ዕዉነተኛዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እና ህዝባዊ መከላከያ ኃይል ምድር ጦር፣ ሰማይ ኃይል እና ባህር ኃይል የተቆቋመበት ዘመን ጥቅምት ፲፭ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ዓ.ም መሆኑ ሀቅ ነበር ፤ነዉ፡፡
ይሁን እና የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል እንደነበር አለ ማለት ግን ክህደትም ፤ዉሸትም ስለመሆኑ አይጠረጠርም ፡፡
ግንቦት ፳ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት የጥልመት ዕለት ጀምሮ በኢህዴግ ጥርስ የተነከሰበት ብሄራዊ እና ህዝባዊ ጦር ቀርቶ ዛፉ ሳይቀር ተነቅሏል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት አባላት ከዚያች ዕለት ጀምሮ አስካዛሬ የት እንዳለ ታሪክን ፣ ህዝብን እና ባለቤቱን የቀድሞዉን ሠራዊት እና ቤተሰቦችን መጠየቅ ይበጃል፡፡
የኢህዴግ በተለይም የትህነግ ታጋዮች ስም አዲስ አበባ አበባ ይዞ የተቀበለ ሁሉ ወደ ኋላ የአስራ ሰባት ዓመት ደምወዝ እና ጡረታ አበል እንዲታሰብ እና እንዲከፈል ሲደረግ የቀድሞዉ ብሄራዊ ህዝባዊ ጦር የ፹፫ ዓመት ዐድሜዉን ይዞ በ ፹፫ ዓ.ም. እንደ ዘገ ብረት ከመሬት ወድቆ እና ከአፈር ተቀላቅሏል፡፡
አንኳንስ ለአገር ዳር ድንበር እና ክብር ሲፋለም የነበረ ቀርቶ ሠላማዊ እና በዉጊያ ምንም ዓይነት ተካፍሎ ያልነበረዉ ህዝብ፣ ግዑዝ ነገር እና ዛፍ ተነቅሎ መጣሉን ወይም መጋዙን መርሳት እንዴት ይቻላል፡፡
በአንድ ወቅት ከ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም ድህረ ኢህዴግ በኋላ የአቅም ግንባታ የነበሩት በበቃ ቡና ተክል ተገኝተዉ የተናገሩት “ይህ ቡና ነበር ሲዋጋን የነበረዉ በአስቸኳይ ሊወገድ ይገባል „ በማለት ቀጭን ትዕዛዝ በምሽት ጨረቃ መስጠታቸዉን በጊዜዉ የድርጂቱ ባልደረባ የነበሩ እና በምሽት ሲያስተናግዷቸዉ የነበሩ ሠዉ ሚዛን ፤ዓማን ዙሪያ በአንድ አጋጣሚ ያጫወቱኝን ሳስታዉስ ኢህአዴግ አገር እና ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጠፈጥሮም ጠል መሆኑን የተረዳሁበት ጊዜ ነበር ፡፡
ተራራ የሚያንቀጠቅጥ በሚል ተራራ ለመዋጥ፤ መሬት ለመሰልቀጥ …..እንዲያዉ ምኑ ነበር ያልተሞከረዉ ዓባይን ለማድረቅ ፤ ዳሽንን ካለበት ለማላቀቅ ሲቅት በወረቀት መሞከሩ የዚህ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ /አስገኝ አረንጓዴ ብር በለዉ ዶላር በጥላቻ ስም ባልበለዉ ላጥፋዉ መባሉ ያኔም አሁንም ድመት መንኩሳ ዓመሏን አትረሳ ነዉ ፡፡
ርግጥ ነዉ ምሽት እና አረቂ ሰኔ እና ሰኞ ሆነዉ ሆድ ያበዉን …….እንዲሉ ቢሆንም ቂም የተቋጠረበት የኢትዮጵያ ህዝብ እና ህዝባዊ ብሄራዊ ጦሩ ብቻ እንዳልነበር ዕልፍ አዕላፍ ጉዳዮችን በመሬት ላይ ላለ እና ለነበር ብዙ ዕማኝ አያስፈልገዉም ፡፡
ሁላችንም በኢትዮጵያ የነበሩ እና ያሉ ህዝባዊ ተቋማት እንደ ጥንቱ፣ አንደ ስያሜ፣ እንደ ስራቸዉ እና ግብራቸዉ ቢሆን ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን አንድም ቀን ደስ ባለን ዳሩ ፍየል ዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ….ሆኖ ነገሩ ሁሉም በሁሉ ባይተዋር ሆኗል በአገሩ ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !
አለን !