February 23, 2024
2 mins read

በዝቋላ ገዳም አራት መነኮሳት መገደላቸውንየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታወቀች

Zukala Monks murdered by Abiy Ahmed
Zukala Monks murdered by Abiy Ahmedበምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ የሚኖሩ አራት የገዳሙ መነኮሳት በታጣቂዎች መግደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታውቃለች።
ቤተክርስቲያኒቱ የህዝብ ግንጙነት መምሪያ ባወጣው መረጃ መሰረት ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ/ም ታጣቂዎቹ አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ወስደዋል። የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት እያደረገ በነበረበት ወቅትም የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም የገዳሙን መጋቢ አባተክለማርያም አስራትን፣ ጨምሮ አራት መነኮሳት መገደላቸውን እና አብረው ከነበሩት ውስጥ አንድ አባት ብቻ በህይወት መትረፋቸው ተገልጿል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ የህዝብ ግንጙነት መምሪያ ባወጣው መረጃ መነኮሳቱ የተገደሉት መንግስት «ኦነግ ሸኔ» እያለ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ነው። በአሁኑ ወቅትም መነኮሳቱ እና የገዳሙ ቅርሶች አደጋ ላይ በመሆናቸው የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ጥበቃ እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያኒቱ ጥሪ አቅርባለች። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ የሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በርካታ መነኮሳት እንዲሁም ቅርሶች የሚገኙበት ጥንታዊያን እና ታሪካዊ ገዳም ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት ዘረፋ፣ ቃጠሎ እና ከባድ ጉዳቶችን እንደደረሰበትም ቤተ ክርስቲያኗ ያወጣችው መግለጫ ያመለክታል።
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

188942
Previous Story

የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ግድያ

Abiy Blood Thirsty man
Next Story

በኦሮሞ እልፍኝ የተደበቁ ሳጥናኤል አብይ እና ጥቂት እፉኞች ፥ የጨነቀለት መከራዉን ሲያሳዩት የነበረውን ኦሮሞ አድነን እያሉ ነው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop