እናቷን አባቷን ባለቤቷን ሶስት ልጆቿን እህቷን ከአራስ ልጇ ጋር ወንድሟን ከአራት ልጆቹ ጋር በአጠቃላይ ሃያ አንድ ቤተሰቦቿን በግፈኞች የተገደሉባት ምስኪን እህታችን ናት ። ጠይባ ሁሴን መሐመድ ትባላለች ።
ጠይባ ሁሴን መሐመድ በዱባይ ለሰባት ዓመታት ፣ በሳዑዲ አረቢያ ደግሞ ለስምንት ዓመታት ሰርታለች ። በሰው አገር የተንከራተችላቸው ቤተሰቦቿ ወለጋ ጊቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ምንም ባላወቁት ሁኔታ ተገድለውባታል ።
በ1977 ዓ/ም ከኮምቦልቻ እና ከከሚሴ እናት እና አባቷ ወደ ወለጋ እንደሄዱም ሰምቻለሁ ። ጠይባ የተወለደችው ወለጋ ነው ።
ምን ብለን የትኛውስ ኃይለ ቃል ነው የሚያጽናናት !?
EthioVoice.net