May 9, 2023
13 mins read

አብይ አህመድ በዐማራው ሕዝብ ላይ የከፈተውን አረመኔያዊ ወረራ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

For Immediate Releasse

ግንቦት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
ሜይ 9 ቀን 2023 (May 9, 2023)

አብይ አህመድ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የፈፀመው አረመኔያዊ መንግሥታዊ ሽብር አሁን በዐማራው ሕዝብ ላይ ለከፈተው መጠነ ሰፊ ፋሺስታዊ ወረራ እንደ ገፊ ምክንያት እንዲወሰድለት የሸረበው እርኩስ ሴራ ነው::

እኛ በተለያዩ ዓለማት የምንገኝ ሲቪክ ድርጅቶች አብይ አህመድ በዐማራው ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ፋሺስታዊ የዕብሪት ወረራና ጭፍጨፋ አጥብቀን እናወግዛለን:: የኢትዮጵያ ሕዝብም እንዲያወግዘውና ከተወረረው የዐማራ ሕዝብ ጋር በመቆም ይህን አስከፊ ሥረዓት ለማስወገድ ለመራራ ትግል ቆርጦ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን::

የአብይ አህመድ ሠራዊት በሰሜን ሸዋ፣ በራያ ቆቦ፣ በሰሜን ጎንደርና በሌሎችም አካባቢዎች በዐማራው ሕዝብ ላይ አረሜኒያዊ ጭፍጨፋ እያካሄደ ይገኛል:: ብዙዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ እንስሳት ሳይቀሩ በከባድ መሳሪያ እየተደበደቡ ይገኛሉ:: ዐማራውን እንዲጨርስ ከተላከው አብዛኛው ሠራዊት የኦሮሞ ልዩ ኃይል ቢሆንምቁጥሩ ቀላል የማይባል የመከላከያ አባላት ደጀን የሆነውን የዐማራ ሕዝብ አንወጋም ብለው ከሠራዊቱ ራሳቸውን ያገለሉና መሳሪያቸውን ይዘው ከፋኖ ጋር የተቀላቀሉ መሆናቸውን ሰምተናል:: ይህ የሚያስመሰግን ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተስፋ እንጠብቃለን::

የአብይ ህመድ ፋሽሽታዊ መንሥት የዐማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻውና ፋኖ በጠላት ወያኔ ላይ ትላልቅ ድሎችን እያስመዘገበ ባለበት ጊዜ ነበር “በድህረ ጦርነት የድል ሽሚያ ፈተና” በሚል ፅሁፍ ሰንዶ ፋኖን እንዴት ማጥፋት እንዳለበት አቅዶ የተነሳው::

ይህንን ሰይጣናዊ እቅዱን እውን ለማድረግ ፋኖን “ኢመደበኛ ሠራዊት” በሚል እንዲፈርስ አውጆ ባልተዘጋጁበት እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ፋኖወችንና የልዩ ኃይል አባላትን “በህግ ማስከበር” ሰበብ እስር ቤት ጨምሮእቸው እስካሁን ከዓመት በላይ በእስር እንዲማቅቁ አድርጓል። ዛሬ፣ ግልፅ ወረራ በዐማራው ላይ በመክፈት፣ ህፃን፣ ሴት፣ ሽማግሌ ሳይለዩ በመጨፍጨፍ ላይ ናቸው። ይህንን ግልፅ ወረራ ከመፈፀሙ አስቀድሞም፣ በአዲስ አበባ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ዐማራወችን እስር ቤት ጨምሮአል:: ከ 40 ሺህ በላይ የዐማራ ተወላጅና ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን ቤቶች ከአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉት ከተሞች አፍርሶ አፈናቅሎአል:: ቤት እንዳይከራዩና ወደ ሌላ ዘመድ ጎረቤት እንዳይጠጉ ክልከላ በመጣል እንዲሰደዱ አድርጓል:: ባጃጅ የሚነዱ፤ ሎተሪ የሚያዞሩ ዜጎችን ዐማራ ናችሁ በማለት ከሥራቸው እያስትጓጎለ ንብረት እየቀማ እያሰቃያቸው ይገኛል::

የዐማራ ባለ ሀብቶችን በሕገወጥ መንገድ ከመሬት ተነስቶ በመፈረጅ ንግዳቸው እንዳይሠራ እገዳ ጥሎአል::

ፋሽስታዊው አገዛዝ ራሱ ሽብርተኛ ሆኖ እያለ፣ ጋዜጠኛችና ምሁራን በሃሳብ ስለሞገቱትና ነውሩን ስላጋለጡበት፣ ሽብርተኛ ብሎ ዘብጥያ አውሮዶአቸዋል:: በዚህ ሰሞን በአዲስ አበባ ብቻ ወደ 20 ሺህ የሚሆኑ ዐማራወችን አፍሶ እንዳሰራቸው እየተዘገበ ይገኛል:: የዐማራው ተወላጅ እየተመረጠ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በመደረግ ላይ ይገኛል:: አብይ አህመድ በዐማራው ሕዝብ ላይ የከፈተውን

ይህን ሁሉ ዝግጅት አድርጎ ሲጨርስ በዐማራው ሕዝብ ላይ የከፈተው ወረራ በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ተቀባይነት እንዲኖረው በማሰብ፣ የራሱ ፓርቲ ፣ የዐማራ ክልል ኃላፊ የነበረውን አቶ ግርማ የሺጥላን እንዲገደል አድርጓል:: ይህን የተለመደ ሴራውን፣ ራሱ አስገድሎ “ገዳዮች እንኝህ ናቸው” ብሎ ከፓሊስ ምርመራ ቀድሞ ማወጁ፣ የእነ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ ምግባሩ ከበደ፣ እዘዝ ዋሴ፣ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ፣ ጄኔራል ሰሀረ መኮንን፣ ኢንጅነር ስመኘው በቀለና፣ ኮሚሺነር አበረ አዳሙን አገዳደል ያስታውሳል::

ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን የአብይ አህመድን በዐማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ግልፅ የእብሪት ወረራ ማውገዝና ለህልውናው መከበር ከሚዋደቀው የዐማራ ሕዝብ ጎን ሊቆም ይገባል::

የዚህ ወረራ መነሻ ምክንያቱ ሕግ ለማስከበር ነው የሚለውን ፌዝ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ አይገመትም:: የወረራው ዋነኛ ምክንያቶች ዐማራውን አንገት አስደፍቶ፣ ወልቃይትና ራያን ለህወሓት ማስረከብና፣ እንዲሁም የኦሮሙማውን እጅግ ፈጣን የሆነ መስፋፋትና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ታላቂቱን ኦሮሚያ ለመመሥረት የሚደረገውን ምኞት ማሳካት ናቸው::

በዚህ ጦርነት ዐማራው በዋናነት የሚታገለው የራሱን ህልውና አስከብሮ ኢትዮጵያውያን ከመፍረስ በመታደግ ሁሉም ነገዶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነትና በፍትሕ ሊተዳደሩ የሚችሉበት ሥረዓት ለማምጣት ነው ብለን እናምናለን:: ይህንን ትግል ሁሉም ነገዶች ህሉም ኢትዮጵያውያን ዛሬ ነገ ሳይሉ ሊቀላቀሉትና ሊያግዙት ይገባል::

የጽንፈኛውን ኦሮሙማ ግሥጋሴ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ በቶሎ ካላስቆሙት ውጤቱ፣ በ16ኛው ክፍለዘመን እንደነበረው 28 ነገዶችን አጥፍቶ የሚቆም እና ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለመኖር ብቻ ሳይሆን፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ትውፊትና እሴቶች በሙሉ ተደምስሰው ፣ ብዙ ሕዝብም እንዲያልቅ የሚደረግ መሆኑ ነው::

ስለዚህ የዘገየ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአስቸኳይ በዐማራው ላይ የተደረገውን አረመኔያዊ ወረራ በመቃወም የዐማራውን ትግል በመደገፍ፣ የሚከተሉትን ጥሪዎች እንዲቀበል እንጠይቃለን፤

  1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አብይ አህመድ በዐማራው ላይ የፈፀመውን ፋሽስታዊና አረመኔያዊ ወረራ እንዲያወግዝና በአስቸኳይ ወረራውን በማቆም ጦሩን ከዐማራ ክልል እንዲያወጣ ግፊት እንዲያደርግ
  2. የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደም መላሽህና ደጀንህ በሆነው የዐማራ ሕዝብ ላይ አንዳትተኩስ ይልቁንስ አገርን ሃይማኖትን ታሪክንና ቅርስን ሊያወድም ቆርጦ የተነሳው አብይ አህመድ ላይ ተገቢውን ተቃውሞ እንድታሳይ
  3. ሌሎች ክልሎች ተራ በተራ በኦሮሙማው ኃይል ከመበላት ለመዳን ዛሬ ነገ ሳይሉ በሚችሉት ሁሉ ከዐማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ: ወራሪውንም ለመቀልበስ ተግተው እንዲሠሩ
  4. ከሁሉም በላይ የሕልውና አደጋ የተደቀነበት የአዲስ አበባ ሕዝብ በአስቸኳይ በዐማራው ላይ የተፈፀመውን ወረራ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ተቃውሞውን እንዲያሰማ
  5. የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማሕበራት ግልፅና የተባበረ ወረራውን የሚቃወሙ ሥራዎች እንዲሠሩ ሕዝቡንም ለትግል እንዲያዘጋጁ
  6. የሃይማኖት ተቋማት ወረራውን በማውገዝ መንግሥትን እንዲያስጠነቅቁ እንዲሁም ለምዕመናን ጥሪ እንዲያደርጉ
  7. ለኦሮሙማው ኃይል ያላጎበደዳችሁ የዐማራ ክልል አመራሮች የዞን የወረዳ የከተሞች ቀበሌ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት ከሕዝባችሁ ጎን በመቆም ወረራውን ለመቀልበስ ተግታችሁ እንድትሠሩ ከሕዝቡ ትግል ጎን እንድትሆኑ
  8. ሚዲያዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ወረራ በማሳወቅና የኦሮሙማን የሴራ ጉዞ እያጋለጣችሁ ያለውን አኩሪ ተግባር አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉበት
  9. በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የኦሮሙማው ኃይል ቀንደኛ ጠላቱ አድርጎ ከፈረጀውና የእብሪት ወረራ ከተከፈተበትና ከተገፋው የዐማራ ሕዝብ ጎን በመቆም ወረራውን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በማሳወቅ ረገድም ሆነ በአገዛዙ ላይ ከተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ዶላር እንዳያገኝ ከሚደረገው ጥረት አካል እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን:: በአብይ አህመድ ሠራዊት የተወረረው የዐማራ ሕዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕፎይታና ሠላም የሚያገኘው አብይ አህመድ የሚመራው መንግሥት ከነ ሥረዓቱ ሲወገድ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለተጠናከረ ትግል ቆርጦ መነሳት ይኖርበታል:: እኛም የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን::

የኦሮሙማ አገር የማፍረስ ታሪክ የመደምሠስ ሃይማኖት የመከለስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ይከሽፋል!
ዐማራው የተከፈተበትን ወረራ በድል በማጠናቀቅ የራሱን ብሎም የኢትዮጵያን ህልውና ያስከብራል!

 

ፈራሚ ድርጅቶች

SIGNATORY ORGANIZATIONS

1. Abba Bahrey Forum
2. Adwa Great African Victory Association (AGAVA)
3. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association
4. Amhara Dimtse Serechit
5. Amhara Wellbeing and Development Association
6. Communities of Ethiopians in Finland
7. Concerned Amharas in the Diaspora
8. DC Task Force
9. Embilta Forum
10. Ethio-Canadian Human Rights Association
11. Ethiopian Community Association of Greater Cincinnati (ECAGC)
12. Ethiopian Dialogue Forum (EDF)
13. Freedom and Justice for Telemt Amhara
14. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
15. Global Amhara Coalition (GAC)
16. Gonder Hibret for Ethiopian Unity
17. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation
18. Network of Ethiopian Scholars (NES)
19. Radio Yenesew Ethiopia
20. Selassie Stand Up, Inc.
21. The Ethiopian Broadcast Group
22. Vision Ethiopia (VE)
23. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop