ብፁዕ አባታችን በሰላም ደርሰዋል ..

ዜና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ነው ዮርክ አየር ማረፊያ ደርሰዋል ኤርፖርት ሲደርሱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ካህናት መዘምራን እና ምዕመናን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኒውዮርክ ጆን ኤፍ ኬኔዲ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ከደረሰባቸው መንገላታት የተነሳ ድካም የሚታይባቸው ሲሆን እንደሚታወቀው ሶስት ቀን በኤርፖርት እና በአውሮፕላን ውስጥ እንዲያሳልፉ ተገደዋል

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ወጣት ቅድምያ መከላከያን ተቀላቀል!! = ቹቹ አለባቸው

2 Comments

  1. አቶ ዳንኤል ክብረት እሳቸውስ በሰላም ደርሰው አገር ወዳድና ምእመኑ በዚህ መልክ አክብሮ ተቀብሏቸዋል አንተ ግን ኦነግና ኦሮሞ ህወአትና ትግሬ የአማራውን እንኳ የበደልከውን በደል አምላክ ይመልከተው፡፡ አላጣህ መጽሀፍ እንገዛሃለን ክብርም ኦርቶዶክስ አካባቢ አልጎደለብህ የጻፍከውን መጽሃፍ የደሰኮርከውን ዲስኩር ተሳስቻለሁ ብለህ የእስላሞች ስብሰባ ላይ ብትናገርም በንቀት ሲያዩህ ነበር፡፡ ጂማ በተደረገው ስብሰባ ይሰቀልልን ሲሉህ ነበር፡፡ ተስፋ በመቁረጥ ይመስላል ሰው በማሳሳት በመሳደብ ላይ እንድትበረታ አደረግህ እንጅ ወደ ኋላ አልሳበህም በእውነት ላንተ አዘንኩ ሊደርስብህ የሚችለውን ሳስብ ይዘገንነኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን በትነህ የሚከፍልህስ ዋጋ ምንድነው?

  2. ዜግነታቸውን ለእንጀራ ሲል የቀየሩ መነኩሴ፣ ነፍሰ ገዳይ ገዥዎችን አምነው አምስት ዓመት ያገለገሉ ጳጳስ፣ በመጨረሻም በዋሻና በገዳም አንድም በፆሎት ሁለትም በማጥናናት የዘር ፍጅት የሚፈጠምበትን አማራ ማገልገል ሲገባቸው ኒዮርክ ለሚኖሩ ጳጳስ ይህ ሁሉ ማሽቃበጥ ለስጋ ነው ለነፍስ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share