June 10, 2023
7 mins read

የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ-ማህበራት ጉባኤ (ኢሕማጉ) ለአማራ የኅልውና ትግል የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ

የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊማህበራት ጉባኤ (ኢሕማጉ)
Congress of Ethiopian Civic Associations (CECA)

 

ለአማራ ልውና ትግል የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ

 

በሕብረተስብ የእድገት ታሪክ ውስጥ የሰው ልጆች ክብራቸውንና ነፃነታቸውን ሙሉ በሙሉ ተገፈው ለከባድ ሥራ፤ እንግልት፤ ግርፋት፤ እሥራት፤ ግድያና ስደት ከተፈራረቀበት የባሪያ አገዛዝ ተብሎ ከሚጠራው ሥርዓት የከፋ ያለ አይመስልም። ዛሬ በአገራችን በአማራው ሕብረተስብ ላይ ግፈኛው የአቢይ ብልጽግና አገዛዝ በማድረስ ላይ ያለው አንድን ዘር ነጥሎ የጥቃት ዒላማ እንዲሆን ማድረግና የማጥፋት እርምጃ በትውልዳችን ከተከሰቱት ኢሰባዊ ድርጊቶች የሚተናነስ ሳይሆን የከፋ ነው።

አማራው የታወጀበትን የጥፋት ዘመቻ ለመመከትና ለአማራው ማንነት፤ ኅልውና፤ መብትና ፍትህ መከበር ብለው ከአማራው አብራክ የወጡ ልጆቹ (ፋኖ፤ የክልሉ ታጣቂ ሃይል) የሚያድርጓቸው  በሕዝባዊ እንቅስቃሴ የታጀበ ሁለገብ ትግል፤ እነሆ ከጀመረ ውሎ አድሯል። በመሆኑም የአማራው ህብረተሰብ ከሠላማዊው ሕዝባዊ ንቅናቄ ጀምሮ ተገዶ  እስከገባበት የትጥቅ ትግል ድረስ ኅልውናውን ለማስከበር የሚደረግ ሕጋዊ ትግል በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ባርነትንና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋውን የሚቃወሙ የዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ሙሉ ድጋፍ ሊሰጠው ይገባል ብለን እናምናለን።

የኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ-ማህበራት ጉባኤ (ኢሕማጉ) የተቋቋመው በኢትዮጵያዊያን ማዕቀፍ የተደራጁ የዲያስፖራ ሕዝባዊ ድርጅቶች በመተባበር ሀገራችን ከዘረኛና ፋሽሽታዊ አገዛዝ ተላቃ ፍትህ፤ እኩልነትና ብልጽግና የሰፈነባት ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚድረግ ሀገር በቀል ርብርብ አጋር ለመሆን ነው። በዚህ መሠረት በተለየ ታላቁና ትልቁ የአማራ ሕዝብ በወያኔና በኦነጋውያን የታወጀበትን ዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመቋቋም ከእልክ አስጨራሽ ትዕግስት በኋላ እያደረገ ያለውን አትንኩኝነትና እራስን የመከላከል ጥረት እንደምንደግፈው እንገልጻለን።

1ኛ) ብሶት  የወለደውን የአማራ የኅልውና ንቅናቄ በሙሉ ልብ እየደገፍን፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ የተጠነሰሰለትን ተመሳሳይ ጥቃት በተረኝነትና በግብዝነት መጠበቅን አቁ   ከአማራው ጋር እንዲሰለፍ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን።

2ኛ) በቅርቡ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር (Amhara Popular Front) መመሥረቱን በሰፊው የሕዝብ መገናኛዎች ሰምተናል፡፡ ይህ ታጋሽ ሕዝብ ያለ አጋር እስከመቸ እየተቀጠቀጠ ይኖራል የሚለውን ወቅታዊ መልስ የሰጠ በመሆኑ እንደ አውሬ ለሚታደነው ሕዝብ መታደጊያነቱ እንደ ምሥራች ሲሆን፤ በኛ እምነት ተጠያቂነትንና ጥራት ያለው ድርጅት እንዲገነባ ትልቅ ጉጉታችንና ምኞታችን እንደሆነ እንዲታወቅልን እንሻለን።

3ኛ) በሕዝብ እምቢተኝነትም ሆነ በትጥቅ ትግል ስልት የሚመሩ ሌሎች የዐማራ ስብስቦች እንዳሉም እንገነዘባለን።  ስለዚህ ባደባባይ የወጡትና በህቡዕ የሚንቀሳቀሱት የዐማራ ድርጅቶች ሁሉ  ቢያንስ እየተክባበሩና እየተናበቡ ቢቻል ደግሞ በአንድነት እንዲሰለፉ አበክረን እንማፀናቸዋለን። ፍኖተ ካርታ ነድፈው ዐማራነትንና ኢትዮጵያዊነትን አዋህደው እንዲንቀሳቀሱ ከመምከር አልፈን  ለትግሉ ስኬት የተቻለንን ድጋፍ እንደምናበረክት ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።

‘መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ’ በሚል መርህ ሥር የተደራጁ የአመራሩ የቁርጥ ቀን ልጆች ትግል በድል እንዲጠናቀቅ የድርጅታችን ልዩ ትኩረት እንደማይለየው እናሳውቃለን።  የዐማራ ሕዝብ ፍትሀን በቅርቡ ይጎናፀፋል፤ ኢትዮጵያንም ይታደጋል።  

የኢትዮጵያን ሕዝባዊ ድርጅቶች ጉባኤ አባላት፤

  1. እምቢልታ/አገር አድን ኅብረት (Embilta)
  2. ግሎባል አሊያንስ (GLOBAL ALLIANC FOR THE RIGHTS OF ETHIOPIANs
  3. የኢትዮጵያ የውይይት እና የመፍትሄ መድረክ (EDF)
  4. ቪዥን ኢትዮጵያ (VISION ETHIOPIA)
  5. የዲሲ ግብረ ሃይል (DC Task Force)
  6. የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW)
  7. ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን የሲቪክ ድርጅቶች ኔትዉርክ (WE CAN)
  8. ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት (E-CDCR)
  9. ልዩ ልዩ የኢትዮጵያውያን ተቆርቋሪ ስብስቦች (concerned Ethiopians)
  10. ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያን ሴቶች ማህበር (Intl Ethiopian Women’s Assn.)

 

 

ኢሕማጉ         2

ከኢሕማጉ አዘጋጅ ኮሚቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop