ተሳጥናኤል ጋራ ሽምግልና ሲሉ!

 

እነ እርመ በላዎች እነ ልበ ቢሱ፣
ዛሬም እንደ ትናንት ሕዝብን ሊያሳስቱ፣
ተሳጥናኤል ጋራ ሽምግልና ሲሉ፣
ቅዱስ ሰማእታት እግዜርን አይፈሩ፡፡

ፈጣሪን አስክዶ ሔዋንን ታሳተው፣
አዳምን ተገነት ወደ ምድር ታስጣለው፣
በእምብርክክህ ተሳብ ይቀጥቅጡህ ታለው፣
ተእባብ ጋር ሊታረቅ ይቀመጣል ወይ ሰው?

ታስራ ሁለት ሐዋርያት አንዱ አርጎ ቢመርጠው፣
በሰላሳ ዲናር በኻራጅ  ተሸጠው፣
በእሾህ አስጨቅጭቆ ደሙን ታስፈሰሰው፣
ተመስቀል በምስማር ችንክር ታስደረገው፣
ተይሁዳ ጋራ እንዴት ውል ያስራል ሰው?

ሙሴ መጣ እያሉ ሕዝብን ያሳሳቱ፣
ለትናቱ ኃጥያት ንስሐ ሳይገቡ፣
ድስኩርን ሲያበዙ ጣት ሲያፍተለትሉ፣
ተእባብ ተይሁዳ ታረቁን ሲሰብኩ፣
ተሳጥናኤል ጋራ ሽምግልና ሲሉ፣
ራሱን ታጠፋው ተሰምቶት ክህደቱ፣
የአስቆርቱን ይሁዳ ታህል እንኳ አያፍሩ!

 

እግዚኦ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንገት የሚያስደፋ ! - ማራኪ ስዊድን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share