January 4, 2024
2 mins read

ቋሚ ሲኖዶስ አላወግዝም አሳስባለሁ እንጅ አለ

415477677 782792903877170 2094494451350276146 nሰሞኑን አቡነ ሉቃስ እንዲወገዙ የሚጮኹ የብልጽግና ገላግልት በርከት ብለው ነበር። ቤተ ክህነቱ በቤተ መንግሥቱ በኩል ይቀልለናል ያሉት ውትወታቸው በዝቶ ሰነበተ።
ቋሚ ሲኖዶስ ግን ዛሬ ባወጣው መግለጫ
“በወንድማማችነት መካከል ጠብን ከሚዘሩ ጥላቻንና መራራቅን ከሚያሰፉ ንግግሮችና ድርጊቶች በመቆጠብ ኹሉም የማኅበረ ሰብእ ክፍል እግዚአብሔር ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይሰጣት ዘንድ በጸሎት እንዲተጋ” አሳስባለሁ ብሏል፡፡
“ከምን ጊዜውም በላይ ሰላምና ፍቅር በሀገራችን እንዲሰፍን በአንድነት ኾነን የምንሠራበት ወቅት ላይ በመኾናችን በመጪዎቹ ዐበይት በዓላት፣ በዘወትሩ መንፈሳዊ አገልግሎት ኹሉም በየደረጃው ያላችሁ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና አገልጋዮች . . . በየዐውደ ምሕረቱ ሰላምንና እርቅን በመስበክ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ችግር እንዲወገድ፣ ማኅበራዊ ሰላም እውን እንዲኾን የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል” ሲልም መግለጫውን ደምድሟል።
በዚህም የቤተ መንግሥቱ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከሽፏል። አሳስባለሁ አለ እንጅ አውግዣለሁ አላለማ። ደግሞም እኮ ለኹሉም የተላለፈ እንጅ ለእገሌ ብቻ አይደለም። ውግዘት ሲጠብቁ ማሳሰቢያ ኾነባቸው። ፊት የሚያጮል መግለጫ።

ዓባይነህ ካሤ – ዲን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop