“በሲና ተራራ
በዛ በከፍታ
በዙፋንህ ሆነህ
ክብርህን አየነው ”
ያኔ ከሲና ተራራ የመጣው አይነት መልዕክት ፤ ለዛሬው ዓለም በእጅጉ ያሥፈልጋል ።
ስለ ተራ ሞቹ ሰው ማን ደንታ አለው ? መንግሥታት እንደሆነ አእምሮአቸው የተያዘው በዝና ነው ። ያውም በሞላጫ ዝና ። ዝና ሞላጫ ነው ። ትላንት ለህዝብ ያሥተዋወቀህ ፣በከፍታ የናኘው ዝናህ ነገ ምደር ላይ ተከስክሶና አልባሌና መሳቂያ ሆኖ ታገኘዋለህ ። ነገ ሥልህ በዘመን ብዛት እጅግ የራቀውን ፣ የነጎደውን ነገ ነው ። ከ10 ትውልድ በኋላ ያለውን ነገ ። በዛ ነገ ፣ የማንኛውም መንግሥት ዝና ይረሳል ። …
በነገ ዕይታ ፣ ህይወት እንቆቅልሽና ድራማዊ ናት ።
ደሞም ተገንዘብ ፣ በህይወት ዑደት ውስጥ ሰው ከትንሾ ትል የሚለይበት የህይወት ዕደት የለም ። ሰው እና ትል በህይወት ዑደት ተመሳሳይ ሽክርክሪት ነው ያላቸው ። ይወለዳሉ ፤ ያድጋሉ ፤ ይምታሉ ። ( ሳያድጉ የሚሞቱ ወይም የሚቀጩ ህይወቶች በሁለቱም ወገን እንዳሉም ይታወቃል ። )
በመወለድ ፣ በማደግ እና በመሞት ደረጃ ሰው ከትል እኩል ነው ።
ይኽ እውነት ቢሆንም በማህበራዊ ኑረው የበለጠ ትል የሚያደርጉት እውነቶች ደግሞ አሉ ።
አንደኛው እንደትል ተነጂነቱ ነው ። ልምጭ እና እሥር ቤት ያለው መንግሥት ሰውን በየቀኑ እንደትል ሲነዳው እናያለን ።
ለምሣሌ ፣ በሚያሳዝን መልኩ ከፊሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ከደርግ ሥርዓት ጀምሮ ሳይወድ በግዱ በየጎጡ መንግሥት እያስፈራራው ለድጋፍ እና ለተቃውሞ ሰልፍ እንደ ትል ወጥቶ ይርመሰመሳል ። በተለይም በኦሮሚያ ክልል ። ተራው ህዝብ ካድሬዎች የፃፉትን ወረቀት ይዞ በግድ በአደባባይ እንዲወጣ እና በማይገበው ቋንቋ ከቲባዎቹ ዘፍነውበት ወደ ቤቱ ይመለሳል ። በነሱ ቤት የቀደመን ጭቆና እና ትምክህት በተመሳሳይ መልኩ መመለስ ፍትሃዊ ና ዴሞክራሲያዊ ነው ። ። ይጮኻል ። ምንም ባልገባውና በማያውቀው ጉዳይ ውስጥ ገብቶ እንዲፈተፍት ይደረጋል ። ባልገባው ጉዳይ “ በግንቦት ሃያ “ ለመከላከያ ድጋፍ ለማድረግ ሰልፍ ወጣ ይባላል ።
ይህ የለየለት ሸፍጥና የጅላንፎ ፕሮፓጋንዳ ነው ። ዛሬም “ አብይ መራሹ ፣ የብልፅግና መንግሥት “ እንደ ወያኔ እና እንደ ደርግ በውሸት ፕሮፓጋንዳ የሚያምን መንግሥት የሆነው ከሥሪቱ የተነሳ እንደሆነ አውቃለሁ ። ያልተዘራ አይታጨድምና ! ( መቼም አብይ አህመድ በአንድ እጁ ማጨብጨብ አይችልም ። )
በአንድ እጅ ማጨብጨብ ባይቻልም ፣ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የአገር መሪ በመሆኑ ሁሉም አካባቢ ፣ ጎጥና ቀበሌ ውስጥ ሳይቀር ፤ በሚጠፋው ጥፋት ጣታችንን ወደ ሰውየው መቀሰራችን አይቀርም ። የህግ አሥፈፃሚው ቁንጮ በመሆኑ !
ዛሬ አብይ አህመድን በመልካም የሚያነሰው እጅግ ጥቂት ሰው ነው ። በተደጋጋሚ ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በወሰነው ውሳኔ የተነሳ ከህዝብ ጋር ተጣልቷል ። አንዳንድ ክልሎች ውሥጥ ያለው ህዝብም ከወገኖቹ ሥደተሰ ፣መፈናቀልና ምት የተነሳ አምርሮ ጠልቶታል ። እርሱ ግን ዛሬም ህዝብን በግዳጅ ( ለቅንጥብጣቢ ሲሉ በሚጮሁ ምሥኪነሰ ህድ አደሮች እየታገዘ … ) በኦሮሚያ ክልል በግድ ሰልፍ በማሶጣት ፣ “ ህዝብ ለመከላከያ ያለውን ድጋፍ ገለፀ “ ቀማለት ፕሮፖጋንዳ ይሰራል ።
ህዝብ የአገር መከላከያን መቼ ጠልቶ ያውቃል ? ” መከላከያ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ማለት አይደለም ወይ ? ”
በእውነቱ መንግሥት ውሥጥ ከትል ያልተሻሉ ሰዎች ናቸው የተሰገሰጉት ማለትም ይቻላል ። ዛሬ አሰስና ገሰሱ ነው መንግሥት የሆነው ። ይህንን የምታረጋግጡት ስራዬ ብላቸሁ የኦሮሚያ ከተሞች ምሽቶች ምን አሰንደሚመሥሉ ስታዩ ነው ።
“ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች በምሽት ፣ ዘራፊዎች ሥለዘረፋቸው ሳያፍሩ በየመሸታ ቤቱ ያወራሉ ። እጅግ ጉድ የሚያሰኝ የዘረፋ ፣ የመሬት እና ቤት ሽያጭ ታሪክ ያወራሉ ። ከሁሉም የመንግስት ተቋማት በጨረታ ሥም ፣ በግንባታ ሥም በተሽከርካሪ ጥገና እና ነዳጅ ሥም ረብጣ ብሮች ተሞጭልፈው የሚመነዘሩት ና የቃል ኪዳን ውል የሚፈረምባቸው በፍየል ቀርጥ ቤቶች እና በትልልቅ ሥጋ ቤቶች ውሥጥ ነው ። ነጋዴዎች በሥጋ እና በመጠጥ ሥም እጅግ የሚዘገንን ዝርፊያም ያካሂዳሉ ። … ( የአገር ውሥጥ ገቢ ሰብሳቢ ቀረጡ ላይ በደንብ ይያዝልን ። እንላለን ። )
ባይገርማችሁ ፣ አንዳንድ እጅግ ያጌጡና በመብራት ያሸበረቁ የፍየል ሥጋ መሸጫ ቤቶች ፣ ጥብሥ ብቻ ሳይሆን ዝሙትም ያቀርብላችኋል ። አንዳንዴም ካላሥተዋላችሁ ፣ የፍየል ጥብስ ብለው የሚሸጥላችሁ ፤ የከረመ የበሬ ሥጋ ነው ። በሥካር ልብ ልታውቁ አትችሉምና ! ! እንኳን የበሬ ሥጋ ይቅርና ጨጓራ የበዛው የበሬ ሥጋ ቢቀርብላችሁ ወይም አንጀት ተቀላቅሎ በደበዘዘ መብራት ቢሰጣችሁ ከመብላት ውጪ አማራጭ የላችሁም ። ( አይጥ ጠብሰው ቢሰጧችሁም በፍየል ጥብስ ሥም በስካር መንፈስ እንክት አድርጋችሁ ትበላላችሁ ። )
በአንዳንድ የመዝናኛ ቤቶችም የመጠጡ ጥራት እጅግ የሚያጠራጥራችሁ …ለጤና ማጣት የሚዳርጋችሁ …በውስኪ ሥም የተቀላቀለ አረቄ የሚቀርብላችሁ ። በቢራ ሥም ከዚህ እና ከዛ የተበወዘ ጭላጭ የያዘ ጠርሙስ በግርግር የሚቀርብላችሁ መሆኑንን አታስተውሉም ። …
ይኽንን ማጭበርበር መቆጣጠር ያለበት ህግ አሥፈፃሚው ግን የዕለት ከዕለት ሥራውን አይከውንም ። በህግ ማሥከበር ሥምም ከሁለት ሰዓት በኋላ ኪሱን ለማስከበረ በትጋት የተዘጋጀ ፣ ፖሊሥ ከጎጥ ሲቪል ግብረ ሃይልና በህዝብ መዋጮ የተቀጠረ ሚሊሻ ጋር በየአሥፓልቱ ተሰማርቶ ይገኛል ። …
በየቀበሌው ሁሉም ሚሊሻ ና ፖሊስ ከወዶ ገቡ ሲቪል ሴትና ወንድ ጋር በአብረቅራቂ ልብስ ተከፍኖ ወጪ ወራጁን በመፈተሽ ፣ መኪና አሥቁሞ በመበርበር መንገደኛን ያንገላታል ። ባሥ ሲልም ፣ ” የውሃ መግዣ ፤ የብርድ መከላከያ ፤ ስጡኝ ። ” እያለ ይቀፍላል ። ( አይደረግም ካልክ ድርጊቱ ያጋጠማቸውን የብሾፍቱ ባለሥልጣናት ጠይቅ ። የብሾፍቱ ከተማ መግቢያ ፍተሻ ከአዳማ የተሻለ እና በፖሊስ ብቻ የሚደረግ መሆኑንንም እወቅ ። )
አንዳንዱን ከተማ በተለይም ከአዳማ ጀምሮ ያለውን ሥታሥተውል ፤ ይኽ አገር የአልሻባብ አገር ነው እንዴ ? በሰላማዊ አገር አሥፓልት ላይ የሚፈጠር ህገ ወጥነትን በእንደዚህ አይነት ፍተሻ መከላከል ይቻላል እንዴ ? ህገ ወጦችስ ፍተሻ መኖሩን እያወቁ በአሥፓልት መንገድ እንዴት ደፍረው ይጓዛሉ ? ህገ ወጦችን ፣ ሌቦችና ዘራፊዎችን የሚቆጣጠር የሚያድን …ልዩ ግብረ ሃይል መንግሥት ፣ እንደመንግሥት እንዴት ማቋቋም አቃተው ? ብለህም ትጠይቃለህ ።
ምላሽህም ድሮስ የጃጁና ያውና አንድ የሆኑ ፣ ሆዳም ና ዘረኛ ካድሬዎችን ሰብስቦ ፣ ይኽንን ታላቅ ና በለምጡቅ አእምሮ ህዝብ በድፍረት የሚመራ ፓርቲና መንግሥት ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል ? የሚል ጥያቄ አዘል መልስ ይሆናል ?