ግማሽ ጎፈሬ ግማሽ ልጬ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር ፕሮጀክት

/

በቶፊቅ ተማም

ከዛሬ አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት  አመት በፊት በአፄ ሚኒሊክ መናገሻ ከተማ የሆነችውን አንኮበር ጥለው ወደ አዲስ አለም አቀኑ መቼስ እንጦጦ የሰማይ ጫፍ የወጡ ያህል ቁልቁል ሀገሩን ለመመልከት ምቹ ነው እናም ለንጉሱ ምቹ ቦታ እንደሚሆን አያጠራጥርም ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ከተራራው ጫፍ ቁልቁል የሚታየው ጥቅጥቅ ጫካና አልፎ አልፎ ደግሞ ወለል ያለው ሜዳ ቀልባቸውን ሳይዘርፈው አልቀረም ከሜዳዎች ሁሉ ደግሞ ጎበዛዝቱ በጉግስና በገና ጨዋታ ጉልበቱን የሚፈትሹበትን የሚወድቁና የሚነሱበት መቦረቂያቸው ነው ከእለታት በአንድ ቀን ፍልውሀ ፊል ፊል ወደሚልበት መስክ ወረዱ እዚያም ብዙ ለአይን የሚስብ የተፈጥሮ ውበት ነበረው እቴጌይቱ ግን ከዚህ በላይ ከዚህ በፊት አይተዋት የማውቋት አንዲት ልዩ አበባ መረከቻቸው‹‹ አዲስ አበባ ›› አሉ አዲስ አበባ እንዲህ ተቆረቆረች ህዳር 14 1879 አዲስ አበባም የንጉሰ ነገስቱ መናገሻና የኢትዮጲያ ዋና ከተማ ስፍራ ያዘች ይህች የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ የሆነቸው አዲስ አበባ የብዙ ብሄራዊና ፖለቲካዊ መስታጋብሮች መከወኛ  የአፍሪካ ርእሰ መዲና ብሎም የበርካታ ዲፕሎማትና ዲፕሎማሲያዊ ተቋማት መገኛ የሆነቸው ከተማ በብዙ መንግስታት ስር የመተዳደር እጣ የደረሳት ሲሆን በአሁኑ ወቅትም  በገዢው ፓርቲ ብልፅግና ስር በመተዳደር ላይ የምትገኝ ሲሆን የወቅቱ የከተማዋ አመራሮች ከቀደምት አቻ አመራሮችም በተለየ ሁኔታ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሀገር ወዳድ ባለሀብቶችን የበለጠ በመቅረብና በማስተባበር የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እየከወነ ይገኛል ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ እየከወናቸው ካለው ዋና ዋና ተግባራት መከካል ከዚህ ቀደም በግለሰቦች በሀይማኖት ተቋማት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ይተገበር የነበረውና ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ ወጥ በሆነ መልኩ በመንግስት ቁርጠኝነትና ከፍተኛ ድጋፍ  በቀድሞ ምክትል ከንቲባ ታካለ ኡማ (ኢንጂነር) የተጀመረው የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ሲሆን ይህም ለበርካታ ወላጆች እፎይታን የሰጠ ተማሪዎች የተሻለ የትምህርት አቀባበል ኖሯቸው የተሸለ ዜጋ ይሆኑ ዘንድ እድል የከፈተ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩም ወደ 4 ቢሊየን ብር ገዳማ በአመት ለተማሪዎች ምገባ እየወጣ ሲገኝ በዚህም ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመገብ የቻለ ሲሆን ይህም ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ የተማሪዎች ውጤት ማሳደግ የመድገምና የማቋረጥ ምጣኔን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ተችሏል በምገባ ፕሮግራሙ ከ 16 ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች የስራ እድል ሲፈጥር  ይህም በጎ ስራ በቅርቡ በጣሊያን ሚላን በተካሄደው የአመጋገብና ስነ ምግብ ዘርፍ ከ 133 ከተሞች ተወዳድራ የሚላን ፓክት / Millan Urban food Policy Pact / 2022 አሸናፊ እንድትሆን ማስቻሉ ይታወሳል ከዚኁ ጎን ለጎን ከተማ አስተዳደሩ ቀላል ሊባል የማይችል ወጪ በማውጣት ለተማሪዎች የደንብ ልብስ እና የትምህርት ቁሳቁስ በየአመቱ ለተማሪዎች በማዳረስ ላይ ሲገኝ ይህም ለወላጆች ቀላል ሊባል የማይችል እፎይታን ሰጥቷል ፡፡

ከዚሁ ከምገባ ጎን ለጎን ሊነሳ የሚችለው ሰው ተኮር / Human Oriented / ተግባራት መካከል ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች በቀን አንድ ጊዜ ንፀህ ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ ዜጎች ያለ ምንም ችግር በክብር እጃቸውን ታጥበው የሚመገቡበት የምገባ ማእከል ማቋቋም ሲሆን ይህም አስከ አሁን በከተማው ወደ 15 ገደማ የምገባ ማእከላት ተቋቁመው በቀን 30 ሺህ ዜጎች የምገባ አገልግሎት እያገኙበት ሲገኝ ይህም ከተሰሩ መልካም ተግባሮች መካከል ይጠቀሳል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መሲ ባንቺም ኮራን - ከነብዩ ሲራክ

ሌላው በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ካሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መካከል በተለይ ለአቅመ ደካሞች  የቤት እድሳት ተግባራት ሲሆን ይህንን  በጎ ተግባር  ሌሎች ተቋማት በግል ተነሳሽነት  እየተገበሩት ይገኛሉ ይህም የሚያስመሰግን ተግባር ነው ለዜጎች የተመቸ ከባቢን ከመፍጠር አንፃር በጎ ፋይዳ ሲኖረው  ከዚሁ ጎን ለጎን የተቋማት ማስፋፊያ ግንባታ በተለይም አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመማርያ ክፍሎች ግንባታ በአብነት የሚጠቀስ ሲሆን ይህም ፈረቃን በማስቀረት  በትምህርት ጥራት ላይ የተሻለ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል ፡፡

ሌላው በየጊዜ እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ በማሰብ በከፊልም ቢሆን የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የገበያ አማራጮችን በማስፋት ረገድ የምርት አቅርቦትን በስፋትና በጥራት እንዲሁም በአነስተኛ ዋጋ እያቀረበ ሲገኝ ለዚህም ማሳያ ከ 130 በላይ አማራጭ የእሁድ ገበያዎች በመፍጠር የኑሮ ውድነትን ጫና ለመቀነስ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ከዚህ ባለፈም በተለይ ምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶች ላይ የሚታየውን ረጅም የገበያ ሰንሰለት ለማሰጠር በመሳብ ወደ አምስት ገደማ የሚሆኑ ግዙፍ የግብርና ምርቶች የገበያ ማእከላት በመገንባት ላይም ይገኛል ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በክረምት ብቻ ይደረግ የነበረውን የበጎ ፈቃድ ስራን በበጋውም ይተገበር ዘንድ እየሰራ ያለ ሲሆን የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በአግባቡ ለመከወን በማሰብ  አስተዳደሩ የህብረተሰብ ስራ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ኮሚሽን በማቋቋም ዘርፈ  ብዙ የበጎ ፍቃድ ስራዎች የሰራ ሲሆን ከተማዋ የበጎ ፈቃደኞች ከተማ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ሲገኝ በዚህም ባለፉት የክረምት ወቅቶች ከ1ሚለየን በላይ ወጣቶች በማሳተፍ በሰብአዊና ማህበራዊ አገልግሎት አረንጓዴ ልማትና አከባቢ ጥበቃ ፤የማጠናከርያ ትምህርት የጤና አገልግሎት ፤የአቅመ ደካሞችና የአረጋውያን የአካል ጉዳተኞች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች መኖሪያ እንዲሁም የማእድ ማጋራት ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ ሊባል የሚችል የመንግሰትን ወጪን ማዳን አስችሏል ፡፡

ሌላው ከተማ አስተዳደሩ  በልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ ሰው ተኮር ፐሮጀክት የከተማ ግብርና ሲሆን አስተዳደሩም ይህን በደንብ ለማሳለጥ በማሰብ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አቋቁሞ ወደስራ የገባ ሲሆን በዚህም ዜጎች አነስተኛ ቦታ የተለያዩ ምርቶችን እንዲያለሙ በማድረግ በዜጎች ላይ እየታየ ያለውን የኑሮ ውድነት ማቃለል እየተተገበረ ያለ  ቀላል ሊባል የማይችል ቁጥር ላላቸው ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ሲያስችል በመንግስት እና በግል ተቋማት ያሉ ክፍት ቦታዎች በከተማ ግብርና ስራዎች እንዲሸፈኑ በማድረግ የተሻለ የመሬት አጠቃቀም መፍጠር የተቻለ ሲሆን ከዚህ ባለፈም በተለይ ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰው ህዝብ ቁጥር እያየለ በመምጣቱ ለመዲናዋ የምግብ ፍለጎት የሚውል ተጨማሪ ምርት በማስፈለጉ ይህንን ምርት ለማቅረብ እገዛ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መንግስት ለሚቀጥሉት አመታት ለመተግበር ላቀደው የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር አማካይነት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ሲሆን የከተማዋን በተለይ የዶሮ እና የእንቁላል ፍላጎት ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ ከመፍጠር የከተማው የእንቁላል እና የዶሮ ስጋ አቅርቦት ላይ የበኩሉን ሚና መጫወት አስችሏል የዳቦ አቅርቦትን በተመለከተ ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር በየክፍለ ከተሞች አነስተኛ የዳቦ ፋብሪካዎች በመገንባት ከአመታት በፊት በቀን 300 ሺህ ያልበለጠ የነበረው የዳቦ አቅርቦት ከተማ አስተዳደሩ ከባለሀብቶች ጋር በመሆን በተሰራው ስራ በአሁኑ ወቅት  ከ 3 ሚሊየን በላይ ዳቦ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የሚያስችል አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰንደቅ አላማ “ጨርቅ” መሆኑን የማያውቅ የዓለም ሕዝብ ባንዲራውን ለብሶ እያበደ ነው!

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት ከመንግስት በጀት እንዲሁም  ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር እየሰራቸው ያሉ ሰው ተኮር ተግባራት የሚያስመሰግኑ ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ ከተማዋን የጥበብ ከተማ ከማድረግ አኳያ የጥበብ ጉዳዮችን በአግባቡ ከመደገፍ አንፃር ክፍተቶች በጉልህ የሚታዩ ሲሆን የተወሰኑትን በዚህ ፅሁፍ ለመጥቀስ እሞክራለሁ ፡፡

የመጀመርያው በተለይ የተጀመሩ ንባብ ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞች በአግባቡ መደገፍ ክትትል ማድረግ ደራሲያን ከአንባቢዎች ጋር ተገናኝተው ስለ ስራዎቻቸው የሚነጋገሩበት ከአድናቂዎች ጋር የሚገናኙበት ስራቸውን የሚሄሱበት መድረክ መደገፍ የሚገባ ሲሆን  ከአመታት በፊት በተለይ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፀሀፍት ኤጀንሲ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ይደረጉ የነበሩ የመፅሀፍት ዳሰሳና ውይይት የተቋረጡ ሲሆን በቅርቡ ጊዜ የተጀመረው እና ለጥበብ ፍቅር ባላቸው የዋሊያ መፀሀፍት ባለቤት መልካም ፈቃድ  በየሳምንቱ በዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ አጋፋሪነት የሚካሄደው  የተለያዩ ደራሲያንን በመጋበዝ ይደረግ የነበረው የመፅሀፍት ዳሰሳ እና ውይይት በአካል ከሚታደሙ ታዳሚያን ባለፈ ፕሮግራሙ በአግባቡ ተቀርፆ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጭ በመሆኑ በመላው አለም ያሉ ታዳሚያን የሚከታተሉት ድንቅ የነበረ ፕሮግራም ቢሆንም በቂ ድጋፍ ከከተማ አስተዳደሩም ይሁን ከሌሎች ባለማግኘቱ ሳቢያ በነበረበት ግለት መቀጠል ያልቻለ ሲሆን በፕግራሙ ከብዙ ደራሲያን ጋር የመገናኘት እና ስለ ስራዎቻቸው እና ስለ ስነ ፅሁፍ የመወያየት ፍላጎት ያላቸው የመፅሀፍት አፍቃሪያን ይህ እድል እየመከነባቸው ሲሆን ይህ መሰል ፕሮግራሞች በአግባቡ ሊደገፉ በከተማው በሁሉም አቅጣጫዎች በሚገባው ልክ ሊስፋፉ ይገባል ፡፡

ሌላው ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ገፅታ ለመለወጥ የተለያዩ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ማስዋብና ብሎም ፓርኮችና አደባባዮች ቢገነባም በነዚህ ቦታዎች የከተማው ነዋሪዎች የሚቆዝሙበት ሳይሆን  ለአማተር ከያንያን እንዲሁም ለግል የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዞች እድል በመስጠት በነዚህ አደባበዮች የተለያዩ የኪነ ጥበባት ፕሮግራሞች ማለትም የባህል እና ዘመናዊ ውዝዋዜ ፤የስነ ፅሁፍ፤የሰርከስ ትርኢት የሚታይበት መድረክ እንዲሆኑ መስራት ሲያሻ ከተማ አስተዳደሩ ለአማተር የኪነ ጥበብ ፍላጎትና ተሰጥኦ ላላቸው አማተር ከያኒያን እና የኪነጥበብ ቡድኖች በቂ ድጋፍ በማድረግ የነገ የሀገር ተረካቢ የከነ ጥበብ ባለሙያዎች ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ብሎም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡባቸው መድረክ ማመቻቸት  የሚገባው ሲሆን ይህ መሆን ካልቻለ በቀጣይ ለሀገር ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ብቁ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ማግኘት አዳጋች ይሆናል ፡፡

ሌላው የኪነ ጥበብ አንጓ የሆነውን ቲያትር ስንመለከት ከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ታሪካዊውን ሀገር ፍቅር በማሳደስ ወደ ስራ ማስገባቱ በአዎንታዊ ጎኑ ሲጠቀስ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ ወደ ቀድሞ ስራው ወደ ቲየትር ማሳየት መመለስ ባይችል እንኳ ጠንከር ያሉ የኪነ ጥበብ ፕሮግራሞች እንዲካሄዱበት ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለከተማው የኪነጥበብ እድገት የራሱ አበርክቶ እንዲኖረው ማድረግ ሲያሻ ከዚህ ባለፈ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገርያ የነበረው በተለምዶ ሰይጣን ቤት በመባል የሚታወቀው ሜጋ አንፊ ቲያትር /ዋፋ ሲኒማ/ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ወደ ቀድሞ የኪነጥበብ ተግባሩ በማስገባት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ በተለይ አማተር ከያኒያን ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት ብሎም ለከተማው ነዋሪ የጥበብ ፕሮግራሞች መመልከቻ አማራጭ እንዲሆን ማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ይጠበቃል ከዚህ ባለፈም የከተማው ነዋሪ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተዋል የተባሉ አንፊ ቲያትሮች እንዲሁም ሌሎችን ወደ ስራ ማስገባት እና የጥበብ ማእከላት ተዘጋጅተው ህብረተሰቡ ከኪነጥበብ ትሩፋት ይቋደስ ዘንድ ተጨማሪ ስራዎች መስራት ይጠበቃል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መልስ ለኃይሉ የሺወንድም፤ በወልቃይት ፀገዴ ባህልና ማንነት ጥያቄ እኔም ቅሬታ አለኝ!

በሌላ መልኩ ከተማ አስተዳደሩ የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ  ያለው የህትመት ዋጋ ሲሆን ይህም መልኩም በመነቃቃት ላይ ያለውን የንባብና የመጽሀፍት ህትመት ጉዳይ የበለጠ እየተፈተነ ሲገኝ  በከፍተኛ ሁኔታ በናረው የህትመት ዋጋ ሳቢያ ደራሲያን መፀሀፍት ማሳተም እየተሳናቸው ሲሆን ተደራሲያንም አዳዲስ ስራዎች ለማግነት አዳጋች እየሆነባቸው ሲገኝ ይህን ለመቅረፍ የተሸለ ስነ ፅሁፋዊ  እና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸውን መፅሀፍት ሊያበረክቱ የሚችሉ አቅም ያላቸው ደራሲያንን እና የጥበብ ባለማሎች የሚበረታቱበት ስርአት ዘርግቶ የስነ ፅሁፍ አበርክቷቸውን ወደ አንባቢያን በተመጣጣኝ ዋጋ  ይደርስ ዘንድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ድጋፍ በማድረግ በሀገሪቱ ስነ ፅሁፍ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመቅረፍ መንቀሳቀስ በአሁኑ ወቅት ለአፍታ ቸል ሊባል የማይገባው ጉዳይ ነው ፡፡

በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ከላይ በተወሰኑ መልኩ ከላይ እንደተጠቀሰው በተለይ  ለየት ባለ መልኩ ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር እየሰራቸው ያላቸው ሰው ተኮር ተግባራት የሚያስመሰገኑ የበለጠ ሊጠናከሩ የሚገባቸው ሲሆን ከዚህ በመለስ ከተማ አስተዳደሩ ኪነ ጥበብ ለማህበረሰብ ግንባታ እና ለሀገር ልማት ያለውን ፋይዳ በአግባቡ ዋጋ በመስጠት በተለይ የግሉን ዘርፍ የበለጠ በመሳብ በኪነጥበብ ዘርፉ እንዲሳተፉ በሮችን በመክፈት የጀመራቸው በተለይ ሰው ተኮር ተግባሮች ምሉእ ያደርጋቸው ዘንድ በኪነ ጥበብ አፍቃሪያን ስም ጥያቄ እያቀረብኩ ይህ መሆን ባልቻለበት ሁኔታ  የከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት ግማሽ ጎፈሬ ግማሽ ልጪ ከመሆን የማይድኑ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸው በተለይ ቁስ ላይ ብቻ ያተኮሩ ውብ ከተማን ለመፍጠር በማለም እያከናወናቸው ያሉ  ከተማን የማስዋብ እና ሌሎች በቅርቡ በስፋት ሊተገበሩ ዝግጅት እየተደረገባቸው ያሉ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ያለ ኪነ ጥበብ ምሉእ እንደማይሆን በግርድፉም ቢሆን በምትገልፀው ዘመን አይሽሬ የደራሲ በዓሉ ግርማ ግጥም ለሀሳቤ መቋጫ ላድርግ ፡፡ ሰላም

ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር

ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል ሀገር

ህንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ

መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ

ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድን ነው ውበቱ

የኔ ውብ ከተማ የኔውብ አገር

የሰው ልጅ ልብ ነው

የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

4 Comments

  1. “ሀገር ወዳድ ባለሀብቶችን የበለጠ በመቅረብና በማስተባበር የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እየከወነ ይገኛል ፡፡”
    I think you have more than enough outlets under the control of the OPDO (Walta, Fana, ETV, OBN, EMS etc) for your cheap propaganda. ሰው ተኮር? Who is ሰው? You mean there are two types of creatures? Are those people whose homes have been demolished without warning and prevented from renting or even living in shanty shelters in the area not considered ሰው? Do you mean Oromo ተኮር? Even then I doubt if the innocent Oromo people are the true beneficiaries of this apartheid and fascist system.
    The truth is that all the aid is meant to debilitate and make dependent ( not empower ) Addis Ababa residents so they will be unable to resist the Mogassa (Coerced assimilation project) of the OLF

  2. ዶር አብይ ሁሉም ነገር የእምቧይ ካብ ሁኖበታል ከአማራም፤ከኦርቶዶክስም፤ ከሌላውም እልህ ከሚጋባ ጊዜ ወስዶ ወደ ትክክለኛው አለም ቢመለስ መልካም ይሆናል ቢያንስ ልጆች አሉት ሰው ማፈርም ጥሩ ነው ትላንት ትግሬዎች የውሻ ቆዳ ሲያለብሱት አመት ሳይሞላው ያንን ሁሉ ረስቶ መገባበዝ መነጠፍ ምን ይሉታል ያስንቀዋል። ዛሬ የተናገረውን ነገ አይደግመውም እሱ ጋር ቀረቤታ ያላቸው ቀን የሚጠብቁለት መሆኑን መረዳት አለበት አገሩ መቅኖ አሳጣው የሚመርጣቸው ሰዎች ሁሉ ይገርማል ጥፋት ሲያጠፉም ገምግሞ ወይ እርምት ወይ ማባረር የለም ቀጥሉ ጨምራችሁ አጥፉ ነው የሚለው ታከለ ኡማ፤አዳነች አቤብ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ሽመልስ አብዲሳ ፤ሌንጮ ባቲ፤ሱሌማን ደደፎ፤አዲሱ ቂጤሳ/አረጋ እያለ ይቀጥላል…. እነዚህ ሰዎች የስራ ልምድ እንዲያዳብሩ እንጅ በያዙት ቦታ ውጤት ያመጣሉ ተብሎ መቼም አይገመትም።አገሩን እንዳልነበረ ሲያደርጉት በተባራሪም የሰማም አይመስልም። በጊዜ እርምት ባለመውሰዱ ነግሮች ተክማችተው ዛሬ ማጅራቱን ይዘውታል

  3. is that woman Adanece Abebea or Adane Abebe? did she made hormone treatment she looks like male.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share