የአዲስ አበባ ዋና ከተማ እና የወልቃይት ደንበር የኢትዮጵያ እና የቀጠናው የወደፊት የህልውና መሠረት ናቸው

6yyyggff 1 1 1
#image_title

በዚህ አጭር ፅሁፍ ኢትዮጵያ ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ፣ ታሪክ ወ.ዘ.ተ. ወልቃይት ፣ ራያ እና አዲስ አበባ  ከተማ የመላ ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያ ፣ የመላ ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈባቸው ሃብቶች ፣ ቀየዎች ፣ የኢኮኖሚ መሰረቶች ወ.ዘ.ተ. መሆናቸው “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም” ካልሆነ በስተቀር ጠንቅቆ የሚታውቅ በመሆኑ  አጠር ያለ መርጃ ከመስጠት በስተቀር በዚህ ጉዳይ ላይ አታካራ ለመግጠም አይዳዳንም።

ግራ ነፈሰ ቀኝ ግን እንኳን አዲስ አበባ ይቅርና ነቀምትን ፣ አሩሲ አሰላን ፣ ባሌ ጎባን ፣ ድሬድዋን ፣ ጅጅጋን ፣ ሐረርን ፣ ጅማን ፣ አክሱምን ፣ መቱን ወዘተ መሰል የኢትዮጵያ ዋና ከተሞች የከተማነት ቁመና እንዲኖራቸው ያደረገው ‘የአማራ ሕዝብ” ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሕዝቦች ጋር ተርባርቦ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሃቅና እውነታ ነው።

በዚህ ፅሁፍ ግን የህውሃት ተስፋፊወች እና ኦነጋውያን ብልፅግናዎች እርስ በርስ ደም መፋሰሳቸውን ከዕቁብ ሳይቆጥሩ ፣ ወደ ጎን አርገው ፣ ከሁለት ሚሊየን በላይ የትግራይን ፣ የኦሮሞን፣ የአፋርን ፣ የአማራ እና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ለጋ ወጣቶች ደም አፍስሰው እና ይህ ሃገራዊ የጋራ ቁስል ሳይጠግግ ለምን አዲስ አበባን ተስፋፊ ኦሮሞዎች የኛ (ኬኛ) አሉ እና ስግብግቦቹ የህውሃት ቡድኖች ወልቃይት የግላችን (አነ እዩ) አሉ የሚለውን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ  ዐይኑ ፣ ልቡናው እና ውስጠ ህሊናው የነገሩን ውስጠ ወይራ ሚስጥር እና ሴራውን እንዲያውቀው እና ራሱን እንዲያዘጋጅ  ለማድረግ ነው ።

የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ከጎንደር ተሻግሮ አዲስ አበባ  ዋና ከተማ ተብላ ከመሰየሟ በፊት ጎንደር ላይ ሁነው ዐፄዎቹ ኢትዮጵያን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ማለትም    በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግስት በ1380 ዓ.ም. ፣ በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ከ1413ዓ.ም. -1468ዓ.ም. ፣ በዐፄ ንብለ ድንግል ከ1508ዓ.ም.-1540ዓ.ም. (የአዋሽ ወንዝን ፣ የዱከም ወንዝን ፣ ከየረር ተራራ የሚመነጨውን ወንዝ ይዞ) ፣ የዝቋላ ገዳም ፣ የአምባ ነገስት ተራራ እና በ1889 የእንጦጦ የዐፄ ሚኒሊክ እና የህትጌ ጣይቱን  ቤተ-መንግስት የሆነውን አካሎ “አዲስ አበባ” የሚል ስያሜ ከማግኘቱ በፊት  “በረራ” በሚል ስያሜ ያስተዳድሩት እንደነበር እውቅ ተመራማሪ የሆኑት እና ምሁራን ቁልጭ እርገው እስከማስረጃው ተንትነው አስቀምጠውታል።

ከእነዚህ ምሁራን መካከል እነ ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ሀርትዌቲግ ብራትረት፣ ሳሙሄል ወከር፣ ማርኮ ቬጋኖ እና ጣሊያናዊው የመሬት ካርታ ተመራማሪ ፍራ ማወር በማያወላዳ መልኩ ፣ ቁልጭ ባለ እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ አስቀምጠውታል።

የተባበሩት መንግስታትም

“Minilik II then formed his imperial palace in 1887.[9][10] Addis Ababa became the empire’s capital in 1889, and subsequently international embassies were opened.[11][12] Addis Ababa urban development began at the beginning of the 20th century, and without any preplanning.[8]”

ከላይ የተፃፈውን የተባበሩት መንግስታትን የምስክርነት ሃተታን ስናይ ዐፄ ሚኒሊክ ሁለተኛ በ1888 ዓ.ም. ቤተመንግስታቸውን ካስገነቡ በኋላ በ1989 ንግስናቸውን አፅንተው ከዚያም  በአዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ኢምባሲዎች አየተከፈቱ  የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የእድገት ፈርጥ እያስመዘገበች አሁን ካለችበት ደረጃ ደርሳለች ብለው መስክረውል።

ከሚኒሊክ ስርወ መንግስት በፊት ዐፄ ቲዌድሮስ ዋና ከተማቸው ጎንደር ላይ ቢሆንም ሸዋን አካተው  ያስተዳድሩ ስለ ነበር አዲስ አበባን ፣ ደቡብን ክፍል ፣ ምስራቁን ፣ ሰሜኑን እና ምዕራቡን ከኦሮሞ ወረራ ነፃ በማድረግ የአባቶቻቸውን ፈር  ተከትለው ያስተዳድሩ እንደነበር በግልፅ የሚታወቅ ነው።

 

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የመሆኗን እውነታ የአፍሪካ አድነት ድርጅት /OAU/ ፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ ፣ መላ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሆነ በአዲስ አበባ የተሰየሙ ኢምባሲዎች የሚመሰክሩት እውነታ ነው።

 

የወልቃይት መሬት ከተከዜ ወዲህ የአማራው እና የጎንደሬው ዐፅመ እርስት መሆኑን በ1424 በመፅሃፈ አክሱም ፣ በ1520 -1527 በፖርቺጋላዊው በኤፍ አልፈሬዝ ፣ በ1833 በሬቨረንድ ማይክል ራስል ፣ በስቲቨን ሮቢንሰን ፣ በዘመነ መሳፍንት በ18ኛው ክፍለ ዘመን በስኮትላንዳዊው ጅምስ ብሩስ ፣ በጣሊያን ወረራ ወቅት “ጎንደሬ በጋሻው “ በሚል በጎንደሬው የስነ ፅሁፍ እና የታሪክ ልሂቅ በአቶ ገሪማ ታፈረ እና በጎንደሬዎ የሕግ ምሁሩ አባት አቶ ፍታየ አሰጉ በ2021 ባሳተሙት መፅሃፎቻቸው እና  የምርምር ፅሁፎች ወልቃይት ጠገዴ የአማራው እና የጎንደሬው ዕፅመ እርስት መሆናቸውን በማስረጃ አስረግጠው ከትበዋል።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት የማስረጃ ክትቦች ለመንደርደሪያ ተከተቡ እንጂ የዚህ  ፅሁፉ ዋና ዓላማ “አዲስ አበባ እና ወልቃይት” እነዚህ ሁሉ ማስረጃዎች እያሉ የትግራይ እና የኦሮሞ ተስፋፊዎች ለምን እነዚህን የኢትዮጵያዊያን ጉሮሮ እና የጀርባ አጥንት የሆኑትን ለም መሬቶች ፣ ከተሞች ሊሰለቀጡ ፈለጉ የሚለውን ለማስረዳት ነው። ይህ እኩይ ዓላማቸውን ተግባራዊ ሊያደርጉ ተፍ ፣ ተፍ የሚሉት በሚከተሉት ዋና ምክንያቶች ነው ፣

  • በመጀመሪያው  አማራ እና ኦርቶዶክስ ጠል የሆኑት የምዕራብያውያንን ተልእኮ ለማስፈፀም ይቻላቸው ዘንድ የህውሃት ተስፋፊዎች ወልቃይትን በመውረር እንዲሁም አማራ ጠል የሆነው የኦነግ ጥምቅ  የኦሮሞ ብልፅግና ደግሞ የኢኮኖሚ ፣ የዲፕሎማሲ እና አማራ የመሰራታትን አዲስ አበባን ወደ ጉያቸው በማስገባት ያነገቡትን እኩይ ዓላማ እውን ለማድረግ ይቻላቸው ዘንድ ይህ አካሄዳችን ወሳኝ እና የሚያዋጣ ስልት ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው፣
  • ወልቃይት የታመቀ የተፈጥሮ ሃብት ማለትም እንደ ዕጣን ፣ ሙጫ ፣ ዕምቅ የከርሰ ምድር ወ.ዘ ተ. ክምችት ያለው ምድር በመሆኑ ፣
  •  በእርሻው ደግሞ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ እንደ ጥጥ ፣ ሰሊጥ ፣ ለውዝ ፣ የሱፍ ምርት ወ.ዘ.ተ የወልቃይት መሬት ስለሚያበቅል ይህ ዕምቅ ሃብት በመቆጣጠር እና በመውረር የኢኮኖሚ ችግራችንን እንፈታልን ፣ ድህነትንም እስከወዲያኛው ቀርፈን አካባቢያችንን ከላቀ ደረጃ ላይ እናደርሳለን ብለው ስለሚያስቡ ፣
  • ከኢትዮጵያ የታሪክ ጠላቶች እንደ ግብፅ እና አክራሪ ሱዳኖች ካሉ ሃገሮች ጋር በደንምበር ተገናኝተው አፍቅሮተ ኢትዮጵያ እና በሃይማኖቱ ቀናይ የሆነውን የአማራ እና የሌሎች ሕዝቦችን ተነሳሽነት እና የአንድነት ትብህላቸውን በኃይል ለመደፍጠጥ፣
  • በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ዙሪያ ከምዕራባዊያን ጋር ተመሳጠረው ተገዳዳሪ የሆነ ፅንፍ የረገጠ ኃያል ያለው ቡድን ለመፍጠር ፣
  • የኦነግ ፅንፈኛ የኦሮሞ ብልፅግናዎች እንደ ቤንሻንጉል ፣ ጋምቤላ ያሉ ክልሎችን በኃይል ደፍጥጠው በመያዝ እና በመውረር በ1500 ኪሎ ሜትር ከሚርቋቸው እና በዘር ግንድ በፍፁም ከማይገናኟቸው ኢትዮጵያ ጠል እና ሃገር አጥፊ ቡድን  ህውሃት ጋር በመመሳጠር እና በመቧደን በትርክት ብቻ ጨቁኖኗል ብለው የሚያስቡትን አማራ በጋራ ለማጥፋት ፣ ከዚያም አልፈው ሃገረ ኢትዮጵያን ድምጥማጧን ለማውጣት እና የያዙትን የዓላማ ትስስር እና ህሳቤ እውን ለማድረግ ይቻለናል በሚል ስሌት ወልቃይትን ለትግራይ ተስፋፊዎች  ፣ አዲስ አበባን የኦሮሞ ፅንፈኞች በመቆጣጠር እና በመውረር ፣ ለመዝረፍ እና ለመቀራመጥ ስላሰቡ፣
  • በኢትዮጵያ ደም ፣ አጥንት እና ገንዘብ የተገነባውን እነሱ “የህዳሴ ግድብ” የሚሉትን “የአባይ ግድብ” ከመላው የኢትዮጵያዊ እና ከአማራ የተፈጥሮ ባለቤትነት ፈልቅቀው በማውጣት የሁለቱ አሸባሪ እና ተስፋፊ ቡድኖች የህውሃት እና የኦነግ ብልፅግና   የጋራ ሃብታቸው ለማድረግ ስላሰቡ ፣
  • ይህን ሁሉ ጥምጥም ሴራ ሞክረው አማራውን እና ሌላውን ብሔር ብሔረሰብ ማበርከክ ካልቻሉ ወልቃይትን እና ራያን የትግራይ ህወሃት በማድረግ ፣ አዲስ አበባን የኦነጋዊው የብልፅግና ክንፍ አርገው በመቆጣጠር የመገንጠል ህሳቤያቸውን ባፀደቁት የሕገ መንግስት አንቀፅ -39 መሰረት ለመከውን ወደ ኋላ እንድማይሉ መላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ሊረዳው የግድ ይላል እንላለን።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባው ዋናው ጉዳይ ወልቃይት በትግራይ ተስፋፊዎች ቁጥጥር ስር ከዋለ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከጎረቤት ሃገራት ጋር የነበራቸው የንግድ ፣ የማህበራዊ ፣ የኢኮኖሚ ወ.ዘ.ተ. ግንኙነት ያልቅለታል ።

ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እራሷን ለመከላከል መነሻ ድንበር አጥታ የትግራይ እና የኦሮሞ ቀኝ ተገዥ የምትሆንበት ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ።

የኢትዮጵያ ፣ የአማራና የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች  ህልውና ስጋት ላይ ይወድቃል።

አዲስ አበባ የኢኮኖሚ ፣ የዲፕሎማሲ ፣ የባህል ፣ የማህበራዊ ወዘተ የማስተሳሰሪያ ውል እንደመሆኗ በአንድ ቡድን ማለትም በኦነጉ የኦሮሞ ብልፅግና ስር ከወደቀች አማራን ጨምሮ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ሁለተኛ ዜጋ በመሆን የጭቆና ቀብር ላይ ለመውደቅ ይገደዳሉ።

ይሄም በመሆኑ የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ለበለጠ ትርምስ ፣ ጦርነት ፣ ያለመረጋጋት እና ለከፋ ድህነት  ሰለሚዳረጉ አዲሶቹ የምዕራቢያውያን የቀኝ አዙር ቀኝ ገዥዎች (Neocolonialists) ከኢትዮጵያን አልፎ አፍሪካዊያንን እንደፈለጉ ይመዘብራሉ ፣ ይቆጣጠራሉ ።

ስለዚህ አዲስ አበባ የሃገረ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና ወልቃይት ፣ ጠገዴ እና ራይ የእምየ ኢትዮጵያ ደንበር እና አጥር ሁነው እንዲቀጥሉ ታላቅ የጋራ ተጋድሎ ማድረግ የግድ የሚል ይሆናል።

የተወሰኑ ብሔር ብሔረሰቦች ሃብት እና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚደረገውን የግለኝነት እና የገብጋባነት ህሳቤ ፣ መባከን እና ጡዘት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊታገለው የግድ የሚል ይሆናል።

ከዚህ ባሻገር ወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ ጠለምት ፣ ራያ እና አዲስ አበባ  ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ቀጠና የወደፊት የህልውና መሠረት ፣ የጋራ ሃብት እና መገለጫ በመሆናቸው  የእናት ጡት ነካሾትን ሴራ እና ዱለታ በጋራ በመከላከካል  የኢትዮጵያ ሃብት እና አሻራ ሆነው ይቀጥሉ ዘንድ ጥርሳችንን ነክሰን ልንታገል የግድ ይላል ብለን በአፅንኦት እንመክራለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ  እንግሊዝ።

 

1 Comment

  1. ዳሩ እሳት መሀሉ እሳት፤ የብልፅግና ፖለቲካ ርዕዮት የት ያደርሰን ይህን?!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

353413777 5907153302723573 1358624770594519522 n 1
Previous Story

ጋዜጠኞቹ መስከረም አበራና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ችሎት ለህዝብ ክፍት እንዲደረግ ታዘዘ

haile larebo
Next Story

ዐቢይ አሕመድ አሊ ለሥልጣን የበቃው በምርጫ ነው ወይ በቅርጫ (ኘሮፌሰር ኀይሌ ላሬ)

Go toTop