February 23, 2024
23 mins read

በኦሮሞ እልፍኝ የተደበቁ ሳጥናኤል አብይ እና ጥቂት እፉኞች ፥ የጨነቀለት መከራዉን ሲያሳዩት የነበረውን ኦሮሞ አድነን እያሉ ነው

ካሌብ ታደሰ

የካቲት 10, 2016

Abiy Blood Thirsty man

በኦሮሞ እልፍኝ የተደበቁ ሳጥናኤል አብይ እና ጥቂት እፉኞች ፥ የጨነቀለት መከራዉን ሲያሳዩት የነበረውን ኦሮሞ አድነን እያሉ ነው:: ሲጀምር ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ ከህዝብ ጋር ችግር የለብትም ኖሮበትም አያውቅም!!

በአዳማ (ናዝሬት) ጨፌ በተባለው ምክር መሰብሰቢያ አዳራሽ በቅርቡ በነበረው ስብስባ ላይ ሺመልስ አብዲሳ፣ አሁን ያለውን ዘረኛ ስርዓት፣ የኦሮሞ ህዝብ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡ “ኦሮሞ የሆነ ሁሉ ፋኖን መዋጋት አለበት፣ ፋኖ ኦሮሞን ሊያጠፋ ነው ” በሚል፡፡

 

ይህን ያለው ፣ በአዳማ (ናዝሬት) ጨፌ በተባለው ምክር መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው፡፡ በአዳማ (ናዝሬት)  ከ75% በላይ ነዋሪ ኦሮምኛ የማይናገር ነው፡፡ ግን በአዳማ ጨፌው ሲሰበሰብ ሙሉ በሙሉ በኦሮምኛ ብቻ ስለሆነ፣ አብዛኛው የናዝሬት ነዋሪ አይከታተለውም፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከጨፌ አባላት ውስጥም የአዳማ (ናዝሬት) ልጆች የሉበትም፡፡ በአዳማ (ናዝሬት) የተወለዱና ያደጉ፡፡ ይህም ምን ያህል የኦሮሞ ክልል የሚባለው ዘረኛና አፓርታይዳዊ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

ኦሮሞ ባለፉት 30 አመታት፣ በተለይም ደግሞ ላለፉት 6 አመታት ምን ተጠቅሞ ነው:: በእነዚህ ጥቂት አመታት ውስጥ ከብልጽግና ይልቅ ከፍተኛ ውድመትና ጥፋት ደርሷል ስለሆነም አሁን ያለውን ስርዓት ለማስጠበቅ የሚነሳው ? አዎን በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ በኦሮሞ ስም የዘረፉ፣ የተጠቀሙ የተወሰኑ ከኦሮሞ ማህበረሰብ የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ግን ከ98 በመቶ የሚሆነው ኦሮሞ፣ ምን ያገኘው ነገር አለ ?

የኦሮሞ ስቃይ በአብይ አህመድ እና በሺመልስ አብዲሳ፣  የስልጣን ዘመን ኦሮሞ፣ ምን ያገኘው ነገር አለ ? ዛሬ አርብ  የካቲት 15, 2016 ለንባብ የበቃው የሮይተርስ ዘገባ ባደረገው ምርመራ “በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያቀፈ ሚስጥራዊ ወይንም የህቡዕ አደረጃጀት አለው የተባለው ኮሚቴው ስያሜው “ኮሬ ነጌኛ” ወይንም የጸጥታ ኮሚቴ መሆኑን እና አብይ አህመድ ጠ/ሚኒስትር ሁነው በተሾሙ ወራት ውስጥ የተቋቋመ መሆኑን የዜና አውታሩ በሪፖርቱ ጠቁሟል። የተቋቋመበትም ዋነኛ አላማ በክልሉ ከሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ሀይል ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር በተገናኘ በኦሮምያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ  ለመቆጣጠር መሆኑን አመላክቷል። ይህ የህቡዕ አደረጃጀት ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ እና ህገ ወጥ እስራት ትእዛዝ ያስተላልፋል ተፋጻሚነቱን ይከታተላል” ሲል ተናግሯል። ይህ ሚስጥራዊው አካል “ኮሬ ናጌንያ” “Koree Nageenyaa” የሚል መጠሪያ ያለው ሲሆን አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ከያዙ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ስራ መገባቱን አመልክቷል።

የዜና አውታሩ አክሎም ” ኮሬ ናጌንያ በአቢይ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቢሮዎች ውስጥ የሚገናኙ ሲሆን ኮሚቴው የሚመራው በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ መሆኑንም አክለውም የኮሚቴ አባላት በሙሉ ኦሮሞ ናቸው።  በአባልነት የክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ እና የፖለቲካ ባለሥልጣናት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል. ከነሱም ወስጥ የኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ መሪ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በኮሚቴው ውስጥ ተቀምጠዋል፣ የኦሮሚያ የጸጥታ ኃላፊ የሆኑት አራርሳ መርዳሳ እና ሌሎች ግማሽ ደርዘን የሚሆኑ ሌሎች የሀገር ውስጥ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሃላፊዎች በኮሚቴው ውስጥ ተቀምጠዋል ብለዋል ምንጮች።  ይህ ሚስጥራዊው አካል “ኮሬ ናጌንያ” committee is little known beyond a tight official circle” ጥብቅ ከሆነው ኦፊሴላዊ ክበብ በዘለለ ብዙም አይታወቅም።

“ According to a Reuters report “the Koree Nageenyaa – Security Committee in the Oromo language – which began operating in the months after Prime Minister Abiy Ahmed came to power in 2018. The committee’s existence has not been previously reported.” ሮይተርስ የምርመራ ሪፖርቱን ለማጠናከር  “ከ30 በላይ የፌደራል እና የአካባቢ ባለስልጣናትን፣ ዳኞችን፣ ጠበቆችን እና በባለስልጣናት በደል ሰለባዎችን ቃለ መጠይቅ አድርጓል” ብሏል። በተጨማሪም በክልሉ የሚገኘውን “የኮሬ ናጌንያ” ስራዎችን ያውቃሉ የተባሉ ግለሰቦችን አነጋግሯል – አንዳንዶቹ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀዋል። ሚስጥራዊው አካል በክልሉ ውስጥ ግድያዎች እና እስራት ጋር የተያያዘ ነው:: ሮይተርስ በተጨማሪም የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትን ሚልኬሳ ​​ገመቹን ጠቅሶ ስለ ኮሬ ናጌንያ ከመጋቢት 2019 ጀምሮ እንደሚያውቅ ዘግቧል።

የዚህ ቡድን ተግባር የሚፈልጋቸው ሰዎች እያሳደደ መግደል እና ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ  ማሰር መሆኑም ተጠቁሟል. “The people familiar with Koree Nageenyaa’s activities attributed dozens of killings to the committee’s orders and hundreds of arrests. Among the killings, they said, was a massacre of 14 shepherds in Oromiya in 2021 that the government has previously blamed on OLA fighters.”

በኮሚቴው በተላለፈ ትእዛዝ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች፣ “የጸጥታ ስጋቶች” ናቸው በሚል የተፈጸሙ ጅምላ እስሮች በዜና አውታሩ ሪፖርት ተካተዋል። በ2014 ዓ.ም በከረዩ አባገዳዎች አባላት ግድያ ላይ በሰበሰባቸው እና ባገናዘባቸው ማስረጃዎች መሰረት 14 የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት በመንግሥት የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በግዳጅ ወደ ጫካ ቦታ ተወስደውና የአካባቢ አስተዳደር ሰዎች ባሉበት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በጥይት ተመተው የተገድለዋል ብሏል።  እስቲ ጉጂ ያላችሁ ተናገሩ ? ወለጋ ያላችሁ ኦሮሞዎች ተናገሩ፣ ሰሜን ሸዋ ያላችሁ ተናገሩ ? እኔ ባለኝ መረጃ ፣  ኦሮሞ ነን የሚሉ ኦነጋዊ ገዢዎች ስልጣን እንደያዙበት ዘመን፣ ኦሮሞ በታሪኩ ተሰቃይቶ አያውቅም፡፡ በ 2014 th 2015 አመተ ምህረት በምስራቅ ወለጋ የተለያዩ ወረዳዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በመከላከያ የተገደሉ የአማራ ተወላጆች በመቶዎች የሚቆጠሩ ናቸው:: በእስር ላይ የሚገኙትም ተገርፈዋል፣ እንዲሰቃዩ ተደርገዋል ያለው ሮይተርስ ጣልቃ ለመግባት እና ለመገዳደር የሞከሩ ዳኞች እና ጠበቆች ማስፈራራት ደርሶባቸዋል ሲል ገልጿል።

ብዙ ኦሮሞዎች አሁን የፋኖን ዓላማ እየተረዱ የመጡ ይመስላል፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ እነ ብርሃኑ ጁላ የላኳቸው የኦሮሞ ተዋጊዎች አልቀዋል፡፡ ሞተዋል፡፡ ቁስለኞች ሆነዋል፡፡ ይህ በኦሮሞ እናቶችና አባቶች ዘንድ ፣”ለምንድን ነው ልጆቻችን የሞቱት ?” የሚል ጥያቄዎች እየተነሱ፡፡ ይህ አሁን ያለው አገዛዝ ልጆቻችን አታሎ፣ አፍሶ አስፈጃቸው እያሉ ነው፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩም ተማርከው በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል፡፡ ለህዝቡ እየተናገሩ ነው፡፡ ያዩትን፣ የሆነውን ሁሉ፡፡ አገዛዙ የርሱ ጭፍሮችን፣ ይዞ ንጹሃንን በማንነታቸው ፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ ሲጨፈጭፍ፣ ፋኖዎች ተመሳሳይ የበቀል እርምጃዎች በመውሰድ ፣ ኦሮሞን በኦሮሞነቱ አላጠቁም፡፡ ይሄንን ደግሞ በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ያሉ ኦሮሞዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ፋኖዎች ሺመልስ አብዲሳ እንዳለው ቢሆኑ ኖሮ፣ በፍቼ፣ በወለንጭቲ፣ በገብረ ጉራቻ፣ በመኪጡሪ፣ በኢጄሬ ሰሜን ሸዋና በኢጀሬ ምስራቅ ሸዋ፣ በሞጆ፣ በከሚሴ፣ በሸኖ፣ በመንዲዳ፣ በመተሃራ ወዘተ ባሉ አካባቢዎች እልቂት ይፈጠር ነበር፡፡ ፋኖ ሃላፊነት ሚሰማው፣ በዘር ጥላቻ ላይ ያልተመሰረተ እንደሆነ ብዙ ኦሮሞዎች እያወቁ ነው፡፡

ፋኖ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ማንም ኢትዮጵያዊ ባህሉን፣ ቋንቋዎች፣ ቅርሱን ጠብቆ፣ በቋንቋዉ መንግስታዊ አገልግሎት እያገኘ፣ በወደደው ቦታ መኖር የሚችልንበት ስርዓት እንዲኖር ነው የሚታግለው፡፡  ሺመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አበቤ፣ አብይ አህመድ መቀመጫቸው አዲስ አበባ ነው፡፡ የኦሮሞ ክልል ጨፌ ደግሞ ናዝሬት ነው፡፡ ፋኖዎች የብልጽግና ዘረኛውን አገዛዝ ለመገርሰስ፣ ወታደራዊ ዘመቻዎች ባሌ ዲንሾ፣ ወይንም ምእራብ ወለጋ ጉሊሶ ወይም አርሲ ኮፈሌ አይደለም የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከ90% በላይ ኦሮሞ ባለበት አካባቢ፡፡ ሺመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አበቤ፣ አብይ አህመድ መቀመጫቸው አዲስ አበባ ነው፡፡ አዲስ አበባንና አዲስ አበባን አካባቢ፣ እነ ናዝሬትን ከተቆጣጠሩ፣ የኦሮሞ ብልጽግና አገዛዝ ሙሉ ለሙሉ ያከትምለታል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ደግሞ ፣ በአዲስ አበባ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ፣ በናዝሬት፣ በደብረ ዘይት፣ በአጠቃላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚኖረው ማህበረሰብ አብዛኛው ኦሮሞ ያልሆነ፣ ፋኖን የሚደገፍ ነው፡፡ ያሉት ኦሮሞዎች ቢሆኑ፣ ሚኒሊካዊ ኦሮሞዎች እንጂ ጽንፈኞች አይደሉም፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ጠብቁን ብለው ቢጮሁ እነ ሺመልስ አብዲሳ፣ የሚሰማቸው ማንም የለም፡፡

አብይ አህመድ ወጥቶ ያወራል፡፡ ሺመልስ አብዲሳ ወጥቶ ይደነፋል፡፡ እነዚህ ሰዎች የስልጣን እድምያቸው ማለቂያ ላይ ነው፡፡ ኃይላቸው እየተሸመደመደ፣ ጦራቸው እየተሸነፈና እየተፍረከረከ ነው፡፡ ያላቸውን ሁሉ አሰማሩ፡፡ አልቻሉም፡፡ ፋኖን በሶስት ሳምንት እንደመስሳለን አሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው እየተደመሰሱ ነው፡፡ ፋኖ ክብዙ አደረጀጀቶች፣ ወደ ሻለቃዎች፣ ከሻለቃዎች ወደ ብርጌዶች፣ ከብርጌዶች ወደ ክፍለ ሮችር፣ ከክፍ፤እ ጦሮችን ወደ እዞች እየተሸጋገረ ነው፡፡ ከኢመደበኛ አደረጃጀት ወደ መደበኛ አደረጃጀት እየመጣ ነው፡፡ መከላከያ የሚባለው ቢፈርስ፣ ፋኖ የአገር መከላከያ ሆኖ የመቀጠል አቅም እንዲኖረው እየሰራ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ሽመልስ አብዲሳ  ፖለቲካ ቁማር እንደሆነ በግልፅ ተነግሮናል:: ካሁን ቀደም ከኦሮሞ አንፃር ቁማሩ ሁለት ጉዳዮችን ያካትታል:: አንደኛዉ ውስጣዊ አንድነቱን መናድ ላይ አተኩሯል::  በኦሮሞ ህዝብ መካከል የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ (ባሌ፣ ወለጋ፣ አርሲ፣ ቦረና፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ሀረርጌ፣ ጅማ ወዘተ) በሀይማኖትና በጎሳ (ክርስቲያኖች፣ ሙስሊሞች፣ ዋቄፋና ወዘተ) እና በሶሺዮ ኢኮኖሚ ተግባራቶቻቸው ላይ ሳይቀር መከፋፈል መፍጠር ወይም ማበረታታት ተከፋፍሎ እንዲያንስ ታስቦ ነጣጥሎ ለምግዛት ይሰራ ነበር አሁን የጭንቅ ቀን  “ኦሮሞ ተንሰ::”የኦሮሞ ሕዝብና መንግሥት የመጀመሪያውም ኾነ የመጨረሻው ተልዕኮው ይህን መንግሥታዊ ሥርዓት መጠበቅ ነው”

የቅርብ ጊዜውን ብልጽግና ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በመስኪድ ፈረሳ ምክንያት የቱለማ ኦሮሞን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ለማጋጨት የተሰራዉ ተንኮል ይታወሳል:: በመዋቅር ስም በደቡብ ኦሮሚያ የተፈጠረዉ ውዥንብርም ወንድማማቾችን ነጣጥሎ ለማዳካም ከተሸረበዉ ሴራ ይመነጫል:: እንዲህ ዓይነት ተንኮል በዞን… በወረዳ… በቀበሌና በጎጥ ደረጃም ተተግብሯል:: ለማንኛዉም ሴራዉ በተደጋጋሚ ተሞክሮ እንደከሸፈ ቁማርተኛዉም ያዉቃል! ደስ የሚልው ህዝቡ ከሴረኛዉ ቀድሟል!

ኦሮሞን በወንድሞቹ ዘንድ ለማስጠላት የተወጠነዉ ሌላኛው ቁማር አሁን በመጨረሻ ሰኣት የጭንቀት ሰኣት የመዘዟት:: በአንድ በኩል ከሌሎች ኢትዮጲያዊ ወገኖቹ ጋር በመከራ እሳት እየተቃጠለ ያለዉን ንፁህ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚ ለማስመሰል የሀሰት ሪፖርት ይቀርባል:: የፎቶና የቪድዮ ድራማ ይሰራል:: በሌላ በኩል ደግሞ ልክ በዘር ፖለቲካ ካጠመቃቸው አባታቸው ወያኔ የውድቀት ፖለቲካ መማር ያልቻሉ ድንዙዛን ያንኑ መልሰው አሳፋሪ ተግባራት ተፈፅሞ በኦሮሞነት ካባ ይፎከራል ያደንቁሩናል::

ሀይማኖትና ብሔር በአደባባይ ይዘለፋል:: ያለሀፍረት “ፖለቲካ በማታለል የታጀበ ቁማር ነዉ” ይባላል:: ቁማሩን የሚጫወቱትም ለኦሮሞ ተብሎ እንደሆነ ይመሰላል:: ጫወታዉን ለማሳመር በቁማርተኛዉ ስብዕና ፈፅሞ የሌለዉ ኦሮሙማ በየመድረኩ ይደጋገማል::

በዘመድ አዝማድ ተደራጅቶ ሀገር ይጋጥና በተጎጂዉ ህዝብ ስም ለመሸፈን ይሞከራል:: በህዝቡ ዘላቂ ኪሳራ ሴረኛና ዘራፊ ጊዜያዊ ርካሽ ጥቅሙን ያካብታል:: ህዝቡ ግን በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን በረሃብ ሲሞት ሁሉም አይቷል:: የሌሎችን እርዳታ እንኳን እንዳያገኝ ለገፅታ ጥራት ተብሎ መከራዉ ይደበቃል:: በአጋጣሚ የህዝቡ መከራ ከተሰማ መልሶ ለመሸፈን ዶክመንተሪ ይሰራል:: አሁን በኦሮሚያ ስለህዝቡ ሞትና መፈናቀል መረጃ ማግኘት ከሰማይ ይርቃል! የክልሉ ህዝብ በኢህእዴግ ዘመን የነበረዉን ነፃነትን እንኳን አጥቷል:: በሌቦች ዉሳኔ ምርቱን ከገበያ ዋጋ በታች ለቁመርተኛዉ ደላሎች ለመሸጥ ይገደዳል:: ማህበራዊ ግልጋሎት ከናካቴዉ ተረስቷል::  በተለያዬ ቦታ ሰዉ በዘፈቀደ ይገደላል::

አብይ አህመድ ሰልጣን እንደያዜ ስለማዐከላዊው የስቃይ ምርመራ ሲደስኩር አሁን እንደ  እንጉዳይ በየቦታው በየባለስልታኖች ቤት ሳይቀር ለመስማት እንኳን የሚቀፍ ግፍ ፣ለህዝብ የቆሙ ንፁሃንን ከልጆቻቸው ነጥሎ፣ በቶርቼር (torure) ገላቸውን መበጣጥስ፣  ሰቃዩና ጥፍር ነቀላውን በማሳለጥ እንደትላንቱ ዜጎችን በምርመራ ስም ማኮላሸት ከአባትችሁ ወያኔ በከፋ መልኩ ቀጥላጭችሁበታል! በናንተ ሌብነት ምክንያት በታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥላችሁ ዉሃ ሲጠይቁት ወተት የሚሰጥ የዋው ህዝብ ገፊና አፈናቃይ እንዲመስል ተደርጏል:: ከነባራዊዉ ትርክት አንፃር ይህ እዉነት ለማመን ሊቸግርም ይችላል:: ግና መራራ ሀቁን መግለፅ አሁን ግድ ይላል:: የቁማርተኛ ሌባ ወንጀል ፈፅሞ ኦሮሞን አይመለከትም:: በመሰረቱ ሌባ ሆድ እንጂ ብሔር .. ሀይማኖት ወይም ሰፈር የለዉም:: እዉነቱን ለምናገር ግን የኦሮሞ ህዝብ የአማራና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን የወንድሞቹ ደስታና ሀዘን ተጋሪ እንጂ ለቁማርተኛ ሌቦች ወንጀል አባሪ አይደለም::  ቁማርተኛ ሌቦች በህዝብ ኪሳራ ለመጠቀም ኦሮሞን ልዩ ተጠቃሚ ለማስመሰል ብዙ ደክሟል:: በተጨባጭ ግን ምስኪኑ የኦሮሞ ህዝብ የቁማሩ ልዩ ሰለባ ሆኖ ይገኛል:: ከሁሉም ለከፋ መካራ መጋለጡ አንሶት በወንድሞቹ ዘንድ ባልተገባ መንገድ ይታያል:: እዛው  እራሳች ሁን ቻሉ የጨነቀለት አለ ስፋኙ እውነት ነው የጨነቀለት ስት ሰርቅ ስትገድለው ስታኮላሸው ኑሮን ምድራዊ ሲኦል ስታደርግበት ት ዝ ያላለህ ህዝብ አሁን የጨነቀለት ፈልከው ብዙ አይደንቅም የዘረኞች የዘራፊዎች የጨቋኞች በመውደቂያቸው ዋዜማ የሚያሰሙት ጣር ስለሁነ የኦሮሞ ህዝብም እዛው እራሳችሁን ቻሉ በሎ በስብሰባችሁ ላይ ነግሮዋችዋል! ….ይሰማል በኦሮሞ እልፍኝ የተደበቃችሁ ሳጥናኤል አብይ እና ጥቂት እፉኞች እዛው እራሳችሁን ቻሉ!! ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ ከህዝብ ጋር ችግር የለብትም ኖሮበትም አያውቅም!!

*****የጨነቀለት አለ ዘፋኙ ገና ብዙ እናያለን*****

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop