June 10, 2023
17 mins read

አቅምን አለማወቅ፣ አደገኛ ልታይ-ባይነት ወይስ ጥንታዊት ኢትዮጵያን ለመበጥበጥ የተወጠነ እቅድ በተግባር ላይ ማዋል?  ትርጉም-አልባ የሚመስሉት የጠ/ሚ አብይ ድርጊቶች ሲተረጎሙ

352796059 10159641544063576 3938792214993568717 n 1 1 1 1 1
#image_title

በ ኢትዮጵያ ሀገሬ

 

መግቢያ

በዚህ መጣጥፍ ውስጥ፣ ከ 2018 ጀምሮ ሥልጣን ላይ የተቀመጠውን የ ጠ/ሚ አብይን እርምጃዎችና ሃሳቦች ጠጋ ብለን እንመለከታለን። ጠ/ሚኒስተሩ የሚፈጽሟቸው ተግባሮች ሁሉ ያልታሰበባቸውና ትርጉም የሌላቸው ሊመስሉ ቢችሉም፤ በቅርብ ሲመረመሩ ግን አጥፊ በሆነ መሠረት ላይ የቆሙና ታስቦባቸው የሚተገበሩ እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል። የዚህ መጣጥፍ አላማ ይህ፤ ጠ/ሚኒስትሩ በእቅድ የየሚሄዱት አደገኛ ጉዞ ኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለውን ጥፋት ለግንዛቤ ማቅረብ ነው።

 

ኤኮኖሚው

በጠ/ሚ አብይ አስተዳደር ሥር ብሔራዊ ኤኮኖሚው አሽቆልቁሎ አሽቆልቁሎ ከፍተኛ ውድቀት ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ በባለሁለት አኃዝ የዋጋ ግሽበት፣ ዋጋው በወደቀ ብርና እየተባባሰ በሚገኝ ድህነት ተወጥራለች። እነዚህን ፈተናዎች ለመወጣት መላ በመፈለግ ፋንታ፣ ጠ/ሚንስትሩ ያለ የሌላቸውን ገንዘብ ሁሉ ከንቱ በሆኑ የቤተ-መንግሥትና የመናፈሻ ግንባታዎች ላይ ያፈስሳሉ፤ የሕዝቡን አጣዳፊ ችግሮች ዞር ብለው አያዩም።

 

ትህነግ ያነሳሳዉ የትግራይ ጦርነት

ትህነግ ያነሳሳው ጦርነት በሰሜኑ ያገሪቷ ክፍል ውስጥ ከፍተኛ ጥፋትን አስከትሏል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለሞትና ለመፈናቀል ከመዳረጋቸው በተጨማሪ በርካታ መሠረታዊ ተቋማትም ፈርሰዋል። ይህ ጦርነት ብዙ ምክንያቶችን ይዞ በመነሳት የጠ/ሚንስትሩን ግብ መትቷል፤ ለምሳሌ ያህል – በአማራና በትግሬ መካከል ያለውን ክፍፍል ማጠናከርና ከወያኔ ጋራ የይምሰል ኅብረት በመፍጠር በሁለቱ ክልሎች መሀል ያለውን ግጭት ማስቀጠል። የጠ/ሚኒስትሩ እርምጃዎች ለኢትዮጵያ መከፋፈልና መበታተን መንገድ ይጠርጋሉ፤ ይሄም የከፋፋይ አላማን የተከተለ ነው።

 

ሰበብና ጥላቻ (“አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ”)

ጠ/ሚንስትሩ አማራን ጠልቶ የማስጠላትና ኢላማ የማድረግ ውርሳቸውን ቀጥለውበታል፤ ትጥቅ በማስፈታት አመሃኝተው የፈጸመት ሕዝቡን ለእልቂት የሚዳርግ ወታደራዊ ዘመቻ ይሄንን በግልጽ የሚያሳይ ነው። የሚወስዱት እርምጃ በአማራ ላይ ብቻ የሚቆም ሳይሆን፤ የኦሮሞን ሰልቃጭ የበላይነት የሚቃወሙትን ማንኛቸውንም ብሔሮችም የማይምር ነው። የአማራውን ሕዝብ ለማዳከምና ዳግም እንዳይነሳ አድርጎ ለመስበር ከጽንፈኞች ጎን ለጎን በመሆን የሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ኢትዮጵያን ወደባሰ አለመረጋጋት የሚያስገባ ነው።

 

አገራዊ አንድነትን ማናናቅ

የኦሮሞን ፍጹም የበላይነት ለማራመድ ብልው፣ ጠ/ሚንስትሩ አገራዊ አንድነትንና የጋራ ታሪክን የሚያራክሱ ተግባራትን ያራምዳሉ። አገራዊ ቅርሶችንና ብሔራዊ መለዮችን ያፈራርሳሉ።  የኦሮሞ ብሔርተኞች አዲስ አበባ ላይ የሚገፉትን የባለቤትነት ጥያቄ በግልጽ ይደግፋሉ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ያራክሳሉ። የጠ/ሚንስትሩ እርምጃዎች፤ ለምሳሌ ያህል ኦሮሞ ያልሆኑትን የአዲስ አበባ ኗሪዎችን ማፈናቀል፤ ሕዝባዊና አገራዊ ትስስርንና አንድነትን የሚሸረሽርና የሚጎዳ ነው።

 

በከተሞችና በአንድነት ኃይሎች ላይ የሚፈጸም ጥቃት

ኗሪዎቻቸው ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ በመሆናቸው የሚታወቁ መለስተኛና ትላልቅ ከተሞች፤ በጠ/ሚንስትሩ ዘንድ ለኦሮሞ የበላይነት አጀንዳ በእንቅፋትነት የተፈረጁ ናቸው።  ከዚህም በመነሳት፣ በተለያዩ ማህበረሰቦች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸምና ተቃውሟቸውን በማፈን ጠ/ሚ አብይ ሥልጣናቸውን የማረጋገጥ ተግባራቸውን ቀጥለዋል።

 

የጠ/ሚ አብይ ፖለቲካ መዘዞችና የአስቸኳይ ምላሾች አስፈላጊነት

የጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጊቶች ሲከማቹ አገሪቷን ወደ ውድቀት ብሎም ወደ መበታተን ሊገፉ የሚችሉ ናቸው። ከዚህ ጋር የሚመጣው ከባድ መዘዝ አልፎ ተርፎ ቀጠናዋንም ሆነ የቀረውን አለም ሊያሳስብ የሚገባ ነው። ብጥብጥና ሁከት፣ የወንጀል መስፋፋት፣ የማኅብረሰቦች መናወጥና አለመረጋጋት፣ እንዲሁም መጠነ ሰፊ ስደት፤ ከብዙዎቹ ጥቂቶች ክስተቶች ናቸው። ይህ አይነቱን የጥፋት ውጤት አስቀድሞ ለመከላከል ወይም ለማገት አስቸኳይ ርምጃ ይጠይቃል።

 

የአስቸኳይ እርምጃዎች ጥቆማ

የጠ/ሚ አብይን አደገኛ ሂደት ለመግታት፤ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያኖች ሁሉ የሚከተሉትን ማስቀደም ይኖርባቸዋል፤ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ከሚያስተባብር አማራጭ ራእይ በመነሳት ብሩህ የሆነ እቅድ ማጠንጠን የዛሬውን የሚተካ ዘላቂ ሥርአት ለመመሥረት የሚያስችልና ከጊዜያዊ ትብብር ያለፈ የረጅም ጊዜ ስልትን መቅረጽ የኦሮሞን ፍጹም የበላይነት ምኞት እየታገሉ፤ በሌላ ጎን ደግሞ ሁሉን አቀፍ የሆነና ተቀባይነትን የሚያገኝ፤  በተግባርም ሊተረጎም የሚችል ራእይን መቅረጽ አንድነት፣ ሰፊ ቅስቀሳና የሁሉንም ዜጎች ደህንነትና ጥቅም የሚያስቀድሙ ግቦች ላይ ትኩረት ማድረግ ሰፊ ግንዛቤ ያለው ስልት በማውጣት የአኮኖሚ ችግሮችን መፈታትና የሕዝብን ደህንነት ማስቀደም ስብአዊ ጥቃቶችን በማውገዝና ለተጠቁትም ፍትህን በማረጋገጥ ለሰብአዊ-መብቶች መሟገት የኢትዮጵያን ደማቅ ታሪክና የተለያዩ የባህል እሴቶች በመጠበቅና በማክበር አንድነትንና የጋራ ማንነትን ማስተዋወቅ

 

ለዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ መጣር፤

በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ተቃዋሚ ኃይሎችን ስጋትና የለውጥ ጥያቄዎች በተመለከተ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር፣ የዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን ማግኘት ይጠቅማል። ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴው እንደ የተበበሩት መንግሥታት አይነቶችን አለም-አቀፋዊ ድርጅቶችም ሆነ በቀጠናው ውስጥ ተጽእኖ ወይም ጥቅም ያላቸውን አገሮች ያካትታል።

 

ማኅበራዊ ሚዲያንና ሌሎችንም የኢንተርኔት መድረኮች መጠቀም፤

ማኅበራዊ ሚዲያንና ሌሎችንም የኢንተርኔት መድረኮችን በሰፊው በመጠቀም የተቃዋሚ ኃይሎችን ድምጽ ማስተጋባትና የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለአለም ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። መረጃዎችን ሆነ የግል ገጠምሽኞችን በቪዲዮም ሆነ በሌሎችም ቅንብሮች በማሰራጨት ባገር ውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ድጋፍን መሰብሰብ በመንግሥት ላይ ተጨማሪ ጫና በመፍጠር ሥጋቶች መልስ እንዲያገኙ ሊረዳ ይችላል።

 

የአለም-አቀፍ ሚዲያን መሳብ፤

አክቲቪስቶች የአለም-አቀፍ ሚዲያ ዘርፎችን በመቅረብና ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ በማስረዳት፤ ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ስለሰላማዊ መፍትሔዎች አስፈላጊነት እንዲናገሩ ማበረታታት ይችላሉ። ለጋዜጠኞች ትክክለኛና አስተማማኝ መረጃዎችን ማካፈል፣ ቁልፍ ሚና ያላቸው ሰዎች ለቃለ-መጠይቅ እንዲቀርቡ ሁኔታ መፍጠር፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን መስጠትና ትኩረት የሚስቡ ሌሎች መድረኮችን መፍጠር በሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ተግባሮች ናቸው።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ አንድነትንና አብሮነትን መኮትኮትና ማሳደግ

ኅብረትንና ጥምረትን አገር ውስጥ አጠናክሮ መቀጠል ለሰላማዊ ተቃውሞ ውጤታማነት ወሳኝ ነው።  በተለያዩ የብሔርና የፖለቲካ ቡድኖች መሀል አንድነትንና መደጋገፍን ማበረታታት የተቃዋሚ ኃይሉን የተባበረ ድምጽ በማጠንከር፤ ለውጥ የማምጣት ተጽእኖውን ከፍ ያደርገዋል። መወያየትን፣ መግባባትንና መደጋገፍን በማበረታታት፤ ልዩነትን እያጠበቡና በጋራ ራእይ እየተመሩ ለሰላማዊና ሁሉን አቀፍ ለሆነች ኢትዮጵያ የመሥራት ሁኔታን ያጠናክራል።

 

ሕጋዊና ፍትኃዊ መፍትሔዎችን መፈለግ

አገራዊም ሆነ አለም-አቀፋዊ ተገባሪነት ያላቸውን ሕጋዊ መንገዶች መጠቀም ለሰላማዊው ተቃውሞ ፍሬያማ ስልት ሊሆን ይችላል። የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ክስ መመሥረት ወይም አቤቱታ ማቅረብ፣ የአለም-አቀፍ ድርጅቶች ባልደረባዎች የሆኑና የሰባዊ-መብት ሕግጋትን በተመለከተ ረቂቅ እውቀትና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዮች ማማከር፣ እንዲሁም ለማንኛውም ሕጋዊ እርምጃ ሊያገለግሉ የሚችሉ መረጃዎችን በሥርአት መዝግቦና ጠርዞ ማስቀመጥ አስፈላጊ ተግባሮች ናቸው።

 

  1. ቀጠናዊ ድርጅቶችን መቅረብ

ኢትዮጵያ የተለያዩ ቀጠናዊ ድርጅቶች ውስጥ አባል ናት፤ የአፍሪካ ኅብረትንና ኢጋድን (Intergovernmental Authority on Development) በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። እነዚህን ድርጅቶች በመቅረብና ኢትዮጵያ ላይ ስለተከሰተው አደጋ በማሳሳብ ለሰላማዊ መፍትሔዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ መሥራት ይቻላል። ሪፖርቶችን ማቅረብ፣ ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ፣ እንዲሁም የተቃዋሚዎች ስጋት በስብሰባ አጀንዳዎች ውስጥ እንዲካተቱ መገፋፋት ሊጠቀሱ የሚገባቸው ጥቂት ተጨባጭ ተግባሮች ናቸው።

 

ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችንና የአካባቢ ተነሳሾችን መደገፍ

በራሳቸው ተነሳሽነት በየአካባቢያቸው ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ማህረሰቦችን መደገፍ ለውጥን ከውስጥ ሊያመጣ የሚችል ኃይል ነው። እነዚህን የአካባቢ እንቅስቃሴዎች በቁሳቁስና በአቅም ግምባታ በመደገፍ፤ ሰላማዊው ተቃውሞ፤ ማኅበረሰቦቹ ራሳቸው ለችግራቸው መፍትሔ እንዲፈጥሩ፣ እንዲነቁና ለመብታቸው እንዲሟገቱ ጉልበት ይፈጥርላቸዋል።

 

የሰላም መርሆዎችንና ጽናትን መጠበቅ

ለውጥ እስኪመጣ ድረስ በሚደረገው የትግል ጊዜ ሁሉ የሰላም መርሆዎችን መከተልና በፈተናዎችና በትንኮሳዎች ሳይበገሩ ጽናትን ማሳየት ለሰላማዊ የለውጥ ታጋዮች ወሳኝ አቋም ነው። ሰላማዊ የትግል ዘይቤዎችን በጽናት በመከተልና ለጉልበት ባለመከጀል፤ ተቃዋሚው የሞራል ከፍታውን ሊያስመሰክር ይገባል፣ በዚህም ሰፊ ድጋፍ ሊያገኝና ሌሎቹንም ወደትግሉ ሊስብ ይችላል።

ሊጠቆም የሚገባው ጠቃሚ ነጥብ፤ የተጠቀሱትን የትግል ስልቶች በጥሞና ለመተግበር እንዲቻል መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ነው። እነኚህም ሁኔታዎች በጥንቃቄ እቅድ ማውጣት፣ ማቀናበርና ከተጨባጩ ሂደት ጋር ማጣጣም ናቸው። አውዱና ተጨባጭ ሁኔታው  የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉና ሰላማዊ ታጋዮች ይሄን ማገናዘብና እርምጃቸውን ማስተካከል ይገባቸዋል፤ ይህ ግን መርሆዎቻቸውንና ግባቸውን እንደጠበቁ መሆን አለበት።

 

መደምደሚያ

ኢትዮጵያ ወሳኝ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች፤ የመበታተን አደጋም ተጋርጦባታል። በብሔር ተከፋፍላ የምትበታተን ኢትዮጵያ ሊሚገጥማት የሚችለውን መከራና ስቃይ መገመት አይከብድም። ከራሷ፣ ማለትም ከዜጎቿም አልፎ ለምትገኝበት ቀጠናም ሆነ ባጠቃላይ ለአለም የሚተርፍ፣ መቼም የማያልቅ ጦርነትና አለመረጋጋት ያሰጋል።

 


ለተጨማሪ መረጃ የዚህን ጽሑፍ የእንግሊዘኛ አማራጭ በሚቀጥሉት ሊንኮች ማግኘት ይችላሉ።

https://zehabesha.com/is-ethiopia-undergoing-planned-implosion-ethiopia-a-call-for-action/

https://zehabesha.com/is-ethiopia-undergoing-planned-implosion-ethiopia-a-call-for-action-part-2/

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop