ለብአዴን መኖር የሚከፈለዉ መስዋዕትነት ስንት ነዉ ?

Biaden 1ብአዴን (ብሄረ አማራ ዴሞ.ንቅናቄ) ስም፣ ምግባር እና ተግባሩ ሁሉ በተዉሶ የተገኘ በመሆኑ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ ከፍጥረቱ አስከ ሞቱ በምግባርም ሆነ በተግባር አያዉቀዉም ፡፡

ራሱ ድርጂቱ ብአዴንም ማን እና ለማን እንደሚሰራም ሆነ በማን ስም እንደሚኖር ወይም ህልዉናዉ እንተመሰረተ አያዉቅም ፡፡

በርግጥ ስያሜዉንም ራሱ ድርጂቱ በራሱ እና እወክለዋለሁ በሚለዉ ህዝብ ልክ አለመሆኑን ጥንት ቀርቶ ዛሬም መረዳት አልቻለለም ፡፡ በአዴን የሞተዉ በሰፊዉ ህዝብ ላብ፣ ደም እና ህይወት ዋጋ የተገኘዉን ድል ሁሉ ከአሂአዴግ መስረታ ዕለት ጀምሮ አሳልፎ በመስጠት የሚታወቅ አድርባይነት እና ጥገኝነት የተተኛወተዉ ስብስብ መሆኑን እያወቀ ኢትዮጵያን እና የዓማራን ህዝብ ክብር ዝቅ በማድረጉ ለፀረ ኢትዮጵያዉያን እና ዓማራ ህዝብ ታማኝ አገልጋይ መሆኑ ነዉ ፡፡

ዋና ዋና የትግል ጓዶቹን እና ነፍስ ያላቸዉን እነ አቶ ሙሉዓለም አበበ(መጀመሪያዉ ር/መስተዳደር)፣ እነ ዶ/ር አምባቸዉ መኮንን ፣ እነ ጀ/ል አሳምነዉ ፅጌን…..የመሳሰሉትን  ዛሬ ላይ ለመድረሱ ምክነያት የሆኑትን ለመዘከር እና ከእነርሱም መማር የማይችል መሆኑ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ እና ዓማራ ህዝብ ለሚገኝበት  የመከራ ምዕራፍ መንስዔ ነዉ ፤ ነበር ፡፡

በአዴን ወደ ግዕዙ በድንነት ስለመቀየሩ ከሶስት አሰርተ ዓመታት አስቀድሞ በጥዋቱ ህዝቡን እና አግሪቷን የከዳ ቢሆንም ዛሬም በጥገኛ የፖለቲካ ስልጣን ተጣብቆ ለመኖር በራሱ ህዝብ እና አገር ላይ የሞት አዋጂ መፍቀዱ በተለይም በዓማራ ህዝብ ላይ ጥልቅ ጥላቻ እና ንቀት ያለዉ መሆኑን እና በቂም በቀል በስልጣን ለመቀጠል ያለዉ ፍላጎት እየደረሰ ያለዉ የዓመታት መከራ ፅዋ ሞልቶ ሲፈስ የሚታይ ነዉ ፡፡

በአስራ ዘጠኝ  ዘጠና ሰባት ምርጫ  በዓማራ ህዝብ በተለይም በጎጃም የደረሰበት ዉድቀት እና ከዚያም በፊት ሆነ በኋላ በተቐጣጠሉ የህዝብ የመብት ፣ የፍትህ እና የህልዉና ጥያቄ በብአዴን -ኢህአዴግ ጥርስ የተነከሰበት ህዝብ ዛሬ“ በጥቁር ጠበንጃ “ ስም ኢትዮጵያ እና ህዝቧ  በዋናነት የዓማራ ህዝብ እየከፈለ ያለዉ ሁለንተናዊ መከራ በብአዴን -ኢህአዴግ የግፍ ዉሳኔ  የዕሳት እና የጥፋት ቤተ ሙከራ እንዲሆን አድርጎታል ፡፡ ለስልጣን እና የቡድን ጥቅም ሲባል ህዝብ ፣ የህዝብ ተቋማት ፣ የዕምነት እና የባህል ቅርሶች እና ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ሀብቶች በማዉድም ለመኖር መፈለግ እና ለዚህ ሲባል የሚከፈለዉ ዋጋ ስንት አስኪደርስ እንደሆነ የሚጠይቀም ሆነ የሚጠየቅ አለመኖር ግን የዘመናችን አሳዛኝ ታሪካዊ እና ሰባዊ ዉድቀት ነዉ ፡፡

ዛሬ በ21ኛዉ ክ/ዘመን ላይ ሆኖ ለህዝብ እና ለአገር ግዴለሽ የሆነ ድርጂት ወይም ኃላፊነት ያለዉ አካል ቢኖር ከኢትዮጵያ ዉጭ ስለመኖሩ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡

በቅርብ እንኳን በመካከለኛዉ ምስራቅ በአስራኤል እና በፍልስጤም መካከል በተነሳዉ ግጭት ወይም ጦርነት በተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኃላፊነት የሚገኙ ሰወች በግል ምልከታ ባሰሙት  ድጋፍ እና መንቀፍ ከስልጣናዉ የተነሱ ወይም እንዲነሱ ሆኖ መስማታችን የማንማርበት ከሆነ ዕዉነት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ስለ ፖለቲካ ስልጣን እና ስለ ኢህዴግ  ሲባል ዋጋ እንዲከፍሉ የሚሆነዉ አስከ ስንት እና የት ነዉ የሚል ጠያቂ እና ተጠያቂ ከድፍን ፻ ሚ/ን ህዝብ ዉስጥ እንዴት ሠዉ እንጣ ? ፡፡

አንድነት ኃይል ነወ

Allen

Leave a Reply

Your email address will not be published.

corenel Abiy
Previous Story

በኢትዮጵያ ምድር የኮነሬል አብይ የድሮን ቦንብ ጭፍጨፋ ዘመን!!! –  ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

024 1433
Next Story

0:24 / 14:33 የፋኖ ታሪካዊ ኦፕሬሽን በደጀን ከተማ |ፋኖ በሶስት ግንባር እየለበለባቸው ያሉ ኃይሎች | በዐቢይ የተካዱት ባለሥልጣናት አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

Go toTop