ያልተገታ ምላስ አማራውን ይጎዳዋል አክሎግ ቢራራ (ዶር)

/

የጂምላ እልቂት፤ የጂምላ እስራት፤ የጂምላ እንግልት፤ የጂምላ ፍልሰት፤ የጂምላ የስነልቦና ጦርነት፤ የጂምላ የተቋማት ውድመትና የማህበረሰባዊ ኢኮኖሚ ምክነት የሚካሄድበት ሕዝብ አማራው መሆኑ አያከራክርም። ለዚህ ነው፤ የአማራው ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተናበበ ትግል የጀመረው። ለዚህ የተቀደሰ የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የኢትዮጵያዊነት፤ የዜግነት መብትና የዲሞክራሲ ትግል ድርሻየን በመወጣት ላይ እገኛለሁ።  

ጥራት ያለው ዘገባ እስካደረጉ ድረስ ነጻ ሜድያዎች ከፍተኛ ሚና አላቸው። የሃሜት፤ የስም ማጥፋት፤ የድብቅ አጀንዳ ምሺግ ከሆኑ ግን ጉዳታቸው ያመዝናልል። በተሳሳተ ትርክት የሚሰቃየው የአማራ ሕዝብ በራሱ ስም ሜድያዎች የተሳሳቱ፤ ሃሜታዊ፤ ክሳዊና ሹሙጣዊና አማራውን ከአማራ የሚለያዩ ትርክቶችን ካስተጋቡና የገቢ ምንጭ ካደረጉ የአማራውን የፍትህ ትግል ይበርዙታል። በአሁኑ የሞት የሺረት ወቅት፤ አማራው ወዳጅ እንጂ ሰው ሰራሽ ጠላት አያስፈልገውም። አማራው ተባብረህ ምታው እንጂ ከፋፍለህ ብላው አይፈልግም።

የዚህ ሃተታ መሰረት በቅርቡ ሃብታሙ አያሌው የ360 ቴሌቪዢን ሜድያ ሚናውን ተጠቅሞ፤ ያለ አግባብና ያለ ቦታው የኔን ስም ለይቶ ያሰራጨውን ስም ማጥፋት ዘገባ ለማውገዝና እንዲስበው ለማሳሰብ ነው። 360 የዘለፋ፤ የስም ማጥፊያ ሜድያ መሆኑን በፍጥነት ማቆም አለበት። ሃብታሙ በኔ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የታወቁ አማራዎች ላይ የስም ማጥፍት ዘመቻ አካሂዷል። ለምሳሌ፤ ከታች አባሪ ያደረግሁት የዘሃበሻ ዘገባ እንደሚያሳየው 360 በባለ ኃብቱ የአማራ ትግል ደጋፊ በወርቁ አይተነውም ላይ ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂዷል። ወርቁ አይተነው ከሃገሩ ሸሺቷል።

ሃቁ ምንድን ነው?

ሃብታሙ አያሌው እኔን ሳይጠይቀኝና ሳያጣራ፤ አምብሳደር ስለሺ በቀለ ባከሄዱት የዙም ስብሰባ ላይ “ዶር አክሎግ” ተገኝቷል ብሏል። በሃብታሙ ስሌትና ዘገባ በዚህ የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ስብሰባ ላይ መገኘቴ በራሱ ከአብይ መንግሥት ጋር ቅርበት እንዳለኝ ያሳያል ማለቱ ነው። ለሃቅ ከቆመ፤ ሃብታሙ እኔን ይህ ስብሰባ በምን አርእስት ላይ ነው? ብሎ ሊጠይቅ ይችል ነበር። የቀደመው ህወሃት መሰል ሴራውን ስኬታማ ለማድረግ በሚመስል መልኩ የኔን ስም ማንሳቱ የተለየ ቅቡልነት ያስገኛል የሚል እምነት ስላለው ይመስለኛል። ስም ማጥፋት ከሜድያ ነጻነት ጋር አብረው አይሄዱም ብየ ነግሬዋለሁ፤ አይሰማም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግልጽ ደብዳቤ ለዶ/ር በያና ሱባ (የኦዴግ አመራር) - ከዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ ጂግሳ

ነገሩን የከረረ የሚያደርገውና 360 ዘገባውን እንዲስበው የሚያስገድደው ሃብታሙ አያሌው የ360 ን  መድረክ ተጠቅሞ የኔን ስም ክሳዊና የአቢይ መንግሥት ወገንተኛ ለማስመሰል የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዓምት መቀየሪያ ግብዣ በኤምባሲው ባካሄደበት ወቅት መሆኑ ነው።

እኔ ለፌስታው አልተጋበዝኩም። ብጋበዝም አልሳተፍም። ያልተጋበዝኩበት ዋና ምክንያት እኔ በአብይ ዘግናኝ መንግሥት የኦሮሙማ አጀንዳ ላይ የምጽፈውና የምናገረው የማያሻማ አቋም መያዜን የሚያሳይ በመሆኑ ነው።

ሃብታሙ አያሌው ፌስታውንና የሕዳሴ ግድቡን ቀደም ሲል የተካሄደ የዙም ስብሰባ ለምን አቆራኝቶ አወጣው? በኔ ስሌት ያወጣው ሆነ ብሎ እንጂ ሳያስበው አይደለም። በጀርባ ሌላ ነገር አለ የምለው ለዚህ ነው።

የ360 ታዳሚዎችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው የሚከተለውን ነው።

 • የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን፤ አማራውን ጨምሮ ይመለከታል። እኔ አምባሳደር ስለሺ በሰጡት ማብራሪያላይ እንድገኝ ተደውሎ የተጠየቅሁበት ዋና ምክንያት ፕሬዝደንት ትራምፕ “ግብፅ ግድቡን ቦምብ የማድረግ መብት አላት” ባሉበት ወቅት ከቅርብ ባለሞያ ጓደኞቸ ጋር ሆነን አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት፤ ለአሜሪካ የፋይናንስ ተቋምና (ትሬዠሬ)፤ ለዓለም ባንክ ፕሬዝደንትና ቦርድ ባለሥልጣናት የአቋም ደብዳቤ አዘጋጅተን ዶር አክሊሉ ኃብቴ፤ ፕሮፌሰር አልማዝ ዘውዴና እኔ በአካል ዋሺንግቶን ዲሲ ለሚገኙት ባለሥልጣናት ሁሉ አቅርበናል።

 

 • የአራተኛውን የሕዳሴ ግድብ ሙሌት በሚመለከት እኔ እንድገኝ የተጠራሁበት ምክንያት አንድ፤ በአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ ባለቤትነት ላይ በጥናትና ምርምር የተደግፉ ትንተናዎችንና ምክረ ሃሳቦችን ስላቀረብኩ፤ ሁለት፤ እኔ የኢትዮጵያ ውሃዎች መማከርት ካውንስል (Ethiopian Waters Advisory Council) መስራችና ሊቀ መንበር ሆኘ ስላገለግልኩ ነው።

ለ 50 ዓመታት ስሟተትላት ለቆየኋት ኢትዮጵያ፤ ህወሕት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጀሞሮ የህልውና አደጋ ለተከሰተበትና ለምታገልለት ለአማራ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ልማት አግባብ አለው ብየ አሁንም፤ ወደፊትም ለምደግፈው ለሕድሴ ግድብ ሙሌት ዘገባ እንኳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቀርቶ፤ የግብጽና የሱዳን መንግሥት ጥሪ ቢያደርጉልኝ እገኛለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትዕግሥተኛ ሰው - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ለመሆኑ ሃብታሙ አየሌው እኔ በሕድሴ ግድብ ውዝግብ አል ጃዚራ ጋብዞኝ ዶሃ ፤ ክታር መሄዴን ያውቅ ይሆን?

ስለሆነም በአምባሳደር ስለሺ የዙም ስብሰባ ተገኝቻለሁ። ወደፊትም ከጋበዙኝ እገኛለሁ። አለመገኘት ድንቁርና ነው። ሕዳሴ፤  የአማራውን ህይወት በቀጥታ ይመለከተዋል። የአባይ ወንዝ እኮ የአማራ ሕዝብ እምብርትና ህይዎት ነው።

ሃብታሙ አያሌው የማያውቀው ሃቅ አለ። ይኼውም ግድቡ የተጸነሰው በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት፤ ፕሮጀክቱ የተጀመረው በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ፤  ሕዳሴ ግድብን በሚመለክት የሶስተዮሽ ውል የተፈረውመው በጥቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆኑና የአራተኛው ግድብ ሙሌት ስኬታማ እንዲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ገንቢ ሚና መጫወታቸውን፤ ይህ ግዙፍ ግድብ ስኬታማ እንዲሆን $5 ቢሊየን ዶላር ያዋጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን፤ ግብጽ አሁንም ይህ ግድብ ያቋተው ግዙፍ ውሃ ወደፊት ድርቅ ሲከሰተ የአስዋንን ግድብ ለመሙላት ከሕዳሴ ኃይቅ ውሃ ቋት ልቀቁልን ብላ የምትከራከር መሆኑንና ኢትዮጵያ ሌሎች ግድቦች በተለይ የመስኖ እርሻን ለሚያስፋፋ ግድቦች መሰናክል እንደምትሆን ይገነዘብ ይሆን? መልሱን እራሱ ይናገር።

ባጭሩ መንግሥት ቢቀያየርም እንኳን፤ የሕዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሃውልት ነው። ከአብይ መንግሥት በላይ ነው፤ ከአቢይ ጋር ሊያያዝ አይችልም። ይያያዛል ብሎ መተቸት ከድንቁርና በላይ ድንቁርና ነው።

ይህንን ትችት ከመጻፌ በፊት በተደጋጋሚ ሃብታሙ አያሌው የተናገረውን ሺሙጥና ክስ እንዲስብ ጠይቄው እንደ ነበረ ልታውቁት ይገባል። ጓደኞቸም እንደ ጠየቁት አምናለሁ።

በራስህ ሜድያ አቅርበኝና ሃቁን ልናገር ብየው እሺ ካለ በኋላ ቃሉን አላከበረም። እኔ በሱ ሜድያ ብቀርብ ይህንንና ሌሎች ጉዳዮችን አነሳ ነበር።

የ360 ሜድያን ፕላትፎርም ተጠቅሞ ምንም በማያውቀው ጉዳይ የሰውን ስም መዝለፍ፤ መተቸት፤ መክሰስና ማሺሟጠጥ በሃልፊነት ያስጠይቃል። የሜድያውንም ተአመኔታ ወደ ጥርጣሬ ሊያሸጋግር ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያን እናድን::

የሃብታሙ አያሊው ሽሙጥና ስም ማጥፋት እኔ ቀን ከሌት ለምታገልለት፤ ለምሟገትለት፤ እውቀቴን፤ ልምዴን፤ ገንዘቤን ፈሰስ ለማደርግለት ለአማራው ሕዝብ የኢምንት ያህል አስተዋጾ አያደርግም። እኔም የሱን ትችት ምክንያት አድርጌ ከቆሙኩለትን አላማ ፍንክች አልልም። የአማራው ጉዳይ ከ360 በላይ ነው።

የሚታዘበውና የሚፈርደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ በተለይ አማራው።

ሜድያዎችንና ታዳሚዎችን አደራ የምልው በአማራው ሕዝብ ስም አማራውን አትከፋፍሉት። አማራውን ጠላት አታብዙበት። አማራውን እንደኔ በግልጽ ሆነ ወይንም በህቡእ የሚደግፉትን ግለሰቦች፤ ባለ ኃብቶች፤ ምሁራንና ሌሎች አትዘለፉ። አማራው ወዳጂ እንጂ ተጨማሪ ጠላት አይፈልግም።

ፈረንጅዎች አለማወቅን ማወቅ ራሱ እውቀት ነው ይላሉ። ሃብታሙ አያሌው አለማወቁን አያውቅም። እኔ ብቻ አውቃለሁ የሚለው የአብይ ግትርነት አገርና ሕዝብን ዋጋ እያስከፈለ ነው። ይሄ ተመሳሳይ ችግር የተለያዩ ሀሳቦችን ማስተናገድ ወዳለበት የሀሳብ ገበያ መሆን የሚገባው የሚዲያ መድረክ፤ በግለሰቦች አዛዥነት፤ ታዛዥነት፤ ዳኝነትና የውስጥ አጀንዳ የሚከሰት ከሆነ ጥፋት ያመጣል፡፡ ትግሉን ከመጥቀም ይልቅ ለአማራ ሕዝብ ጠለፋን በማመቻቸት፤ ተጨማሪ ጠላት እያመጣ፤ እርስ በእርስ መደማመጥ እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

በመጨረሻ፤ በግልጽ መናገር እንዲሚቻለው ይህ ስም የማጥፋት መንገድ ጨርሶ የአማርን ሕዝብም ሆነ ትግሉን አይጠቅምም፡፡

የአማራው የፍትህ ትግል ይለመልማል!!!

ዘረኝነት ይውደም!!!

September 19, 2023

https://youtu.be/LIqGVHG_hls?si=9xP9R8GcmHDiIwV6

 

13 Comments

 1. This is a good response. If there is any hidden agenda Habtamu knows let him come out and defend himself. I didn’t like it when he called your name in the Media and it is not fair he is not giving you the platform in the media to respond for his allegation. For that matter not all professionals who are currently working for the government should be demonized let alone those outside the government. We should point out faults based on fact.

  • ሀብታሙ ዶር አክሎግን ቀደም ብሎ መጠየቅ በተገባው ነበር ስልጣንም ሆነ ገንዘብም የሚፈልጉ አይመስሉም እንደ ልጅ ነገርን አያገናዝብም በሙያ ጓደኞቹም ፍሬን እንዲይዝ ሊመከር ይገባዋል። ታማኝ በየነ የሚሉትም አንደኛው ትኩረት ፈላጊና ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን እዳ ሰው ነው።

   • ሙራድ፦
    በዚህ ድረ ገጽ ላይ ብዙ ታዋቂ ሀያሲያን መጣጥፎች ውስጥ በማያስፈልግ አግባብ፣ ያለቦታው፣ መባል የማይገባውን ሆን ብለህ ይሁን ተልእኮ አንግበህ ነገሮችን ወደ አልተፈለገበት ለመቀየር እይተውተረተርክ ነው፡፤ የምታተርፈው ድካምና “ሀፍረት አይሰማህ ይሆናል እንጅ ሀፍረትን ብቻ ነው፡፡ ሀሳብ በሀሳብ ፣በማስረጃ፣ አስተማሪ በሆነ መንገድ ይተቻል ይሞገታል እንጅ ዘሎ ቁብ በስድብ??
    ሀብታሙን ከታማኝ ጋር???
    አይጠቅምምና ይቅርብህ፡፡

 2. Well, as a matter of the right to respond to not only what Habtamu Ayalew but also to what any person of critique says and defending oneself, the responder’s (Dr. Aklog’s) respond makes sense.

  However;
  . as a matter of a very clear and bitter reality of how he (the Dr.) understood the very terribly messy and disastrously ugly political situation of the country and the way he behaved towards the so called political reform of Abiy and his evil guided or evil- minded ruing circle was a terrible political stupidity and moral degradation , to say the least. I know some people may see this clear and direct comment of mine as an insult or down grading peoples’ intellect. My response will be as long as the comment is about political and moral standards of individuals in the very discourse of the socio- politics of the country , not about personal affairs , so be it !
  Yes, calling a spade a spade based on the very facts of what a spade looks like and what it does is the right thing to do if we have to get out of the age old and horrible crisis of intellectualism !
  Needless to say that it was and is individuals who allowed and keep allowing themselves to remain victims of dangerous opportunism and cynicism made the very essence and meaning of intellectualism nothing but terribly weak if not good for nothing .
  Yes, allowing one’s very valuable property ( intellect /knowledge ) to be the very instrument of ruthless ruling elites and political elites is not only a matter of damaging but also killing the generation .
  Was it not vividly clear to witness people like Dr. Aklog putting themselves in a very messy and dangerous political and moral quagmire by being the playing cards of very mischievous and idiotic political game of Abiy’s “medemer” and trying to mislead (fool) the people at large?

  These guys who allowed themselves to be the playing cards of the very cynical, conspiratorial , hypocritical , dishonest, extremely misleading, terribly ruthless , etc head of government and so called Prosperity Party that is the most deadly politics of ethno- centered cannot and should not go without being challenged ! Not at all!
  The guys such as Dr Aklog have been writing and crying about external powers as if Abiy and his ruling circle were and are not at the very forefront of responsibility and accountability. They have been writing and talking about the politics of the Horn of Africa and so and so forth where as the most dangerous threat for the very existence of the people in general and the Amharas in particular for five solid years !
  Is this not the very tragic situation as far as the very essence and purpose of intellectualism is concerned ?
  The Dr. tries hard to use the Dam as his “wonderful and legitimate “ appearances and dancing tail waging dances with those officials and cadres of the very butcher political system of ethno-centrism .
  It is deeply disturbing to hear those terribly failed educated people of ours arguing that the untold sufferings and destruction of humanity created in the very image of God is okay as as long as those butchers and destroyers build a great Dam !!! Terribly idiotic !!!
  They have no any sense that if this generation is able to get rid of the unbelievably criminal political system of Abiy Ahmed and his self- dehumanized cadres including the so called ambassadors , there is no doubt that it can make miraculous developmental works and projects let alone a single Dam . Arguing that I or we support the butcher for the simple reason of having a Dam is extremely idiotic and deadly !
  The other point is that guys like Dr Aklog do not even have the moral and intellectual gut to regret and say sorry for the terrible mistake they did!
  Sad and sad and dad !

 3. ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፦ አሁንም ምንጊዜም እናከብርወታለን፡፡
  በማንኛውም መመዘኛ በዚህ ቀውጢ ወቅት እብዱ፣ የአእምሮ በሽተኛው ወፍዘራሹና አሻራ የለሹ፣ ከስልጣኑ ይልቅ አንድ ሽህ ሳይሆን 30 ሚሊዮን ህዝብ ቢሞት ግድ በማይሰጠው በአብይ አህመድና በእርሱ አገዛዝ ውስጥ በሚደረግ በማንኛውም ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ በህዝብ አይንና በህዝብ እይታ አገር አጥፊውን ስርአት መተባበር ነው፡፤ ወንጀል ነው፡፤ ስርአቱን ለመጣል በሚዋደቀው ህዝብ ደም መሳለቅ ነው፡፡
  የህዳሴ ግድቡን በሚመለከት ለማስተማር የሄዱበት ርቀት ግጥም ቢጨምሩበትም ከከብት እረኞቹ የተሻለ አያደርግወትም፡፡ ሀብታሙ አያሌውም ሆነ የኢትዮ 360 አዘጋጆችና ሚሊዮኖች ታዳሚወች ይህንን ጠንቅቀን እናውቃለንና፡፡
  ስለዚህ ሀብታሙ አያሌዉና የሚሊዮኖች አንቂ ደወልና የትክክለኛ መረጃ ምንጭ የሆነው ኢትዮ 360 ሜድያ ከብርጌድ ጦር፣ ከክፍለ ጦርና ከእዝ በላይ የገዳዩን የአብይ አህመድ አገዛዝ እየተዋጋ ያለ የብዙ ሚሊዮኖች ሜድያ እንጅ እርሰዎ እንደሚሉት የሀብታሙ አያሌው መፈንጫ ወይንም ዘረኝነት መናገሪያ፣ ሰው መክፋፋያ ሜድያ አይደለም፡፡
  ንገረኝም ካሉኝ በእኔ ግምትና እይታ ሀብታሙ አያሌው አንቱ የሚያሰኝ የጋዜጠኝነት ሙያ ያለው፣ታማኝና ትኩስ መረጃወችን መሰረት አድርጎ የመተንተን ብቃት ያለው ጀግና ጋዜጠኛ ነው፡፡ ከትንተና ብቃቱ ጋር መረጃን ተንተርሶ ለማስረዳት የማይቸገር ፍርሀት የሌለበት ምጡቅ ነው፡፡ እንሳሳለታለን፡፡ ያለቅንጣት ማጋነን እርሱን ኢትዮ 360 ላይ በማገኘታችን እድለኞች ነን፡፡
  አንድ ነገርን ከእርሰዎ ምክር ልውሰድ፦ የአማራው ትግል ወዳጆችን ለማብዛት ማንም ጋር “”መዋዛት”” አለበት፡፡ ምሳሌ፦ ትግሉን የጎዱና የስርአቱ አገልግሎት ውስጥ ሚና የነበራቸውን እንደ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዮሀንስ ቧያለው፣ ክርስቲያን ታደለና…..ወዘተረፈ መሰሎቹን ማቅረብ እየፈተሹም ወደትግሉ በሂደት ማቀላቀል ያስፈልጋል፡፤ በዚህ ልክ ነዎት፡፡ ነገር ግን እርሰዎ እንዳሉት ለትግሉ ገንዘብ ይርዱ/ ሀሳብ ይሰንዝሩ አወቅን እንበል፡፤ እናስ??? እርሰወንና ሀብታሙ አያሌውን ለማወዳደር ባንፈልግም ኢትዮ 360 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አታጋይ ሜድያ ስለሆነ እንደ አይን ብሌናችን እንደምንጠብቀው እንዲያውቁልን እንፈልጋለን፡፡
  በሙሉ አቅሙ ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለውና ተወዳጁ የሁላችን የሆነው የዘሀበሻ ድረ ገጽም ሰሞኑን የብዙ በማር የተለወሱ ዩቲዩበሮችና የዲያስፖራ ፋኖ መሪ ለመሆን የሚቃጣቸውን በውጭ አገራት ቁጭ ብለው ከነእድፋቸው እየሞተ ያለው ብአዴን ተላላኪ ሆነው አመራር ለመስጠት ተደራጀን የሚሉ ታጋይ አታጋዮች “”ፋኖወች ነን”” የፋኖ አመራር ሰጪወች ልንሆን ከሳምንት በፊት ነው የተደራጀን ነን”… ወዘተ ባዮች መፈንጫ ባይሆን ይመከራል፡፡
  የአማራ ህዝብ ትግል የትግሉ አመራርም በትግሉ ሜዳ መሬት ላይ ያለና በስትራቴጅ በትክክልና በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ የፋኖ ትግል አይጠለፍም፣ አይኮላሽም፡፡
  ዘሀበሻ ድረ ገጽ ፦ ይህችን አጭር አስተያየቴን ሳታወጣት ብትቀር ያስተዛዝባል!!!

 4. ለዶ/ር አክሎግ ያለኝ አክብሮት እንደተጠበቀ ሆኖ በእኔ እይታ ስህተታቸውን አለማሳወቅ ስህተት ስለመሰለኝ ከጽህፋቸው መደምደሚያ ጀምሬ የኋሊት አጭር አስተያየቴን እንደሚከተለው አቅርቤያለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህንን የሀሳብ መድረክ ፈጥሮ እንዲንተነፍስ ላስቻለን ለዘሀበሻ ድረ ገጽ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፡፡
  ዶ/ር አክሎግ እንድያውቁት የሚገባው የአማራው ትግል የህልውና መሆኑን ነው፡፤ ፍትህ ድሞክራሲ ምናምን .. ከመኖር መቻል በኋላ የሚመጡ ናቸው፡፤ እውነታውን ያለመረዳት ስህተታቸው ከዚሁ ይጀምራል፡፡
  ዶ/ር አክሎግ ሀብታሙ አያሌው አለማወቁን አያውቅም ብለዋል፡፡ዶ/ር አክሎግ እርሰዎ አለማወቅዎን ያውቃሉን?
  ሀብታሙ አይሌውኮ በሀሜት ወይንም በድብቅ ሳይሆን ፊት ለፊት ወጥቶ ነው የእርሰዎንም ጉድ የዘረገፈው፡፤ እርሰዎም ጉድዎን አልካዱም፡፤
  ጉዱ ምንድን ነው ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ጉዱ ጉድ ከሆነ ይህንን ይመስላል፡፡ በዶ/ር አክሎግ ቢራራ ደረጃም ሆነ ሌላ ሰማንኛውም ሰው የአብይ አህመድን ስርአትና የጭፍጨፋ አገዛዝ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፍ የሚያስቀጥል ስብሰባና ዝግጅት ላይ በማንኛውም መልኩ መሳትፉ የለበትም የሚል ነው፡፡ ዶ/ር አክሎግ ይህንን ማድረጋቸውን አልካዱም፡፤ ሀብታሙ አያሌውም ይህ ስህተት መሆኑን ነው የዘገበው፡፤ የጉዳዩ መሰረታዊ መነሾም ይህ ነው፡፡ ህዝቡ ፍርዱን ይስጥ፡፡ አኛ ሚሊዮኖች የ360 ደጋፊወችና ታዳሚወች ሀብታሙ አያሌውን ደግፈን ቆመናል፡፡
  ዶ/ር አክሎግ የተሰብሰብኩት በግንባር ሳይሆን ‘በዙም” ነው ብለዋል፡፡ ስብሰባ ስብሰባ ነው፡፡ዶር አክሎግ አሁንም ሳያፍሩ ከጠሩኝ እገኛለሁ ብለዋል፡፡
  ዶር አክሎግ፦ ይህንኑ አቋምዎን አሳውቀው ሀብታሙ አያሌው ታዲያ ምን ብሎ ነው በ360 ሜድያ ላይ ቀርበው ይህንኑ አጠናክረው እንዲናገሩ የሚጋብዘወት?? ኢትዮ 360 ሜድያኮ ባለቤት አለው፡፤ እኛ ሚሊዮኖች ነን ባለቤቶቹ፡፡ ያቋቋምነውም እኛው ሚሊዮኖቹ ደጋፊወቹ ነን፡፡ እርስዎ ይህንን አይነት አቋም ይዘው ይህንኑ ለመስማት በኢትዮ 360 ላይ እንዲቀርቡ አንፈቅድም፡፡ አሰራር አለንኮ፡፡ ከፈለጉ እንደለመዱት መሳይ መኮንን አንከር ሜድያ ጋር ድጋሜ ሄደው የሚፈልጉትን ይበሉ፡፡
  ዶ/ር አክሎግ የሀብታሙ አያሌውን ሀጢኦቶች ሲዘረዝሩ የባለሀብቱን የአቶ ወርቁ አይተነውንና የሌሎች አማራወች ጭምር ስም አጥፊ ነው ያሉበት ጉዳይ አግባብም እውነትም አይደለም፡፡አቶ ወርቁ አይተነው በአማራ ክልል የአብይ አህመድን አዲሱን ምርኩዝ አቶ አረጋ ከበደን በሚመለከት “’የእኛ ሰው ስለሆነ አትንኩት”” ያለበትን ጉዳይ አንስቶ ነው ስለአቶ ወርቁ አይተነው ፊት ለፊት ይህንኑ በይፋ የተናገረው፡፡ አዲሱ የአማራ ክልል መሪ አቶ አረጋ ከበደ የእርሰዎም ሰው ናቸውን??
  የአማራው ትግል ገንዘብ በመስጠት ወይንም ደጋፊ አስተያየቶችን በመሰንዘር የሚሸነገል አይደለም፡፤ የህልውና ትግል ነው፡፡አሁንስ ገባዎትን???
  ዶ/ር አክሎግ ስለግድቡ ሙሌት ሲጽፉ ልጥቀስ፡ ” አራተኛው የግድቡ ሙሌት ስኬታማ እንዲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ገንቢ ሚና መጫወታቸውን ሀብታሙ አያሌው አያውቅም ብለዋል፡፡ ሰይጣን እንዳይሰማዎ!!!
  ግድቡ ስንት ተርባይኖች እንዲኖረው ታቅዶ ስንት ተርባይኖች አሁን ላይ እንዲኖሩት ተደረገ?? በግድቡ ላይ ባለፉት 12 አመታት ውስጥ በተለይም አብይ አህመድ ስልጣን ከመያዙ በፊት በነበሩት 7 አመታትና ከዚያ ወድህም ባለፉት 5 አመታት ምን ታቅዶ ምን ተፈጸመ?? ይህ መሬት ላይ ያለ ሀቅ እውን ሆኖ እያለ ዶ/ር አክሎግ ብለው የአብይ አህመድ “ገንቢ ሚና” እያሉ ለመግልጽ ምን ብድግ ቁጭ አደረገዎ??
  በመጨረሳም ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ሊያስታውሱት እንደሚችሉ የምገምተው የ60ወቹ ትውልድ በዚያ ጊዜ ብዙ መበላላቶችን አሳልፏል፡፤ ያኔም ጥቂት ፖለቲከኛ ዶክተሮች ነበሩ፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስም ያህል ሀይሌ ፊዳና ዶ/ር ነገደ ጎበዜ መኢሶንንን ወክለው ዶር ሰናይ ልኬ ወዝ ሊግን ወክለው ወደቀኝና ወደግራ ሲሳሳቡ ደርግ የሚሰራውን ሰርቶ ሁሉንም ጭው አደረጋቸው፡፡
  ዶር አክሎግ፦ ወደህሊናዎ ይመለሱና ያደረጉት የዙም ትሳትፎና በይበልጥም የአብይ አህመድን ገንቢ ሚና አጉልተው መግለጽዎ ስህተት መሆኑን ይረዱ፡፡
  አበቃሁ፡፡

 5. አይ ዶክተር አክሎግ! ያልተገታ ምላስ አሉና እርስዎም የመለስን ቃል “ሕዳሴ ግድብን” እንደ አዝማች በመጠቀም ነቀፋዎትን አዥጎደጎዱት፡፡ እንግዲህ የወቀሱት ሰውም አጠፋ ይመልሳል፡፡ መቼ ሊቆም ነው?

  በሕዳሴ ግድብ እያሳበቡ አምስት ዓመት ሙሉ ሰው በላውንና አረመኔውን ሰይጣን ይጥራውና አብይን ደገፉ፡፡ እርስዎ እኮ ተስምንተኛ ክፍል ያልዘለለው ጆሮ ጠቢ “ለመጀምርያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሬ እምለው ሰው አገኘሁ!” ብለው እስተሚሰግዱ ያንከረፈፍዎ ሰው ነዎት፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሐብቴም በልጦብዎት ማለት ነው፡፡ ብዙ ጉድለት ሊኖርበት ቢችልም ሐብታሙ ግን እንደ እርስዎ በአደባባይ ለዚህ ሰይጣን አልሰገደም፡፡

  እኔ እምልዎት ተፖለቲካ ጡረታ የሚወጡ መቼ ነው? ከመኢሶን እስክ ፒፒ!

  በአባይ ግድብ እያሳበቡ ተአብይ ባለልስኖች ጋር ኢምባሲ ጉብ ብለው የሚውሉት አማራን በተረጠበው ድሮን ለሚጨፈጭፈው ለአብይ ሰይጣናዊ አገዛዝ እውቅና በመስጠት ነው? አማራን በድሮን የሚጨፈጭፈው በኢምፓሲ ሰራተኞች በኩል ገንዘብ እየተረጠበ መሆኑን ይህ ከስምዎ ግርጌ የሚለጥፉት ፒ ኤች ዲግሪ አይነግርዎትምን? በስመ አብ!

 6. Bekele ሃብታሙ ነህ በቃ ነገር አብርድ ሰው አልወደደልህም አሽሙርም ይቅርብህ ከነምናላካቸውም መስከንን ማገናዘብን ተማር እሳቸው ላይ ሾተላህን ካነሳህ ማን ይቀርሃል ነገ ደግሞ ፋኖ ላይ ትዘምትበታለህ ስትናገር በማስተዋል እና በእውቀት ይሁን ይህን ብሽሽቅ ተወው፡፡ ሁሉንም እኔ ልስራው አትበል እንደ አብይ ሳንፈልግ በኛው መሃል እንዲህ አታናግሩን ቢበዛብን ነው፡፡ ይነበብ መዝገቡ አንተም ሃብታሙ ልትሆን ትችላለህ ዶር አክሎግ ያሉት የህዳሴ ግድብ ከመሪዎች በላይ ነው መሪዎች ይሄዳሉ ይመጣሉ ይህ ግ ን የኢትዮጵያ ሃውልት ነው በተለየ መልኩ ነው የማየው ነው ያሉት፡፡ 5 ቢሊየን ዶላር የፈጀውን የህዝብ ንብረት አብይን ያቆስልኛልና ግብጽ መጥታ ታደባየው ልትሉን ነው፡፡ አባይ ተስፋችን ነው ግብጽ ጦር ይዞ ቢመጣ አብይ ይወገዳልይ ግድቡን ትምታው ልትሉን ነው? ይሄ ትግሬያዊና ሻቢያዊ አካሄድ ነው አስተካክሉት ሁሉን አትንከሱ፡፡

 7. ዙቤዳ፦
  በቀለንም ሀብታሙንም ይነበብ የተባለውንም ሶስቱንም አስተያየት ሰጪወች በአንድ ወንጭፍ ክንፋቸውን መታሻቸው አይደል፡፡ ጎበዝ!!
  አንቺ በአለቃሽ፣ በቀጣሪሽና በደመወዝ ከፋይሽ በአውሬው አብይ አህመድ የዘመኑ አገላለጽ “ጀግኒት ነሽ”‘፡፡ ምናልባትም ይህንን ያሰብሽውና እንዲትጽፊም የተደረግሽው ከዝናሽ ታያቸው ኩሽና ውስጥ ሆነሽሊሆን ይችላልና ናኚበት፡፡
  የጽሁፍሽ ይዘት ጭፍን ያለ አድርባይነት ነው፡፤ ትንሽ እንኳን ማስመሰል አልቻልሽበትም፡፡
  ብስለት ካለሽ አይሆንም እንጅ ‘የሚሊዮኖች ህይወት በተረኞች እየታረደ ከሚጠፋ 5 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል ያልሽው ግድብ ድርግም ብሎ ይጥፋ’ ብለሽ ታስቢ ነበር፡፡ ግን ህይወት የሚሊዮኖች ህይወት ማጥፋቱም በቅርቡ በፋኖ ድል አድራጊነት ይቆማል፡፡ ግድቡንም ህዝቡ በኦሮሙማ እየተመቻቸ ካለው ስልቀጣ አውጥቶ ሲጀመር ለታቀደለት ለአገር ልማት ያውለዋል፡፤ አዲሱ የአገሪቱ ሀይል ከማንም ጥቃትም ይከላከለዋል፡፡ በነገራችን ላይ የግድቡ ባለውለታ ለግድቡ ያዋጡት መላው ኢትዮጵያዊያንና የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጠው መናጢው ነገር ግን ከአብይ አህመድ አንድ ሽህ ጊዜ የሚሻለው አቶ መለስ ዜናዊ እንጅ አብይ አህመድ አይደለም፡፡ አብይ አህመድ አሊ ምኑም ውስጥ የለበትም፡፤ እንዲያውም ለግድቡ ስኬት መሰናክል የሆነባቸው ዝርዝር ጉዳዮች በማስረጃ ተሰድረው ስለታያዙ ወድፊት ይገለጻሉ፡፡
  ስለግድቡ የአብይ አህመድ ጉዶች ውስጥ አንዷን ብቻ ልጥቀስልሽ፡፡ ለምን የተርባይኖቹ ቁጥር ዝቅ ተደረገ?? ነገሩ አንቺ ይህ መሰሉ ነገር አይገባሽምና አትጨነቂ ተይው፡፡
  ስለግድቡ ሌላውን የአብይ ጉድ ላሳንልሽና ከገባሽ ለመረዳት ሞክሪ፡፡ አለቃሽ አብይ አህመድ ግብጽ ፓርላማ ፊት ቀርቦ ወላሂ ወላሂ እያለ ቁርአን ቀርቦለት እየማለ ምን ብሎ ነው ለግብጾች መሀላ የፈጸመው?? ይህንንስ ታውቂ ነበርን?? ትረጅስ ነበር፡፤ ዳሩ ግን ያን ጊዜ ያሁኗ ዙቤዳ አልነበርሽምና ይህንንም ተይው፡፡ አትጨነቂ፡፡
  እውነቱን ልግለጽልሽ፡፡ አመንሽም አላመንሽም ሀብታሙ አያሌው እንደዚህ አይነት ትርክርክ ነገር ውስጥ አይገባም፡፡ በሳል አናሊስት ነው፡፡
  በእውንም እኛ (የኢትዮ 360 ደጋፊወች) እንፈልግ የነበረው ሀብታሙ አያሌው አቶ አክሎግ ቢራራን በኢትዮ 360 ሜድያ ላይ እንዲያቀርባቸው ነበር፡፤ ነገር ግን አቶ አክሎግ ቀድመው “” እምባሲው ድጋሜ ቢጠራኝም ድጋሜ እሰበሰባለሁ”” ስላሉ ይህም ድርጊታቸው ከፋሽስት ስርአት ጋር መስራትና በሚጨፈጨፉት ወገኖቻችን ሬሳ ላይ መረማመድ መሆኑን ስለምናምንበት ይህንኑ አቋማቸውን ከእርሳቸው ለመስማት ድጋሜ እርሳቸውን ኢትዮ 360 ላይ የማቅረቡን ሀሳባችንን አንስተናል፡፡
  ይህንንም የምንለው እኛ ሚሊዮኖቹ የኢትዮ 360 ደጋፊወችና የአብይ አህመድ ተቃዋሚወች ነን፡፡ አሁንስ ገባሽ ወይንስ አሁንም እዚያው በሻሻ ነሽ ??
  አብይ አህመድ በማንኛውም መንገድ ቢወገድ ለአገሪቱ መፍትሄ ነው፡፡ እኔም ፋኖ ነኝ፡፡ ሀብታሙ አያሌውም ፋኖ ነው፡፤

  • ዚነት መልካም ለአቅመ ማሰብ የደረስክ ስላልመሰለኝ ያልጠራውን ሃሳብህን ተከትሎ አስተያየትም ሆነ መልስ መስጠት አስፈላጊ ሁኖ አላገኘሁትም በነዚህ ታላላቅ ሰዎች የሚጻፈው ሃሳብንም የመትረዳ አይመስለኝም፡፡ መልካም አመት በአል

 8. Well, it is the right thing to say that we need to make our comments focused on what the Dr. tried to argue and behave towards the very criminal political system which people are terribly languishing in.

  Trying to defend the Dr who is one of those who claim themselves as intellectuals but horribly failed to show the very essence and meaning of intellectualism which is of course a means or an instrument used to fight against both natural and political catastrophes .

  Yes, allying oneself with the very dishonest and brutal ruling elites who have gone to the extent of undertaking absolutely inhumane killings of innocent citizens and making so many millions dead alive and trying to use the Abay Dam as justification is absolutely a moral decay and political idiocy !!!

  Yes, trying to tell millions of parents and the innocent people at large that it is okay to lose their loved once as long as dams , roads, bridges, buildings , schools, etc are built or being built is not only political idiocy but also absolutely inhuman !!!

  That is why it is fair enough to say that the Dr needs sincere regret and apology for being part and parcel of a horrible political system and its orchestrators !!!

 9. The topic itself fits the political behavior of the writer very well, not the critique !

  It is the writer himself who is losing and damaging the very essence of intellect and intellectualism by allowing himself to be the participant of events or activities of highly conspiratorial and seriously criminal ruling elites and their parasitic partners !

  Is there any other very terribly undisciplined and uncontrolled political behavior than messing one’s own political and intellectual personality with that of criminal political system ?

  Is there any other type of intellectual crisis than arguing that it is okay to dance a tail waging dance with criminal ruling elites because they claim the construction of a big dam or any other project ?

  This absolutely idiotic and cruel as far as the untold sufferings of the innocent people are concerned !!!

 10. ዚነት ላንተ መልስ መስጠት ፈረንጆች unprofitable argument የሚሉት ነው እርግጠኛ ነኝ አንተም ሃብታሙ ልትሆን ትችላለህ፡፡ የዶ/ር አክሎግን ሪፖርት አንብበው የእኔም ጽሁፍን ይዘቱን ገምግመው ለዚህ ያልታደልክ ከሆንክ አኞ ማብሰል ነው ተወው ይመችህ ምን በወጣህ ታስባለህ አእምሮህ ሳይሆን ጣትህ ነው የሚያስብልህ በርትተህ ተሳደብ ያንተ አስተዋጽኦ ይሄ ነው ማለት ነው ብትችል ማይክ ይዘህ የዚህ አይነት ቋንቋ ተስቶህ ተናገረህ 360ን ታዘጋዋለህ፡፡ አንተ ጥሩ ሰው ልትሆን ትችላለህ የአርቆ ማሰብና ማገናዘብ እጥረት ሳይጎዳህ አልቀረም ይህ ደግሞ ቀደም ባለው እድሜህ ካልተስተካከል አሁን ይከብዳል፡፡ ሰላም ሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share