
ግድቡ በቀደሙት ነገስታት ሂሊና ተጸንሶ በመለስ ዜናዊ ተወልዷል። ከዚያን ዕለት ጀምሮ ከጉሯሯችን ቀንሰን ያቆምነው የዚህ ትውልድ ብቸኛ የአንድነት ትውክልት ነው – GERD
ሕዳሴ ግድብ ሲነሳ ህሊናዬ ላይ አብሮ የተቀረጸው ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የሚለው ድንቅ ስም ነው – መሃንዲሱ።
በሴራ በተተበተበች ሃገር ደጉ ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ ሙቶ መገኘቱን ሰማን እንዴትና ማን እንደገደለው የነገረን የለም፤ እንባችንን አፍሰን ቁጭ አልን እንጂ፤ ልብ ይሰብራል።
ሕዳሴ የፊታችን ጳጉሜ 4 ይመረቃል ተብለናል፤ ለዚህ መብቃት ታላቅ ስኬት ነው።