May 18, 2023
5 mins read

ማደናቆር ማሸጋገር ነዉን ?

Abiy is a killer e

የኢትዮጵያ አንድነት እና የሕዝቦች ሉዓላዊነት  ከፈተና አልፎ ኢህአዴግ መጋኛ  ከሆነባቸዉ ግንቦት ሀያ ቀን ሽ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ጀምሮ አስከዛሬ ተደርሷል ፡፡

Abiy is a killer eዛሬም ብአዴን ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የሚያዜመዉ  የሕዝብ መብት እና የአገር አንድነት ከመከራ ወደ መከራ በተሸጋገረ  ቁጥር  አለን ለማለት የህዝብን ቁስል እና በደል  ችላ በማለት ሲነፍስበት እኔ ላሻግር ሲል ግማሽ ምዕተ ዓመታት አለፉ ፡፡

በለፈለፉ ….አንዲሉ አበዉ ብአዴን ኢትዮጵያ የግዛት አንድነቷን የሚጎዳ አደረጃጀት ሲመሰረት ፣ ዓማራ እንደ ህዝብ በጠላትነት ተፈርጆ ሲሳደድ እና በመላዉ አገሪቷ በሶስተኛ ደረጃ ዜግነት ሲቆጠር ፣ በማንቱ የፖለቲካ ዉክልና እና የህግ ከለላ ሲነፈገዉ  በዚህም በማንት ፍጂት እና ዕልቂት ሲካሄድበት  ከዚህ በላይ በአማራ ህዝብም ሆነ ከኢትዮጵያ አንድነት አደጋ መግባት ምን ይኖራል ብሎ ነዉ ብአዴን በየጊዜዉ  ከዕንቅልፉ ሲነሳ ከፈተናዎች ለማሻገር ብሎ ማደናቆር ፡፡

አስኪ ክልሎች ሲደራጁ  በስያሜም ይሁን በይዘት  እንደ ዓማራ እና ኢትዮጵያ የተጎዳ ወይም ቤተ ሙከራ የሆነዉ የትኛዉ ክልል ነዉ ፡፡

ዓማራ ክልል ዓማራ ከተባለ የብሄር ብሄረሰብ የአዉራጃ መስተዳደር መኖር ለዓማራ ክልል እና ህዝብ ሲሆን እና በሌለች የአገሪቷ ክፍል ግን መንገድ ላይ ዕግር ለመታ ዕንቅፋት ለማንሳት የቦታዉ ብሄረሰብ መሆን በሚጠየቅባት አገር ብሄራዊ አንድነት እና አብሮነት የሚፀናዉ በዕኩልነት አስከሆነ በመላ አገሪቷ  የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሆኑ ዓማርያን የፖለቲካ ዉክልና እና ራሳቸዉን በራሳቸዉ የማስተዳደር ህጋዊ ዋስትና ሲነፈጋቸዉ እና የዘመናት አድሎ እና መድሎ ሲደርስባቸዉ እያየ ያለፈ አሻጋሪ ዛሬ እንዴት ይሆን ኢትዮጵያን የሚሻግር፡፡

ኢትዮጵያ እንደ አገር ኢትዮጵያዉን እንደ ህዝብ በተለይም ዓማርያን በፀረ-ኢትዮጵያዉን ጠላቶች  በተጠነሰሰ  የጥላቻ ፖለቲካ በአገራቸዉ የመኖር እና ሰርቶ የማግኘት ተፈጥሯዊ መብተቻዉ በማን አለብኝነት ተገፎ ያለከልካይ አሁን በሚገኙበት ቀዉስ ዉስጥ መድረሳቸዉ እየታወቀ ይህ ፈተናዎችን ወደ ድል ከማለት በህዝብ እና በአገር ላይ እየደረሰ  ያለዉን የጨለማዉ ዘመን መከራ እና ግፍ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ  ባለበት ለማስቀረት የዚህ ሁሉ አስኳል የሆነዉን ኢህአዴግ ማክሰም እና አገሪቷን ወደ ቀደመ አንድነቷ እና ታላቅነቷ ፤ ኅዝቡንዳ  ተሟላ ሉዓላዊ ነጻነት እና ክብር ሊያደርስ ወደ ሚችል ብሄራዉ እና ህዝባዉ መንግስት ቢባል በጥቂቱም ቢሆን  በሽግግር ስም ከማደነጋገር ወደ ወደ ዕዉነተኛ ቁም ነገር ይለወጥ ነበር ፡፡

የኢትዮጵያም ሆነ የዓማራ ህዝብ ችግር የመሰሪ እና የአደንቋሪ ዕንቅፋት መኖር እንጂ ከመሻገር አልፎ በራሱ  መብረር የሚችል ህዝብ መሆኑን መረዳት ከመደነቋቆር ወደ መተባበር ያደርሳል ፡፡

ዝንተ ዓለም በአገር እና ህዝብ ህመም የፖለቲካ ትኩሳት ለማስታመም ሽግግር  እና ተሀድሶ  መልሶ መላልሶ የሞኝ ለቅሶ ለህዝብ እና ላገር ችግር አይሆንም ፡፡

 

Allen Yet men!

 

Unity is strength!

 

https://youtu.be/f88ze8pGfO0

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182680
Previous Story

የአዲስ አበባ ክልልነት ድምጽ ተሰማ፣ የአማራ ብልጽግና የዛሬው ውሎ፣ ከሸኔ ጋር በከባድ መሳሪያ ውጊያ ተጀመረ፣ የፈረሱት መስጊዶች 13 ደረሰ

182687
Next Story

ጨቅጫቃ አጋር እና አሮጌ መኪና አትስጠኝ…” | ፍራሽ አዳሽ | ተስፋሁን ከበደ | ጦቢያ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop