May 23, 2023
6 mins read

አማራን የማጥቃትና ሀገር የማፍረስ ወንጀል ይቅርታ የለውም፣ ተያይዞ መጥፋትን ያስከትላልና

 ዶ/ር በቀለ ገሠሠ ([email protected])

FwwPCSnWIA81yYz
#image_title

ሀ) የተባረከች ሀገር ነበረች፣

የምድሯን ስፋት፣ የወንዞችዋንና የሃይቆችዋን ብዛትና ግዙፍ  የተፈጥሮ ሃብቶችዋን ስንመለከት በእርግጥ አምላክ ሁሉንም አሟልቶ እንደፈጠራት እናያለን። ውድ ሀገራችን ነፃነቷንም ጠብቃ የኖረችው በአባት አያቶቻችን  ደምና አጥንት ነበር። እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር እየዘረጋች የጌታን  በረከት ትቀበል ነበር (ኢትዮጵያ ታበጽእ እዴዊሃ ሃበ እግዚአብሔር የተባለው ለዚህ ነበር)።

እንግዳ ተቀባይነት፣ ያለውን ማካፈል፣ የወደቀውን ማንሳት፣ የሞተውን አለመርሳት  የመሳሰሉ ቅዱስ ተግባራት ቆንጆ ትውፊቶቻችን ነበሩ።

ለ) ዛሬ ግን እጅግ ከባድ መከራ ላይ ለምን ወደቅን?

ዛሬ ምን መጣና የሰው ህይወት እንደዚህ ረከሰ? እርጉዝ ሴቶችን፣ አረጋውያንና ሕፃናትን እንደዚህ ሲያሰቃዩና ሲጨፈጭፉ እንዴት ኃፍረት አይሰማቸውም?  እያንዳንዳችን ራሳችንን እንጠይቅና መልስ እንፈልግ፣ እንታረም።

እግዚአብሔር ባምሳሉ የፈጠረን እንድናስብና በጎውን ከክፉ እንድንለይ ነው። ከከብቶች በታች ሆነን የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ ሆነን ስንገኝ እጅግ በጣም  ማዘን ይኖርብናል። ንፁሀን ምስኪን ዜጎችን መግደል፣ ማፈናቀልና ማሰቃየት ለምን ተመረጠ? ይሄ ከእግዚአብሔርና ከስብዕና ጋር ክፉኛ እንደሚያጋጫቸው እንዴት ማወቅ ተሳናቸው? ይዋል ይደር እንጂ በፍርድ ቤቶችም ሊያስጠይቁ እንደሚችሉ ማወቅ እንዴት ተሳናቸው? ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ዕድሜ ልካቸውን በኃፍረት እየተሸማቀቁ እንዲኖሩስ ለምን ተመረጠ?

ሕፃናትን መንከባከብና ማስተማር ሲገባ ለጦርነትና ለስደት መማገድ ትልቅ ኃጢአት መሆኑስ እንዴት ተረሳቸው?

ገበሬው ወጥቶ በሰላም ካላረሰ፣ ነጋዴው በሰላም ተዘዋዉሮ ካልነገደ ምን ሊበላ ነው?

አማራ ወይም ኦርቶዶክ ስለሆኑ ብቻ እየተመረጡ የሚጨፈጨፉት ዜጎች ደም ወደእግዚአብሔር ይጮሃል።  ደጋግሜ እንደጠቀስኩት ውዲቷ አገራችን የምድር ላይ ገነት ናት። ይህችን የመሰለች ቅድስት አገር ማውደምና ማፍረስስ ለምን አስፈለገ? ማንን ለመጥቀም ነው? ተያይዞ መጥፋት ካልሆነ ማንም በተናጠል ሊጠቀም እንደማይችል ማወቅ አለባቸው።

ሕዝባችን ለብዙ ሺ ዓመታት በነፃነት ወጥቶ በሰፈረበት ምድር ላይ እዚህ አትገቡም፣ እዚያ አትኖሩም እያሉ ንፁሃን ዜጎችን መጨፍጨፍና ማፈናቀል ምን ይባላል?

ውሎ ሳያድር ተንበርክከን ከእግዚአብሔር ይቅርታን እንጠይቅ፣ ንስሐ እንግባ። እያንዳንዳችን በሚከተሉት መንገዶች ግዳጃችንን እንወጣ።

ሐ) የመንግሥት ዋናው ኃላፊነት የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ማስጠበቅ ነው። የተጎዱትን መንከባከብ ነው። የመከላከያ ኃይሎች ዋና ኃላፊነት ድንበሮቻችንን መጠበቅ ነው። የፓሊስ ሠራዊት ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብና ፀጥታን ማስጠበቅ ነበር። እነዚህ ሁሉ ዛሬ አይታዩም።

መ) የኃይማኖት አባቶች ኃላፊነት የተሸከሙትን የጌታ መስቀልና ቁራን ማክበር፣ ለሰላም መጸለይና እውነትን መመስከር ነው።

ሠ) የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብን ማቀራረብና የተጋጩትን ወገኖች ማስታረቅ ይጠበቅባቸዋል።

ረ) ወጣቶች በዘርና በኃይማኖት መከፋፈል የለባቸውም። ነግ በኔ ብለውም  ማሰብ ያስፈልጋል። ስለዕውነት መቆም አለባቸው። ለመብት በጋራ መታገል ይጠበቅባቸዋል። ሀገር ለመረከብ መዘጋጀት አለባቸው።

በመጨረሻ እየተካሄደ ያለው በተለይ አማራውን የማሰቃየት የእብደት ዘመቻ ቶሎ መቆም እንዳለበት በአጽንዖት ላሳስብ እወዳለሁ።

 

የጭቁኖች አምላክ እርዳታ አይለየን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop