a result of the recent conflict in Amhara.”…………………(4)

(7) አራት መቶ ኃምሳ ቢሊዮን ብር ውድመት፡- በአማራ ክልል በጦርነቱ የደረሰ አጠቃላይ የመሠረተ-ልማት ውድመት ከ450 (አራት መቶ ኃምሳ) ቢሊዮን ብር ውድመት  በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታልና ጤና ተቆማቶች መሳሪያዎች፣ ቴሌኮሙኒኬሽን መስመሮች፣ የመብርትና ውኃ አገልግሎቶች መሣሪያዎች፣ ትልልቅ የጭነት መኪኖች ቃጠሎ፣ የአበባ እርሻዎች ቃጠሎ፣ የተቃጠሉ የእህል ክምሮች፣ የተዘረፉ የእህል መጋዘኞች፣ ፋብሪካዎች፣ የተነዱ የቁም እንሰሳት፣  የተዘረፉ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ወዘተ የተነሳ በመንግሥትና በግል መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተለይተዋል፡፡

(8) ዓመታዊ በጀት ለጦርነት እየዋለ ነው፡-የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የ2016ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 802 ቢሊዩን ብር በጀት ጦርነት ማስኬጃ ሆኖል፣  ይህም በዩኤስ 15 ቢሊዩን ዶላር ይሆናል፡፡ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ56 ብር ሂሳብ ገደማ የተሰላ ነው፡፡ በጥቁር ገበያ አንድ የአሜሪካ ዶላር 116 ብር ደርሶል፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ በአስር ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ገዝተን ፋኖን በጦርነት ገጥመን እናሸንፋለን ብሎ ተመጻድቆል፡፡ ኮነሬሉ ጦርነት በገንዘብ ኃይል የሚያሸንፍ መስሎታል፣ ሆኖም   የምታሸንፈው የህዝብ ድጋፍ ከጎንህ እስካለ ድረስ ነው፡፡ የዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ሁለት ቢሊዮን ዶላር አናበድርም ብለው ደጅ የጠና ኮነሬል አስር ቢሊዮን ዶላር ይመኛል፡፡ ኮነሬል አብይ የ2016ዓ/ም ዓመታዊ በጀት ለክልሎች ከተመደበው በጀት  አማራ ክልል በጀት   45.1  (አርባ አምስት) ቢሊዮን ብር፣   ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግብ  3.0  (ሦስት )  ቢሊዮን ብር በጠቅላላው አርባ ስምንት ቢሊዮን ብር የአማራ ክልልን በጀት አጥፎ ለጦርነቱ መጠቀም ከጀመረ ቆይቶል በቀጣይም የሌሎች ክልሎች በጀት መታጠፉ አይቀሬ ነው፡፡ መሃይሙ ኮነሬል ለሃያ አመት እንዋጋለን ይላል በየትኛው ኢኮኖሚህ፣ በዚች አመት እጅ ትሰጣለህ፣ ስንዴ ለምኖ ሸጦ የጦር መሳሪያ መግዛት አክትሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግንጊልቻ (Gingilchaa)- የጠቅላዩ የፓርላማ ውሎ ትዝብት... በ-ሙሉዓለም ገ/መድኀን 

(9) የዓለም ባንክና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (World Bank/ IMF) የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ድርድር የኢትዮጵያ የብር ኖት የውጭ ምንዛሪ ተመን ማርከስና የውጪ እዳ ጫና በተሳለ ቢላዋ ጫፍ ላይ እንደመሄድ  ነው፡፡

Ethiopia’s Currency Quandary Places IMF Deal on ‘Knife’s Edge’…/  Ethiopia’s Currency Quandary Places IMF Deal on ‘Knife’s Edge’ Government needs IMF funds for debt revamp efforts to progress. Other African nations also grappling with currency devaluation Gift this article. By Matthew Hill and Fasika Tadesse/January 12, 2024

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ በመጎዝ የሃገሪቱን ብሔራዊ የእዳ መሸጋሸግ ለማሳካት፣ የኢትዮጵያ የብር ኖት የውጭ ምንዛሪ ተመን ማርከስ ጥያቄን የመቀበልና ያለመቀበል ጥያቄ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ማስከተሉና የህብረተሰቡን ኑሮ እንደሚያናጋ ይጠበቃል፡፡ International Monetary Fund officials are heading to Ethiopia, where the authorities face a tough decision needed to win a bailout that’s key to restructuring the nation’s debt: whether or not to allow its currency to weaken and risk triggering higher inflation and social instability. An IMF mission to Addis Ababa is expected to take place “in the coming weeks,” the Washington-based lender said in an emailed response to questions. The visit follows meetings in October, when the IMF made “good progress” on how to support the nation’s economic program, it said……………………(5)

የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት 3.5 (ሦስት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ድርድር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ ከዓለም ባንክም ሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ለመበደር አቅዶል፡፡ በብሉምበርግና በሮይተርስ ዜና ተዘግቦል፡፡ Bloomberg.com/https://www.bloomberg.com › articles › 23024-01-12 › et… Jan 11, 2024 — The Ethiopian authorities are in talks with the IMF to borrow about $3.5 billion and a similar amount from the World Bank, Reuters reported last …

ኮነሬል አብይ መንግሥት ይሄን ገንዘብ ካገኘ የጦር መሣሪያ ለመግዣ፣ ድሮውን ለመሸመቻ ስለሚጠቀምበት ኢትዮጵያኖች ብድሩን መቃወም የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡ ለዓለም ባንክና ለዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ሹማምንቶች የኮነሬል አብይ መንግሥት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የሚያካሂደውን ጦርነት ማስቆም፣ ለርሃብተኛው ወገናችን የስብዓዊ እርዳታ ማድረስ፣ የፖለቲካ እስረኞች መፍታት፣ ዴሞክራሲያዊ አሰራር ማዘመንና የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ከገባበት አዘቅት ማውጣትና ዘለቄታዊ ልማት ለማምጣት ዋነኛዎቹ ብድር የመስጠት መመዘኛዎች ማድረግ አለባቸው እንላለን፡፡

ምንጭ

(1) https://www.firstpost.com › Vantage/ Ethiopia’s Gestapo.

(2) Urgent Call to Address Escalating Human Rights Violations and Crisis in Amhara, Ethiopia  (https://documents.un.org/doc/undoc/gen/g24/025/69/pdf/g2402569.pdf?)

(3)Ethiopia – Situation Report, 1 Mar 2024

(4) Virtual press conference on global issues transcript-10 January 2024

(5) Ethiopia’s Currency Quandary Places IMF Deal on ‘Knife’s Edge’…/Bloomberg.com/https://www.bloomberg.com › articles › Jan 11, 2024

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share