ይድረስ በብዙ መከራ ውስጥ ላለሽው እህት ዓለሜ – ምናባዊ ደብዳቤ

ይድረስ በብዙ መከራ ውስጥ ላለሽው እህት ዓለሜ

ይድረስ በብዙ መከራ ውስጥ ላለሽው እህት ዓለሜ:: ቅርብ ጊዜ ጋሽዬ የላከለኝን በሃዘን ተኮራምተሽ የተንሳሽውን ፎቶሽን አጄ ላይ አድርጌ እያየሁት “…ፊትሽን አየሁት ተመለከትኩት ገጽታሽንም። ትኩር ብዬ ተመለከትኩት ፊትሽ ላይ ያለውን የሚነበበውን? እልህ፣ ቁጭት፣ ንዴት፣ ተስፋ ማጣት መሄጃ መድረሻ ማጣት። እንባ የሚያቃጥል እንባ። እርግማን።

እንዲያው ምን ብዬ ነው የሚጀመረው? ከየት ብነሳ ይሆን የውስጤ፣ የነፍስያዬን እና የመንፈሴ ጣር የሚሰማው? የነገር ሁሉ ውል በተንኮለኛ ሸማኔ እንደ ተቋጠረ ቁጢት አልፈታ ያለው ትውልድ እንዴትስ፣ ከወዴትስ ቢጀምር ነው የሀሳቡ መልክ የሚያዘው? እንጃ…….

“እየራበኝ እና እየሞርሞርኝ

ከጠገበው ጋራ ልሞት ነው መሰለኝ ! “

1928 ማይጨው ላይ ወራሪውን ጣሊያን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣው የነበረው የኢትዮጲያ ሰራዊት 3 ማርትሬዛ(ጠገራ) ይከፈለው ኖሮ ርሀብ እና ችግሩ ሲጠናበት “እየራብኝ እና እየሞረሞረኝ ከጠገበው ጋራ ልሞት ነው መሰለኝ” ሲል ተቀኘ:: አንዳንዶች በዚህ ቅኔ የጠገበው የተባለው ጣሊያን ነው ይላሉ:: አያይ እንደዛ አደለም ጥጋበኛ የተባሉት ከንጉሱ እስከ አደግዳጊው እንዲሁም ጮማ እየቆረጠ ግፋ በለው ለሚለው ከራስ እስከ ባራምባራስ ያለው ለስልጣን እና ለንጉሱ የቀረበውን ነው ይላሉ:: ዛሬ ብሔራዊ አደጋችን ሊያጠፋን ያቆበቆበው አደጋ አድርባይነት ነው::

የህዝብ መራብ ብዙ ጥጋቦችን…ብዙ አድርባይነትን አሳይቶናል:: ለህዝብ እርዳርታ ማቅረብ የሰበዓዊነት ልክ ነው:: ከዛም ሲያልፍ እንደ ህዝብ እና እንደ ሀገር ግዴታ ነው ( እውነት ነው ከኢትዮጲያ ህዝብ ሱዳን የበለጠበት ማህበረሰብ ቢሆንም ጣት ገማ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም !) ከህዝብ ርሀብ በላይ ለእርዳታ እጃቸውን የዘረጉት አባገዳዎች አድርባይነት ሌላ ሀገራዊ ረህብ ነው::ምን ያህል ሀገሪቷ ሰው እንደተራበች ግልፅ ማሳያ ነው::

ትናንት በጉራፈርዳ…በሆረጉድሩ…በመተከል…በሻሸመኔ…በአርሲ…በጌዲዮ…በኮንሶ ህዝብ እንደ በግ ሲታረድ እና መከራን ሲቀበል እኒህ አባገዳ እና ሀደ ሲቂዎች የት ነበሩ ? በቃ ሀገር ምትወከለው በነዚህ ሽማግሌዎች ነው ? በባለፈው The Economist ጋዜጣ “የኢትዮጲያ መንግስት ርሀብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት ነው ” የሚል ዘገባ አስነብቧል:: በዚህ ረገድ መንግስት እና ህዝብ እርዳታን እንደ ፖለቲካ መዘወሪያ ላለመጠቀሙ ምን ማስረጃ ይኖር ይሆን ? እንደ ኢትዮጵያዊ ከጠገበው ጋር ከመሞት ከራበው ጋር ተርቦ ማለፍ የተቀደሰ ነው::

እህት ዓለሜ በምናቤ ብዙ አውጣለው አወርዳልው በውስጤ ያልው ብሶት ብዙ ቢሆንም….ብቻ

ግን…….ብቻ ግን “ይመስገን” የሚል በእምነት የጠነከረውን ምላሻችሁን እያሰብሁ ነው ‘የሰማይና የምድሩን ያህል፣ የመከራውንና የመዘንጋቱን ያህል፣ የመገፋትና የመፈተንን ያህል ‘ይህ’ ተብሎ በማይሰፈር የምደር ሲኦል ውስጥ ያላችሁ ወገኖቼ እንዴት ናችሁ? የምለው። እንዴት ናችሁ?…. ደህና ናችሁ ማለት ምን ደህነነት አለና …..

አበወይ እንዴት ነው? የጥይት አረር የሚያሳድደው ወንድም ጋሼስ እንዴት ሁኖ ይሆን? እቴወይስ የሀዘን እና የርሃብ ቸነፈሩን እንዴት ችላው ይሆን? እህታለምስ እንዴት ነሽ? ጥጋበኛው የመንግስት ዘረኛ ወታደር እቀየዋ: መንደሯ መጥቶ ልጆቿን አሳጣት… ከቶ አዘኑን ችላው ይሆን? እንደው ለማናቸው አልቅሳ ይሆን ሀዘኗን የምትወጣው? አይወይስ እንዴት ነው? እያልሁ ያው የህያው ሙት ሁኛለሁ።

ጦርነቱ ከቀጠፈው ሕይወት፣ ካጎደለው አካል፣ ካቆሰለው ሥነ ልቦና በተጨማሪ መሠረተ ልማት በዓመታት ወደኋላ መልሷል። ከዚህም ባሻገር ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ባንክ ከተቋረጡ የትየሌሌ ነው……የቤተሰብ፣ የወዳጅ ዘመድ፣ የጓደኛ ድምጽ መስማት ብርቅ ከሆነ ሰነባበተ። ስልክ ብድግ አድርጎ ወደሚወዱት ሰው መደወል ሩቅ ሆነ።

ባለፈው “እግዜርን ተስፋ አድርጌ፣ በበጋ በፀሐይ ተጠብሼ ከሚተኮስብን የጥይት አረረ እግዚአብሄር ከልሎን ባርስም በዘሩ ወቅት በማሳው ትራክተር ሳይሆን ታንክ ተመናሸበት። አሁን በጤፍ ፋንታ አረም አብቦበታል ማሳው” ብሎኝ ነበር ጋሻዬ። እኔም ባለፈው የደውልሁ ጊዜ “በዘረኝነትና በጥላቻ ሀሊናቸው የታወረው ከላይ ከሀገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀምሮ የጦር ጀነራሎች እስከ በታች ሞኮንኖች በዘረኝነት

በሽታ ሀሊናቸው የታወሩ በሚመሩት የዘር ማጥፋት ጦርነት እየፈጁን ነው። …አብዛኛዎቹ ሟቾች የሃይማኖት አባቶችና መነኮሳት እንዲሁም ህፃናትና ወጣቶች መሆናቸውም ተገልጿል። ዐማሮቹን መግደል ብቻ ሳይሆን እህሉን በእሳት ቤታቸውንም ጭምር ዐመድ በማድረግ እያጸዷቸው ነው። አሁን ደግሞ ርሃብ አንጠራውዞ እየፈጀን ነው። ‘ምነው አንድያውን በመድፉ ባለቅን ይሻል ነበር’ የሚያሰኝ ሞት የማማረጥ ጣጣ ወድቆብናል ወንድምዓለም” ያለኝ እያሰብሁ እስካሁን ውስጤ ይታወካል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ታንኩ ሁላ መሬቱን ሲመነሰሽበት ከረመ። ከብቱም ሀይ ባይ ባጣው ጥጋበኛው ዘረኛ መንግስት በወታደሮቹ ከየአቅጣጫው በሚተኮስ ጥይት አለቀ። አሁን ደግሞ የተረፉትን እንኳን ሽጠን ነፍሳችንን እንዳናቆይ ድርቁ አድቋቸዋል። ደግሞስ “ነገ የተሻለ ቀን ቢወጣ አንድያችንን ተነቅለንን እንቅር? እንደው ምን ቢቸግር ከበረቱ ጥጃ፣ ከጎታው ዘር እንዳይኖር ይደረጋልን?” አለኝ። “የልጆቹን ወዳጅ ጥጆቹን ሳይነካ እምነቱን ጠብቆ ነው የሞተው ለካ” የተባለው የማይሻር ምሃላውን ለመጠበቅ ርሃብን ተጨባበጠው።

አረመኔው የአብይ አገዛዝዝ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የማይፈፅመው ጭካኔ የለም። አርሶአደሩ አመት ሙሉ ከሚተኮስበት የጥይት አረረ እግዚአብሄር ከልሎት አርሶ አጭዶ የሰበሰበውን የለፋበትን አዝመራ እንዲህ እያነደዱ ህፃናት አየደፈሩ በጭካኔ እየረሸኑ ነው።

አብይ አህመድ እና ሰራዊታቸው በዘረኝነትና በአማራ በጥላቻ ሀሊናቸው የታመሙ በአማራው ላይ አረመኔያዊ እና ርህራሄ የለሽ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ይህ ዘመቻ በሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በጄት ጥቃቶች፣ በከባድ የጦር መሳሪያዎች እና ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎችን ጨምሮ ወሳኝ የሆኑ መሠረተ
ልማቶችን ሆን ብሎ እና በዘዴ በማውደም እየቀጠለ ነው።

የአብይ አህመድ አላማ የአማራን ህዝብ ማፈናቀል ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ግዛቶቻቸውን በመንጠቅ ወደ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲዋሃዱ በማድረግ በተጨማሪ ከኦሮሚያ ክልል እንኳን በብሄረሰብ ማጽዳት ነው። ይህ አላማ የአማራን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ማሸማቀቅ እና በስልጣኑ ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዳይፈጥር ማድረግን ጨምሮ ምንም አይነት የቱንም ያህል ቢያስቸግራቸውም – በመሰረቱ ይህ ቅድመ መከላከል አድማ ነበር። ግን ነግሮች እንዳሰቡት አልሆነላቸውም ይህ ምስኪን የዋህ አራሽ ቀዳሽ ተኳሽ የሆነው አማራ አምላኩ ከሱ ጋር ነው::

…ሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዐማሮች በመደበኛው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ሠራዊት በእሳት ጭምር እየተጎበኙ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ከብቱንም ገድለው፣ እሱንም ገድለው ሲያበቁ እህሉን ደግሞ የሚያቃጥሉት ለምን ይሆን። ገበሬው እኮ ይሄን እህል ብቻውን አይበላውም። ለከተማም ለገጠርም ነዋሪዎች የሚሆን ቀለብ እኮ ነው።

እህት ዓለሜ ምንድን ነው የምታወራው እንደማትይኝ እርግጠኛ ነኝ የዚህ ሁሉ መከራ መነሻው ከላይ ለመጣፍ እንደሞከርኩት የዚ በዘረኝ ነት ያበደው ለአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ የሆነው የኦሮሙማ አረመኔነት ግልፅ እውነታ። እዚህ ላይ አንድ የአማራ ሰው ተገልብጦ ከተሰቀለ በሁዋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ።ይህንን በመንግስት የሚደገፈው የአማራ የዘር ማጥፋት የ16ኛው ክፍለ ዘመን ዳግመኛ ተሃድሶ እንድንላመድ ይፈልጋሉ።

እህት ዓለሜ ያቺን የ6 ዐመት ጨቅላ ህጻን አንሻ ሰይድ ወለጋ “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም አትግደሉኝ” ያልችውን ታስታውሻታለሽ??…

እንዲያውም ት ዝ አለኝ በተረሽኑት መካከል በህይውት ተርፋ የዝችን ጨቅላ ህጻን ስቃይ የሰማች ያለችውን አስታውስኩኝ ስሚኝማ እህት ዓለሜ

“ራሴን በረፈረፈው ሬሳ ውስጥ አገኘሁት። ካንገቴ ቀና ስል አንዲት ህፃን (በግምት 6 አመት) በ6 ታጣቂዎች ተከባለች እኔ እእዛው አጠገባቸው ብሆንም ከተረፈረፈው

ሬሳ አንዱ ስለቆጠሩኝ አላስተዋሉኝም። ህፃኗን በአማርኛ ያናግሯቴል ፤ከዛ ሁሉም ባንዴ ድምጻቸው የገደል ማሚቱ እስኪያስተጋባ ይስቃሉ ልመናዋ ላይ ተሳለቁባት። በመጨረሻም ህፃኗ ጮክብላ ይህን ስትል ሰማኋት…..”…..”አትግደሉኝ ፣ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ብላ ስትለምን የነበረች ጨቅላ ታዳጊ

ልመናዋ ላይ ተሳለቁባት ቀጥሎ የሰማሁት ድምጽ የጥይት ሩምታ ነበር ለማየት በሚያሣሣ ገላዋ ላይ እሽቅድምድም በሚመስል መልኩ ሁሉም የጥይት አረር አዘነቡባት ሞታ የሚረኩ አይመስልም ነበር። “ነብሴን ለማትረፍ ከነ ሲቃየ ዝም አልኩኝ ከሁሉም ነብሴ ትበልጥብኝ ነበር። ማክሰኞ ህፃኗ የሞተችበት ቦታ ተሰብስበን ሄደን ነበር፤ የለችም ካሳደገኝ አጎቴ ሞት በላይ እሰካሁን የምትጠዘጥዘኝ ህፃን!!”

እህት ዓለሜ ዛሬ የአማራን ትግል ሊያስቆሙት አይደለም ልገዳድሩት አልቻሉም…. “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም “ ያለችው ህፃን ልጅ ግፍ ፣ በአማራነቷ ተመረጣ አማራነቷን እየረገመች የተረሸነችው አይሻ ሙሃመድን የመጨረሻ የጣረሞት ኑዛዜ ፣…..

“ፈረሰኛው ያድነናል ፣ ዝም አይልም “ ያለችው ህፃን እምባ ፣ የሽመልስ አብዲሳ “ሰብረናቸዋል “ ድንፋታ ፣ የሸገሩ ከንቲባ “ህጋዊ ደሃ አድርገናቸዋል “ እብሪት፣ የአዳነች አበቤ “አዲስ አበባ የምትገቡት በኛ ፈቃድ ነው “ ንቀት እና የአብይ አህመድ ክህደት እንደ ነዳጅ ስለሚያቀጣጥለው ነው።

አሁን ግን እህት ዓለሜ የመጣው አማራ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖስ:  በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣ ልሳን

ያለምርጫው የተጎናፀፍከውን ማንነት

አክብሮና በእርሱም ኮርቶ ” ወላሂ ግደሉኝ
እንጂ ለዘላለም አማራ ነኝ ” ብሎ
የሚጋፈጣቸው ነው:: አነሱም በፊቱ መቅም

አቅቷቸው እየትወተረተሩ ነው:: በሚፈሩትና
በሚጠሉት ማንነት ተጋፈጣቸው ። የመኖር
መብቱን እነርሱ እንዲያከብሩለት መጠይቅ
አቆመ:: ምንም ብታደርግ ፣ ምን ያህል

ብታጎርስ ፣ ምን ያህል መልካም ብትሆን ፣
የቱንም እምነት ብትከተል ፣ ከየትኛውም ግዛት
ተከሰት እነርሱ የሚፈልጉት አማራ መሆንህን
ብቻ ነው ። ይህ ለእነርሱ ከበቂ በላይ ነው
አንተን በጅምላ ለመፍጀት። ይህ ደግሞ ከትንሽነት
ምስቅልናቸውና ከምቀኝነትና ከቅናታቸው የሚመነጭ ክፉ ደዌ ነው ።

አሁን እንዲያውም አንሻ ሰይድየሚባል ሻምበል የተሰየመ ተቋቁማል ብለው አጫውቱኝ እንዴት ልብ የሚያሞቅ ነው። ለነገሩ አማራ ባልውለታውን የማይረሳ ፈጣርውን የሚፈራና የሚያከብር፤ ካልነኩት የማይነካ ኩሩ ህዝብ ነው:: አባሎች እንዳሉት “አንሻ ሰይድ የትግላችን ቃል ኪዳን ሆና፣ ታናናሾቿ በማንነታቸው ኮርተውና ተከብረው የሚኖሩባትን ለሁሉም እኩል የሆነችን ሃገር ለመፍጠር እንታገላለን” ሲሉ የሻምበሏ አባላት ተናግረዋል።

እህታለም ባለፈው “ህፃን ልጄ ሊሞትብኝ ነው። የደረቀ ጡቴን ሲጠባ ልቤን ይስበኛል። ያመኛል። እያዞረኝም ነው” ስትይ ለአንድ ባለ ካሜራ የነገርሽውን እናንተ በማታውቁት፣ እኛ ዩቲዩብ በምንለው ተለቆ አየሁት። አዘንሁ አልልሽም። ያ የማውቀው ወተት እየተቀዳ የሚጠጣበት ማጀትሽ ተራቁቶ ሳይ አዘንሁ ሳይሆን መፈጠሬን ጠላሁ ነው ማለት ያሰኜኝ። ቸርነትሽን፣ ፍቅርሽን፣ ድፍን መንገደኛውን “አፈር ስሆን” ብሎ ያጎረሰ ርህራሄሽን አውቀዋለሁና ሳይገባሽ ለሆነው ሁሉ ባለ እዳነት ነው የተሰማኝ።

“አፈር ስሆን” ያለ የፍቅር ስብዕናሽን እንዴት አይኔ እያየ በርሃብና በመከራ አፈር ስትሆኝ እያየሁ “አዘንሁ” ልበልሽ እታበባዬ? ምንም ማድረግ ያለ መቻል ሲኦል ውስጥ ነኝ። ፀፀትና ጥፋተኝነት እንደ እሳት ነፍሴን በዝምታ እያቃጠላት ነው።

እንዴት “ኧረ የወገን ያለህ፣ የመንግስት ያለህ፣ ከቶ ሰው አይደለንምን፣ የነፍስ መግቢያ እንሆናችኋለን ነፍሳችንን አትርፉልን” የሚል ተማፅኖሽን፣ ጣርሽን ሰምቼ ምንም ማድረግ አለመቻል ግን እንዴት ያለ ቅጣት ነው? ‘ምነው ባልፈጠርስ፣ አቤት የእዳዬ ሸክም ክብደቱ’ እላለሁ ለእኔው። አትዘኝብኝ

ይሄንን ልመናችሁን የሚሰማ የመንግስት ባለስልጣን በቴሌቪዥን ብቅ ይልና፣ በእናንተ መከራ የለሰለሰ ምቾቱ ፊቱ ላይ እያንጠባረቀ “በርሃብ የሞተም፣ የተጎዳም የለም። ቢኖር ኑሮ በስልኩ ቀርፆ ‘ተራብሁ’ ይል ነበር” ብሎ ይዘባበትባችኋል። አቤት ይሄን መስማት ደግሞ እንዴት የባሰ እንደሚያም። ከርሃቡ በላይ የመንግስት አሽሙር ይገድላል። ባትሰሙት በተሻለ እህትወይ።

አንድ ጓደናዬ ከዝህ ከሀገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለሁልት ሳምንት መቶ ነበርና ሲመልስ ያጫውተኝ “አዲስ አበባ አንዲት ደሳሳ ቤት ቡና ልጠጣ ጓደኞቼ ጋር ተቀምጬ ነበር። ለመለመን በሚሰቀቅ ስብዕናቸው እጃቸውን ለምፅዋት የሚዘረጉ ወገኖቼን ብዛትና መጎሳቆል፣ የሰው ፊት እሳቱ የሚያደርጋቸውን ማየት አሰቃቂ ነው። ያጫወተኝ እንዴት ልብ ይሰብራል::

ደግሞ አለ….ብዙዎቹ ለጋ ህፃናት ናቸው። እነዚህ ህፃናት በደጉ ጊዜ ቢሆን ጧት ቂጣ በወተት ቁርሳቸውን በልተው፣ አቀበት ቁልቁለቱን እየተፍለቀለቁ፣ እየተሯሯጡ ደብተራቸውን አንግበው ትምህርት ቤት የሚሄዱ ነበሩ። ፊደል በሚቆጥሩበት፣ በሀገራቸው ባንዲራ ፊት ቁመው በሚዘምሩበት አንደበት “አባባዬ ዳቦ ግዛልኝ” እያሉ የአዲስ አበባን ህዝብ ፊት ይማፀናሉ። ላያገኙ ስንቱን በቁልምጫ ሲጠይቁ ይውላሉ መሰለሽ።

ያገራቸው ባለስልጣን ግን “ውሸት ነው አልተራቡም” ይላቸዋል። ይክዳቸዋል። ደጋግሞ ይገድላቸዋል። የማሽላው፣ የጤፉ፣ የወተቱ፣ የቅቤው ባለቤት ሁነው ለአገሬው በልቶ ማደር የነበራቸውን ሚና በጦርነት የነጠቃቸው መንግስታቸው ግን ዳግሞ ርሃባቸውን ክዶ ይቀጣቸዋል።

እህትወይ እኔ ይህን እያየሁና እያወቀሁ ምንም ላደርግ ላልቻልሁት እዘኝልኝ…. “ተማርልን። አንተ እንኳ ለቁም ነገር በቅተህ ችግራችንን ብትፈታልን” ብላችሁ በጨለማ እየዳከራችሁ ወደ ብርሃን ተራራ ያወጣችሁኝ፣ ህይወታችሁን እንደ ሻማ እያቀለጣችሁ ወደ እውቀት ብርሃን የሸኛችሁኝ እኔ አደራዬን በላሁ እናትዓለሜ። አቤት አደራን መብላት፣ ሲፈለጉ አለመድረስ፣ ተስፋን ማጠውለግ ህመሙ! መጥኔ።

ያጓደኛዬ ሲቀጥል እንዲ እያለ የነብሱን ሲቃ ተንፈሰ እዚሁ ቁጭ ባልሁበት ቡና መሸጫ ቤት በረንዳ አበባ ቄሱ መጡ። የቀደሱበትን፣ ያቆረቡበትን፣ እግዜርን ያመሰገኑበትን ደብር ጥለው አዲስ አበባ መጡ። የሚለመኑት እሳቸው ይሄን ሀጢያተኛ ህዝብና መንግስት ቁራሽ ዳቦ እየለመኑት ነው። ስጋ ወደሙን ፈትተው ሰማያዊው መና የሚያቀበሉት ቄስ ይሄው ጦርነት፣ ድርቅና ርሃብ ተባብረው ሞትን ሽሽት፣ ቁራሽ ፍለጋ እንዲፈልሱ አደረጓቸው። አምላክ ለፈተና የላከብን ይሆኑ ይሆን? መቼም ለእንዲህ አይነቱ ፈተናስ ወድቀናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ፌዴሬሽናችን ለዘላለም!! ኮሚቴዎቹ ግን…” MD 2013

የነተበ የክህነት አርማ የሆነው ጥምጣማቸው አናታቸው ላይ አለ። አይ አባቴ ይሄ ህዝብ ፈሪሃ እግዚአብሔር አለው መስሏቸው እኮ ነው። ይቅር ይበሉን። “ልጆቼ ስለ ወላዲቱ፣ ስለ መድሃኒተዓለም ቁራሽ ተዘከሩኝ” ይላሉ። የሚሰጥ የለም። ሁሉም በሀፍረት ይሁን በቸልታ እንጃ ብቻ አንገቱን ደፍቶ ያሳልፋቸዋል።

እኔ ግን ይጦረኛል ያሉትን የበላ ጦርነት፣ መቁንናቸውን ያመከነ ድርቅ፣ መራባቸውን የካደ መንግስት፣ ውለታቸውን የበላ ህዝብ ፊት ቁመው መልስ ያጡት ካህን ከሃጢያታችን እየፈቱን ይሄዱ ይሆን እላለሁ። በእንዲህ ያለው የስቃይ ችንካር ከመሰቃየት የባሰ አለ ይሆን? የሚል እረፍት የሚነሳ አቅመቢስነት የወለደው ፍርሃት ይንጠኛል። ተስፋችሁን የበላ ትውልድ አካል መሆኔ ያሳፍረኛል። ጥፋቴ ርቃኑን ይታየኛል። የምደበቅበት ጥፍር አጣሁ እናትዓለሜ “ተመስገን” የምትይው አምላክ ይሄን ሁሉ እያዬ ይሆን? የሚል ጥያቄ ላነሳብሽ እልና የእኔ መጠራጠርን የሚያመክን እምነትሽ “አምላክ እንደ ሰው አይደለም” ትዝ ይለኛል። በሰው ላይ ተስፋ የማድረግ ነገር እዚህ የመከራ አዙሪት በነገሰበት አገር እንዳልሽው አይሆንም። ግን የሰው መልኩ ሰው ነውና “ተለመኑኝ” የሚል ልመናሽ የማንን ልብ ያራራ ይሆን? ምናልባት የአምላክሽን? እንጃ ብቻ….. እዝጎ ነው መቼም የሚባለው! እያለ ያ ጓደኛዬ የነብሱን ሲቃ ተንፈሰ::

እህትዓለሜ እኔስ ቀኑ ይራራላችሁ እንጅ በሌላው ተስፋ እያጣሁ ነው–በእኔ በእራሴ ሳይቀር። የመንግስትን ነገር ተይው አይነሳ። “ቢቸገር ጨው ብድር” እንዳልሽው ነው። ብቻ እምነታችሁ ይርዳችሁ::

እንዲያው አንድ ነገር እህትዓለሜ በሞቴ ለዛሬ በምናቤ የማውጣውን የማወርደውን የሚያስጨንቀኝ የሃገሬን ህዝብ ልጠይቅ “ደሃ ሲበደል ፍርድ ሲጓደል የግፍ እንባ ይፈስሳል፣ የደሃ አንጀት በሀዘን ይቆረጣል፣ በሀገር ላይ ግፍ ይመጣልና።” ……እኔ ባደኩበት ከቤተሰቤም, ከመደራችን, ሆነ ከአካባቢያችን ሁሉ ስሰማ

ያድኩት ኢትዮጵያዊ ደግ ነው, አዛኝ ነው, ሩህሩ ነው ብቻ ለማለት በዙ ተብላል ግን እውነት በሞቴ ልጠይቅ ….በእውነት ምንድን ነው ኢትዮጵያዊነታችንን የሰለበው???

እህትዓለሜ እስቲ አንዴ የመጨርሻ ጥያቄ ይሄ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለውን ልጠይቀው ፍቀጅልኝ…… …

በአገር ቸው በአገራችን ላይ ንፁሃን በዘርና በሃይማኖታቸው ተለይተው በግፍ ሲገድሎ ፣ ሲታረዱ እያየን እየሰማን ምንም እንዳልተፈጠረ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ዝምታን የመረጥነው ለምንስ ይሆን ምክንያቱ? እንደዚህ ማንነታችንን የሰለበው። እሺ እኮ ለምን ይሆን በአዛውንቶች, በእናቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን ግፍስ የህዝብ ድምፅ የማትሆነው? መሆንስ የከበደህ?

ያሳዝናል እኛ ግን አለምአቀፋዊነን ለማለት ይሆን ወይ አዛኝ ቅቤ አንጎች ሆነን ይሆን ብቻ መልሱን ባጣውበት ምክንያት አልፈን ሄደን ስለ ስለ ፍሊስጤሞች በጋዛ ያለውን ጦርነት, እንዲሁም ስለዮክሬን ጦርንት ከነሱ በላይ በሶሻል ሚዲያው ሳይቀር እናጮሀዋለን, አንዳንዴ ደግሞ ሰለ አንደ ሞሮካዊ ህፃን ጉዳይ በማያገባን ገብተን እንዋትታለን። ለሰው ሁሉ ፍጥረት ማዘን ማሰብ መልካም ነው… ሰማያዊም ነው:: የኛ ነገር ግን ለየት ይላል::

አጠገብህ በረሃብ በጦርንት እየሞተ ላለው ምንም ሳታደርግ እረቅ ሄደህ ብዙ የሚያስብለት የሚጮህለት ለላው ……. “…አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ።” ሰቆ. 5፥1። “…በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፤ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።” ሰቆ.4፥9። “… ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋልና።” ኤር 14፥18። “የመድኃኒታችን አምላክ ሆይ፥ መልሰን፥ ቍጣህንም ከእኛ መልስ።”መዝ 85፥4

ቀኑ ይረዝም ይሆናል እንጂ የእነዚህ ምስኪኖች ደም እንደ ያዕቆብ ደም ኤሳው ሆይ የወንድም ወዴት ነው ማለቱ አይቀርም። ………“…የጻድቃን መድኃኒታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።

እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከኃጢአተኞችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋል፥ በእርሱ ታምነዋልና። መዝ 37፥ 39-40::

ውድ እህት ዓለሜ ይህን ደብዳቤ ስጽፍልሽ በበረታ ሐዘን፣ ጭንቀት፣ መከራ የነገሠበት፤ አጥንት ስር ድረስ ዘልቆ የሚገባ ናፍቆትና መብሰክሰክ ያየለበት ነው:: በመጨርሻም ደብዳቤየን የምቋጨው ያ አንቺ ያስተማርሽን ሲያከብሩን ማክበር ለተጎዱ መርዳት ለፍትሕ መቆም ያለ መደራደር የማይነቃነቅ አቋሜ መሆኑኑን በማረጋገጥ ነው!!

 

ካሌብ ታደሰ ጥር 04, 2016

ይድረስ በብዙ መከራ ውስጥ ላለሽው እህት ዓለሜ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share