የ”ተረኝነት” ማዕረግ ማስቀመጫ! ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ – ጌታቸው ሽፈራው

ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ

በኢትዮጵያ ታሪክ በብሔር ማዕረግ የሰጡ ትህነግ/ህወሓትና የኦሮሞ ብልፅግና ናቸው። በንጉሱና ደርግ ዘመን አንቱ የተባሉ ወታደራዊ ጠበብቶች ነበሩ። ሙሉ ጀኔራልነት ላይ አልደረሱም ነበር። ወታደራዊ ማዕረግ እንደ ቡና ቁርስ በመደዳ አይታደልም ነበር።

ማዕረግን በመደዳ፣ ያውም በብሔር ማደል የጀመረው ትህነግ/ህወሓት ነው። ከጫካ የመጡ ናቸው ተብለው ሲናቁ “ከድሮዎቹ የተሻልን ነን” ለማለት ለሳሞራ ሙሉ ጀኔራልነትን አደሉት። ሳሞራ ሙሉ ጀኔራልነት ሲሰጠው የወል እንጅ የግሉ አልነበረም። “በኢትዮጵያ ታሪክ እኛ ነን የመጀመሪያ ሙሉ ጀኔራል” ለማለት ነበር አናቱ ላይ የማይችለውን ጀኔራልነት የሰቀሉለት። ማዕረጉ የብሔር ነበር። ሳሞራ የመጀመሪያው እኛ ነን የሚሉበትን ማዕረግ ተሸክሞ ይዞር እንደነበረው፣ አሁን ሌላ የግል ሳይሆን የብሔር ማዕረግ አናቱ ላይ ተቆልሎለት የሚዞር ሰው አለ። ብርሃኑ ጁላ!

የኦሮሞ ብልፅግና ከትህነግም ከፍ አደረገው። የወል ማዕረጉን “ፊልድ ማርሻ” አለው። ብርሃኑ ጁላ የብሔር ማዕረግ ነው የተሰጠው እንጅ በወታደራዊ ግዳጅ አይደለም። የተረኝነት ማሳመሪያ ማዕረግ ነው ያሸከሙት።

ብርሃኑ ጁላ ይህ ማዕረግ ሊታደለው ቀርቶ ወታደራዊ ፍርድ ቤት መቆም የነበረበት ሰው ነው። ሰሜን ዕዝን ቆሞ አስመታ። ቀጥሎ ሰራዊቱ ትግራይ ውስጥ ዳግም ተመትቶ በርካታ ውድመት ደረሰ። ወታደራዊ ኃላፊው ብርሃኑ ጁላ ነው። ነገር ግን ኃላፊነት የሚወስደው እንደ ግል አይደለም። ብርሃኑ ጥፋተኛ ቢባል ኦሮሞ ጥፋተኛ የተባለ ነው የሚመስላቸው። የብሔር ጀኔራል ነው። እየወጣ የብሔርተኛ መግለጫ የሚሰጠውም አናቱ ላይ የተቆለለው በብሔር ስም የተሰጠው የማይገባ ማዕረግ ስለሆነ ነው!

ብርሃኑ ጁላ ሲቀባጥር ከሰማችሁት እንደ ማዕረጉ የጥርቅምቅም ሀሳብ አሸክመውት፣ እንዲህ በል ብለውት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሪሂቡ አፍሪካ - በስንታየሁ ግርማ አይታገድ

የብርሃኑ ጁላን ማዕረግ ስታስቡ ሳቃችሁ ከመጣ እንደ ቡድን የተሰጠ መሆኑን አትዘንጉት። እንደ ስልጣኑ፣ እንደ ገንዘቡ በስግብግብነት “ለእኛ ይገባል” ብለው ያስቀመጡበት ነው።

ምርኮኛ ብርሃኑ ጁላ
ምርኮኛ ብርሃኑ ጁላ

 

ጥሪ በዝቶብኝ ተቸግሪያለሁ›› ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ፣ እነጌታቸው ጭንቅ ውስጥ ገብተዋል፣ የታየ ጠበቃ ምላሽ ‹‹እንደነ ለማ በሰላም ቢወጣ…››

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share