ዝናሽ ታያቸውና የመጽሐፍ ቅዱሷ አስቴር

ዝናሽ ታያቸው

የጭራቅ አሕመድ ባልተቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የወንጌል ዘማሪ ነኝ ትላለች፡፡  ስለዚህም ጥያቄው ስለ ወንጌል ታውቃለች ወይስ የገጠሙላትን ሁሉ እንደ በቀቀን (Parrot) እየበቀቀነች ታንጎራጉራለች የሚለው ነው፡፡  ሁኔታዋ ሁሉ የሚያሳብቅባት ግን ስለ ወንጌል ማወቅ ቀርቶ ፍንጭም እንደሌላት ነው፡፡  ፍንጭ ቢኖራት ኖሮ በመጽሐፈ አስቴር ውስጥ በሰፊው የተወሳውን የመጽሐፍ ቅዱሷን የአስቴርን ታሪክ በትንሹም ቢሆን ባስታወሰች ነበር፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሷ ንግሥት አስቴር ባሏ ንጉሥ አርጤክስስ (Ahasuerus, Xerxes) አይሁዳውያንን በገፍና በገፍ ሊጨፈጭፍ በተነሳ ጊዜ፣ እኔም ሚስትህ አይሁዳዊ ነኝና ጭፍጨፋህን ከኔ ጀምር የሚል ጽኑ አቋም በመውሰድ ሕዝቧን ከጭፍጨፋ አድና፣ የባሏ እኩይ አማካሪ የነበረውን ፀረይሁዳውን ሐማንን በስቅላት አስቀጣችው፡፡

ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ግን ባሏ ጭራቅ አሕመድ አማሮችን በጨፈጨፈና ባስጨፈጨፈ ቁጥር “እየሱሴ የኔ ጌታ፣ ያረገልኝ ትልቅ ውለታ” እያለች በመዘመር በጭፍጨፋው እንዲቀጥልበት ታበረታታዋለች፡፡  አማራን ይበልጥ አዳክማ ለባሏ ለጭራቅ አሕመድ ጭፍጨፋ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ደግሞ ጎንደርን ካማራ ለመነጠል ከነ አገኘሁ ተሻገርና መላኩ አለበል ጋር ትመሳጠራለች፡፡  አጋሮቿ ዮናታን አክሊሉንና ሶፍያ ሽባባውን የመሳሰሉ ፀረተዋሕዶ ጴንጤወች ናቸው፡፡  አማካሪወቿ ደግሞ ሌንጮ ለታንና ሌንጮ ባቲን የመሳስሉ የባሏ ፀራማራ አማካሪወች እንደሆኑ ያደባባይ ንግግሮቿ በግላጭ ይመሰክሩባታል፡፡  እሷ ልጇን ትድር ይመስል በጥበብ ተሽሞንሙና በጠያራ ጎንደር ስለምትሄድ ብቻ፣ ልጆቻቸውን ለመቅበር አዲሳባ እንዳይገቡ የተከለከሉትን ያማራ እናቶች፣ ሰላም የምታገኙት ዳቧችሁን በልታችሁ አርፋችሁ ከተቀምጣችሁ ብቻ ነው በማለት በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደደች ትሳለቅባቸዋለች፡፡

አሁን ላይ ደግሞ ያማራ ሕዝብ በከባድ መስዋእትነት ያፈራረሰውን ብአዴንን ባማራ ክልል ላይ መልሳ ለመገንባት የጎንደር ፋኖወችን በሽምግልና ሰበብ ትጥቅ ልታስፈታ ትጣጣራለች።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ስለዚህም ይህች እኩይ ሴት ከባሏ ከጭራቅ አሕመድ ባልተናነሰ ሁኔታ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ናት፡፡  በመሆኗም ያማራ ሕዝብ ሊመለከታት የሚገባው ጭራቅ አሕመድን በሚመለከትበት አይን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰሞኑ ወታደራዊ ግርግር ለማን ነው!? | Hiber Radio Special Program Jan 21, 2023 | Ethiopia

ጣልያኖች ጭራቁን ቤኒቶ ሞሶሎኒን (Benito Mussolini) ዋጋውን ሲሰጡት፣ የሞሶሎኒ ቀንደኛ አበረታታች የነበረችውን ጭራቂቷን ውሽማውን ክላራ ፒታችንም (Clara Petacci) በተመሳሳይ መንገድ ዋጋዋን ሰጧት፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማራ እጅ ሲወድቅ ደግሞ እሱ የሞሶሎኒን (Benito Mussolini)፣ ዝናሽ ታያቸው ደግሞ የክላራ ፒታችን (Clara Petacci) ጽዋ መቅመስ አለባቸው፡፡  ያማራ ሕዝብ የጭራቅ አሕመድ ዓይነት ዳግም እንዳይፈጠር ማድረግ የሚችለው፣ ጭራቅ አሕመድንና ግብራበሮቹን (በተለይም ደግሞ ብአዴናዊ ግብራበሮቹን) ለሌሎች ማስተማርያ በሚሆን መንገድ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣቸው ብቻ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

Mesfin.Arega@Gmail.Com

6 Comments

 1. ጊዜው ሰው ፍራንክ ለቀማ እምነቱንና ማተቡን በመተው የሚሯሯጥበት ነው። አልፎ ተርፎም የሌላው መከራና ሃበሳ ነግ በእኔ ላይ በማለት እጅንና ሃሳቡን የሚዘረጋው ሰው መጠን ከቀን ወደ ቀን እየመነመነ ይገኛል። የእኛውን የእምነትና የወግ ባህል ለተመለከተም ተግባሩና ቃሉ የማይገናኝ እንደሆነ ለመለየት አያዳግትም። ወይዘሮዋ ባላቸው የሚፈጽመውንና የሚያስፈጽመውን ግፍ መስማትም ማየትም አልፈልግም በማለት አይናቸውን ጨፍነው ካልሆነ በስተቀር ምድሪቱ በመከራ እየተናጠች ነው። ሌላው ቢቀር ቤ/ክርስቲያናትና መስጊዶች በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ይቁም በማለት በጋራም ሆነ በተናጠል ድምጽ ያሰሙበት ጊዜ የለም። ያው የሰማይ ቤታችሁ እያሉ ሰውን እያሞኙ የራሳቸውን የምድር ቤት የሚያሰፉ እነዚህ አታላዪች ዛሬ በዓለም ዙሪያ ላይ ሰውን እስከ አጥንቱ የሚግጡ የቁም ሙታኖች ሆነዋል። ለፍትህ መቆም፤ ለተጨቆነና ለተረሳ መፋለም በእነርሱ ቤት የራሳቸውን የኑሮ ብልሃት ያዛባዋልና አይፈልጉትም።
  የጠ/ሚሩ ባለቤት ጊዜ እያለ የራሷን አቋምና እይታ ለህዝብ ግልጽ ማድረግ አለበት። ማንም ቢሆን በቤተመንግስት ስለሚኖር መከራና ሃበሳ አያገኘውም ማለት አይደለም። ሁሉም በጊዜው አስለቅሶ ያለቅሳል። እውቁ ጀርመናዊ የመለኮት ሰው Dietrich Bonhoeffer እንዲህ ይለናል “Silence in the face of evil is evil itself”. ስለሆነም በእምነትና በሌላም ሳቢያ ተገን አበጅቶ ግፍና በደልን እንዳላዪ እያዩ ማለፍ የበደል በደል ነው። የሰው ልጅ እምነቱ የሚለካው ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆንና ዘርን፤ ቋንቋን፤ ክልልንና ሃይማኖትን ተገን ሳያረጉ ለሰው ልጆች ሙሉ መብት በመታገል ነው።

 2. ስለዚህች ሴትዮ የተጻፈው የግርጌ ማስታወሻ ትክክል ነበር ዘሃበሻ ላነሳበት ምክንያት ቢሰጥ መልካም ነበር፡፡ ከግርጌ የሚጻፉ አስተያየቶች ብሽሽቅና ብልግና እስካልሆኑ ድረስ ብዙ ትምህርት ሊገኝባቸው ይችላል፡፡

 3. ስለኝህ ሴትዮ ከግርጌ የተጻፈው አስተያየት ስህተት አልነበረም የድር ገጽ ባለቤቶች ግን ለምን እንዳወረዱት መግለጫ አልሰጡንም፡፡

 4. (2ኛ ነገሥት 9:10) ኤልዛቤልንም በኢይዝራኤል እርሻ ውሾች ይበሉአታል፥ የሚቀብራትም አታገኝም። በሩንም ከፍቶ ሸሸ።
  ይህ ጽሁፍ ከርእሱ ጀምሮ አሳች ነው::
  ንግስት አስቴር እንደአማራ ህዝብ በግፈኞች ለማጥፋት የተዘመተበትን የእስራኤል ህዝብ ለማዳን በነፍስዋ ተወዳድራ ብሞትም ልሙት ብላ ንጉሱ ዘንድ ገብታ ህዝብዋን በጸሎት ተደግፋ ያተረፈች ነች ::እንደንግስት አስቴር ህዝቤን ለመጥፋት የታወጀበትን አድንልኝ ብላ በጸሎት ጉባኤ በኢትዮጵያ በቅርቡ ያቀረበች እህትና የመሰሉት ትክክለኛ አስቴሮቻችን ናቸው::
  ታየች ከጅማሬዋ ሃገር ያፈረሰ የወያኔ ኪነት አረሆ ዘፋኝ ከከሃዲ ባልዋ የወያኔ ስለላ ኢንሳ ባደረባ ውስጥ ውስጡን ጌታው መለስ እንዳለው ኦህዲድ ሲፋቅ ኦነግ ነው እንደሚለው የእርጉዝች ማህጸን በሳንጃ ቀድዶ የሚበላው እነግን ያገለገለ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው ውሸታም አስመሳይ ፖለቲከኛ አብይ አህመድ ሚስት ናት::
  አብይና ዝናሽ የነቢያቱ ጸር የኤልዛቤልና የባልዋ የአክእብ ትክክለኛ ምሳሌ መሆናቸውን አንድ ወንድም ሰሞኑን በክርስቲያንብሎገር የገለጸው ትክክል ነው::ወራሪው ፈርኦንንባህር ያሰመጠ ትእቢተኛውናቡከደነጾርን እንሰሳ ያደረገ ጌታ በአብይ አህመድ ላይ እንዲፈርድ እንጸልይ::ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

 5. ሴትዮዋ ከስማይ ህይወት የምድራዊን ደስታ የመረጡ ይመስላል ሁለቱን ይዞ መጓዝ አይቻልም የምድራርዊዉን መምረጣቸው ሃሳባቸውን ያሳርፈዋል ነገር ግን መስፍን እንዳለው እንደ ፒታች በፒያኖ ክር ወይም ደግሞ እውር ድምብሩ የጠፋው ቄሮ አናታቸውን ቢላቸው እዳው ለእኛው ነው ቢችሉ እንደ እብሪት ነገር ባይሞካክራቸው መልካም ይመስላል እነ ወ/ሮ ሶፊያን ሰብስቦ መጯጯህ እንኳን እላይኛው ቤት የአብይም ቢሮ የሚደርስ አይመስለኝም፡፡ ቢችሉ ጫማ ሮም እገዛለሁ ብለው አንዱ አገር እንደእኔው ስደት መጠየቅ ነው አንድ ምልክት ሰውነታቸው ላይ ቢገኝ ሌላ ማስረጃም አያስፈልግም ደብድበውኝ ነው ቢሉ ይታመናል፡፡ ትኩር ብዬ ሳየው ሳቃቸውም ሳቅ አልመስለኝ ብሏል ጎበዝ ስንቱን ቻልነው? ከአዜብ በኋላ እንዲህ ያለ ነገር ይገጥመናል ብሎ ማን ይጠረጥራል? ዳቦ ቤት ገምብቻለሁ አርፋችሁ ዳቧችሁን ብሉ የተባለው ኩሩዉ ጎንደሬው ነው? አገኘሁ ተሻገር ሹክ ብሏቸው ካልሆነ እንዴት ሊዳፈሩ ቻሉ? ይህ ነገር ልዩ ምርምር የሚጠይቅ ነው በጤናቸው አይመስልም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share