May 26, 2023
8 mins read

‘ተወን በ110 እንላክበት!’ (እውነቱ ቢሆን)

Birr and dollar
#image_title

Birr and dollar

ይህንን ያሉኝ በቅርብ የሚያዉቁኝና የራሴ ዘመዶች ጭምር ናችው፡፤ አብይ አህመድ በዘረጋው የዶላር ጥቁር ገበያ ሰንሰለት መሰረት አንድን ዶላር በብር 110 ሂሳብ እየመነዘሩ ብሩን ወደ አገር ቤት የሚያስልኩት፡፡

“የአብይ አህመድን ጉድና ቅሌት ራሱም አይችለው” በሚል ርእስ እኤአ May 24, 2023 በወጣው የዘሀበሻ ድረ -ገጽ የአማርኛው ክፍል ላይ አጭር ጽሁፍ አውጥቼ  ነበር፡፡ ሰውቼ መነሻቸው ያ ጽሁፍ ነው፡፤ ስጋትም ይመስለኛል፡፡ አይዟችሁ፡ አብይ አህመድ ማርና ወተት የሚያስገኝለትን ያንን ቧንቧ አይዘጋውም፡፡እንዴት ብሎ ሰው እስትንፋሱን ይዘጋል፡፡ ህዝቡን የሚያሰቃየው ያ ባንቧ ሊዘጋ የሚችለው ህዝቡ ኦሮሙማን ጠራርጎ ሲያስወግድ ብቻ ነው፡፡ እኔ ያንን አጭር ጽሁፍ የጻፍኩትም ዘረፋው እንዴት እንደሆነ ለማሳወቅና አብይ አህመድ ሙሉውን የተዘፈቀበት መሆኑን ለማጋለጥ ነው፡፡ እናንተ ግን ያያችሁት የምትልኩትን ብር በዚያ ምንዛሬመጠን ለመላክ አለመቻላችሁ የሚያሰጋችሁ መሆኑ ነው፡፤ አልተገናኝቶ!!!

ነገሩ የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያ ከመሆኑ ባሻገር የራሱን አገር ህዝብ በዘር እየለየ እንደፈለገው ለሚጨፈጭፈው ተረኛው የኦሮሙማ የገዥ ቡድን የመጨፍጨፊያ መሳሪያ መግዣና ሀብት ማካበቻ እየዋለ ስለሆነ ይህንኑ ነበር በጽሁፌ ለማጋለጥ   የሞከርኩት፡

በተለይ የዶላሩ አላላክ በብር ተመንዝሮ አገር ቤት ለተላከለት ሰው በባንክ ቢደርስም ዶላሩ(የውጭ ምንዛሬው) እንደ አገር remittance ተውስዶ ወደ ኢትዮጵያ ሂሳብ /አካውንት የማይገባ መሆኑ ላይ ትኩረት በማድረግ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ፡፡ አሁንም ልድገመው፡፡ ዶላሩ ለኢትዮጵያ አይደርሳትም፡፡ገዥው መደብና የእርሱ ወኪሎች ሆነው ጥቁር ገበያውን የሚያሳልጡት ውጭ ካሉት “”የተመረጡ” ገንዘብ አስተላላፊወች ጀምሮ አብይ አህመድ በራሱ መስመር ያሰማራቸው ሰወች በየቀኑ ቢሊዮኖች ብሮችን ያለገደብ እያንቀሳቀሱ ለተከፋዮቹ በባንክ በኩል የሚከፍሉትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

አላላኩ በህግጋዊዉ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ተመን ማለትም ምሳሌ አንድን ዶላር በብር 54 ሂሳብ በህጋዊ መንገድ ቢሆንና ይህንኑም ህጋዊ አላላክ በሚያስተናግዱት እንደ western union or money gram ወይንም ሌሎች የኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጭ ምንዛሬ አስተላላፊወች በኩል ቢሆን ኖሮ የውጭ ምንዛሬው (ዶላሩ) ዞሮር ዞሮ ገዥው መደብ የሚያዝበት ቢሆንም ቢያንስ ወደ ኢትዮጵያ ሂሳብ /አካውንት ይገባ ነበር፡፡

መንግስት ተብየው የዱርየወቹ ስብስብ ይህንን ስራ ከውጭ አገር ላኪነት እስከ በአገር ውስጥ የተላክን ብር ከፋይነት ድረስ ያሉትንና ስራውን እንዲሰሩለት አቅዶና በራሱ ልዩ የሌብነትና የዘራፊነት አሰራር ያሰማራቸውን ሰወች/ድርጅቶች እንደ አግባባቸው ለስራወቻቸው ሽፋን እየሰጠ ክፍያወችን ይከፍላቸዋል፡፡ በዚህ አኳኋንም የጥቁር ገበያው ስራ ተሳልጦ መጨረሻ ላይ ዶላሩ ውጭ አገር ሰምጦ ይቀራል፡፡

ዶላሩ በውጭ ሰምጦ ይቀራል ስል ሌላ ሳይሆን የገዥው መደብ ሊጠቀምባቸው በመረጣቸው ነጋዴወችና ሌሎች ሰወች/ድርጅቶች የውጭ አገር ሂሳቦች ውስጥ ይገባል ማለቴ ነው፡፡ እንደ አገር በኢትዮጵያ አካውንት ውስጥ አይገባም ማለቴ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በ110 ምንዛሬ ሂሳብ ዶላር ተልኮለት ብዙ ብር የሚያገኘው ሰው ኑሮው ከውጭ አገር ምንም ብር ከማይላክለት ሰው የተሻለ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ አይነቱ ገንዘብ ከውጭ የሚላክለት ሰው ብዛቱ ስንት ነው ጥያቄው?? ሰማይ ላይ በተሰቀለ ኑሮና የዋጋ ንረት ችግሩንስ ምን ያህል ይቀርፍለታል ነው ጥያቄው፡፡

ሌላው ወሳኝ ጥያቄ ደግሞ ሌላው ህዝብ ሜዳ ላይ ዘጭ ብሎ ለምሳሌ ጤፍን በወሬ ብቻ እንዲሰማትና እንዲያልማት ተደርጎ፣ ኑሮው ሰማይ ምድሩ የተደፋበት ሰው፣ ሁሉም ነገር ዞሮበት ያለው ሌላው ህዝብ በስፋት በሚኖባት አገር ውስጥ ምናልባትም 99%ቱ እንደዚህ አይነት መራራ ኑሮ በሚገፋባት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚላከው ብርና የዶላሩ ጥቁር ገበያ ምንዛሬ ምን ማለት ነው ጥያቄው፡፡

ከአምስት አመት በፊት የነበረው የወያኔ አገዛዝ መጥፎ ዘመን ነበር ስንል በነበረው የወያኔ ጊዜ የዶላር ጥቁር ገበያ አስራር የነበረ ቢሆንም በህዝቡና በአገሪቱ ላይ የአሁኑን አይነት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ መመሰቃቀልንና የአሁኑን አይነት የኑሮ ውድነትን እንዳላደረሰ የምንክደው ጉዳይ አይደለም፡፡በወያኔ ጊዜ የነበረውን ያንን እውነታ መካድ ነውረኝነት ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ ሰቅጣጭና ስር ቆራጭ መከራ በህዝቡ ላይ እየወረደ ያለው በአውሬው አብይ አህመድና ሁሉ ኬኛ መመሪያው በሆነው የአረመኔወች አረመኔ በሆነው በአሁኑ የኦሮሙማ ዘመን ነው፡፡

“”ተወን በብር 110 እንላክበት”’ ለሚሉኝ ሰወች አንድ ነገርን ብቻ ብዬ ላብቃ፡

አምና በሬ ነበርኩ ዘንድሮ ወይፈን
እያደሩ ማንሰ ወይ ጥጃ መሆን

ፈጣሪ አምላክ የህዝቡን የነጻነት ተጋድሎ  ወደ ድል ያፋጥን!

2 Comments

  1. ይህ እብሪተኛ የተረኞች ዘረኛና ወንጅለኛ መንግስት አገርን ይዞ ከመውደቁ በፊት ዋና ዋናወቹን ነጥሎ ማስወገዱ ግድ ይላል::
    አለበለዚያ ከሩዋንዳ የባሰ የእርስ በእርስ መተላለቅ ይመጣል::
    ይህንን ደግሞ ገዝው የ666 አማኞች ቡድንና የኢትዮጵያ ጠላቶች አጥብቀው ይፈልጉታል::
    ለይቶ በተናጠል ምርጥ ስትራቴጅ ነው::

  2. ዶላር ላኪው ላይ መፍረድ ቢከብድም የገዥውመንግስት ተባባሪ መሆኑን ግን የግድ መረዳት አለበት::
    አስተላላፊውና ብር ለተቀባዩ የሚክፍለው የዘራፊው መንግስትተባባሪወች ናቸው:: የአብይ አህመድና ቡድኑ ዘራፊነትን የሚያቀላጥፋት ሚንስትር አህመድ ሽዴ, ታከለ ኡማ አዳነች ቀበሮዋ ወዘተ በዝርፊያ የተዘፈቁበት ስለሆነ ምንም ጥርጥር የለውም::
    ይተፏታል ወይንም አንቋቸው ይሞታሉ::
    ህዝቡ እንደገና እንሰራርቶ ይነሳል::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182928
Previous Story

ዶ/ር ይልቃል ተቃውሞ ገጠማቸው/ወንጀለኛው ፖሊስ አዛዥ ተያዘ/ብፁዕ አቡነ አብረሃም ተናገሩ(አሻራ ዜና18/09/2015 ዓ/ም )

348229536 920331625690830 5922480985561943637 n
Next Story

ሻለቃ ዳዊት ስለ ትግሉ እና ሽግግሩ ጊዜ ተናገሩ | Hiber Radio with

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop