May 30, 2023
8 mins read

 ” አንበሳ ለማጥፋት ደኑን ለዕሳት” እንዳንሰሳት ?   

እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ከዉስጥ እና ከዉጭ በቀል ጠላቶች የተለያየ ክህደት እና ጥቃት በህቧ ላይ ደርሷል ፡፡

በዘመናችን የሆነዉ እና እየሖነ ያለዉ ግን በዓይነቱም፤ በብዛቱም  ሆነ በአሰዘኝነቱ የሚለይ እና በህዝብ እና በአገር ላይ የተፈፀመ የክ/ ዘመናችን  በራስ  ራስ ሁለት ምላስ ሆኖ ዝንተ ዓለም በትዉልድ የማይዘነጋ  የክህደቶች ቁንጮ ክህደት ነዉ ፡፡

በቀደሙት የኢትዮጵያ የመንግስት ስርዓቶች የተደረጉ ጦርነቶች የአገሪቷን የግዛት አንድነት እና የህዝቦቿን/ዜጎቿን ሉዓላዊነት ፣ነፃነት እና ህልዉና ለማስከበር  ብሎም ዳር ድንበር ለማስከበር ነበር ፡፡

ይህ ሲሆን መንግስታት ወይም ፖለቲከኞች የስልጣን መንበራቸዉን ለማስጠበቅ አልተጉም ማለት አይደለም ነገር ግን አገር ኢትዮጵያ ፤ወገን የኢትዮጵያ ህዝብ አስካሉ እና ለዕዉነተኛ ብሄራዊ ዕድገት እና ሉዓላዊነት አስከሰሩ ድረስ የማቱሳላን ዕድሜ ሰጥቷቸዉ በኖሩ ኖሮ የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ፡፡

Ethiopia1 1 1 1
#image_title

ምነዋ ካሉ ዛሬ የመከራ እና የደም ጎራ  ቢያመሳቅላት አገር ዜጎች ከዘመነ ኢህአዴግ የጥልመት ዕለት እስከ ዛሬ በባዕድነት በሚታዩባት፣ በስደት እና በሞት በሚቀጡባት ፣ የባህር በር የነበራት አገር ወደብ አልባ ሆና መዉጫ መግቢያ በር ያጣ ህዝብ ፣ በራሱ አገር በነፃነት ለመኖር ተፈጥሯዊ  ህልዉናዉን በተነፈገ ህዝብ …የተሞላች አገር አንድነቷን እና ክብሯን አስጠብቀዉ ያለፉትን ነገስታት እና መንግስታት በዚህ በሞት እና በህይወት መካከል ሆኖ የግፍ ቀንበር ለተሸከመ ኅዝብ  ወደ ኋላ መመልከቱ ምኑ ነዉ ጥፋቱ ፡፡

ድሮ የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን ብሄራዊ ጥቅም የማስቀደም ርዕዮተዓለም ሲሆን በዘመነ ኢህአዴግ (ቀዳሚ /ተከታይ)  አገሪቷ እና ህዝቧ የፖለቲከኞች የግል ንብረት ሆነዉ  የጡረተኛ ፖለቲከኞች አገልጋይ መሳሪያ ሆነዉ የሚስተዋሉበት መሆኑን ያለፉት ረጂም የጭለማ ዘመናት ምስክሮች ናቸዉ ፡፡

የቀደሙት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዜጎች ሉዓላዊነት ቀናይ ሲሆኑ የዘመናችን ጥገኛ ፖለቲከኞች ስለ አገር ብሄራዊ አንድነት ፤ ስለ ህዝብ   ደህንነት ፣ ስለ ትዉልድ መፃኢ ሁኔታ ሊያስብ ቀርቶ የቆመበትን የማያዉቅ በአገር እና በህዝብ ስቃይ የፖለቲካ ሥልጣን እና የቁሳቁስ ምኞት የሚያባዝነዉ ተጧሪ ሆኗል፡፡

የዘመናችን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ከራሳቸዉ ሰፈር  መራቅ  የማይችሉ  ከራሳቸዉ  ድምፅ  ዉጭ ሌላዉ የማይሰማቸዉ  የቀንድ አዉጣ እና የቁራ መንፈስ ያሸነፋቸዉ ከሆኑ ቢቆዩም አስከለተ ሞታቸዉ “ክህደት እና ጥፋት አስከ ዕለተ ሞት ” ብለዋል ፡፡

በዘመናችን የአንድን የፖለቲካ ድርጂት እና ስብስብ ጥቅም በህዝብ ደም  እና በአገር መታመም ኪሳራ ለማስቀጠል የመፈለግ አባዜ እኔ” ከሞትኩ……”እንዳለችዉ የአልጠግብ ባይነት የራስ ወዳዷ እንስሳ  “አንበሳ ለማጥፋት ጫካዉን በዕሳት ” ማቃጠል ይህ ከአገር እና ህዝብ ጥቅም በተቃራኒ ለቡድን እና ለግል ስልጣን ስጋት የሚደረግ በሠላም ስም ማዉደም ስለሚሆን ሊታሰብበት እና ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለፖለቲካ ጥቅም እና ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል በተለያ ጊዜያት እና ጦርነት የርኩስ መዉጊያ በመሆን ሠባዊ ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ፣ ኃይማኖታዊ ፣ ባህላዊ እና ሁለንተናዊ ብሄራዊ መገለጫዎች መጥፋት አይደለም መነካት እንደማይኖርባቸዉ ሁሉም ኃላፊነት መዉስደ አለበት ፡፡

ድሮ የሃይማኖት ተቋማት የዕምነት ስርዓት መፈፀሚያ እና ማስፈፀሚያ ከመሆናቸዉ በላይ የአገር እና የህዝብ ጉዳይ ቀዳሚ እና ዋና ጉዳያቸዉ ነበር ፡፡ ዛሬ ግን በተለይም ከአስራ ዘተኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓም ጀምሮ የፖለቲካ መሳሪያ ከመሆናቸዉ አልፎ ዕጉም ብሎ የጠጠጋን ሠዉ አሳልፎ የመስጠት እና  ከመንፈሳዊ መተጊያ እና በየጊዜዉ የቡድን ዓላማ ጋሻ እየሆኑ ነዉ ፡፡

ለዓመታት ኢትዮጵያዉያን በአገራቸዉ ባይተዋር ፣ ገባር ፣ በማንነታቸዉ ጥቃት ሲደርስ፣ የኃይማኖት እና ዕምነት ቤቶች /ቤተ ዕምነቶች ከጥንት አስከዛሬ በጉልበተኞች ሲደፈሩ ከህዝብ ፊት የማይኖሩ እና ማይመሩ  ከዚህ በላይ ምን ሊሰሩ ያስባሉ ፡፡

ዛሬ ቤተ ዕምነቶች በተለይም አብያተ ክርስቲያናት እና መኢመናኑ በዘመናት ጅረት ያልደረሰበት የጥፋት እና ጥቃት  ጎርፍ ሲያጥለቀልቀዉ እያዩ ዝም የሚሉ ነገር ግን የአገር እና ህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ የት አሉ ፡፡ ዕምነትም ፤ ስልጣንም ……በአገር ነዉ አንበሳዉን ለማጥፋት ጫካዉን በዕሳት ሲቀጣጠል አይቶ የማያይ እንዴት ከሠማያዊ አይደለም ከዚሁ ከጫካዉ ዕሳት ሊድን ይችላል፡፡

ቢሆን ብሎ አንበሳ ለማጥፋት የማይጠፋ ዕሳት ለጫካ መመኘት ማይጠፋ የታሪክ ሰደድ ዕሳት እና የትዉልድ ከምንጊዜም ፀፀት ለመዳን ሁሉም ስለ ራሱ እና አገሩ ይመለከታኛል ባይ በጫካዉ ዉስጥ መሆኑን አዉቆ ሳይጠፋ ሰደዱን ሳይስፋፋ ለእኔ ብሎ ያጥፋ ፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንበሳ ፍርቶ ደንን ለዕሳት ላይቀሬ ተያይዞ መጥፋት በገለባ እና ንፋስ ዕሳት መያዝ ነዉ ፡፡

“ለአገር ለሠላም እና ዕድገት ሠላም እና አንድነት እንጂ ዕብሪት እና ጦርነት አይደለም ፡፡ ”

“አንድነት ኃይል ነዉ !”

Allen T. silassie

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop