ዳር-አገሩ አማራ ስንቅ አዘጋጅቷል ወይ!

December 17, 2023

Amhara

አማን ነወይ አገር፣ ቅዬውና አድባሩ፤
አማራ አማን ነወይ፣ ጎልማሳው ወጣቱ፣
ዘሬን አታጠፉም ሲል በመነሳቱ፣
የቱርክ ዱባይ ድሮን የሚዘንብበቱ፣
በአጥንቱ ካስማነት ባቆማት አገሩ!

አማን ነወይ ሎሌው ባንዳስ አማን ነወይ፣
ንስሃ ውስጥ ገብቶ ልብን አልገዛም ወይ፣
ምሳር ዛቢያ መሆን አልሰለቸውም ወይ፣
በመርዝ በድሮን ወገን ያስፈጃል ወይ?

አማን ነወይ አዲስ በራራ አማን ነወይ፣
የአምስት አመት እንቅልፍ አልሰለቸውም ወይ?

አማን ነወይ ኮልፌ መርካቶ አማን ነወይ፣
አማን ነወይ ቦሌ ፒያሳ አማን ነወይ፣
ስድስት አራት ኪሎ እንጦጦ አማን ነወይ፣
ግፍ ቅርቀብ መጫኑ በቃኝ አላለም ወይ?

ካሳንጅስ ኡራኤል ገርጅስ አማን ነወይ፣
አዲሱ ገበያ ልደታ አማን ነወይ፣
ፈረንሳይ ሌጋሲዎን ቃሊት አማን ነወይ፣
ቀንበር ቅልጥም ሊያደርግ አልተዘጋጀም ወይ?

አማን ነወይ ናዝሬት፣ አሰላ አማን ነወይ፤
አማን ነወይ ጅማስ፣ ሚዛን አማን ነወይ፤
አማን ነወይ ድሬ፣ ሀረር አማን ነወይ፤
አማን ናት ወይ ሻሹ፣ ጎባስ አማን ነወይ፤
አሩሲ ነገሌ፣ ዝዋይ አማን ነወይ፤
ተሰጋጦ መኖር በቃኝ አላለም ወይ?

አማራ በጦቢያ አማን ውሎ አድሯል ወይ፣
አገር አልባ መሆን አላስቆጣውም ወይ፣
በአንድነት ተነስቶ ጎራው አላለም ወይ?

ዳር-አገሩ አማራ በቃኝ ሸልሏል ወይ፣
መጨፍጨፍ ማሰደድ አቁሙ ብሏል ወይ፣
የአያቶቼ ልጅ ነኝ ብሎ ፎክሯል ወይ፣
ፋኖን ሊቀላቀል ስንቅ አዘጋጅቷል ወይ?

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

1 Comment

  1. በላይነህ አባተ ! ዐቢይ ከመጣ ጀምሮ በመቃወም ያልሰለቸህ ሰው ነህ:: ሁላችንም ተቃውሰን ነበር አንተ ብቻ ንቁህ ሆነህ ተገኘህ:: ስለተቃወምኩህ እግዚአብሄር ይቅር ይበለኝ:: አማራ በመጨረሻም እውነትን ስለያዘ ይህን አማራጠል የተቃወሰ ጠሚ ነቅሎ ያነሳዋል በርታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

new ethiopian music 2023 off
Previous Story

ዱባለ መላክ እንብኝ ለነፃነት new ethiopian Music 2023 | Official Music

sahlewerk
Next Story

“የልክልኩን ነገረው/ነገረችው” ፖለቲካ -ጠገናው ጎሹ

Go toTop