ካልተስማሙ የምናዉቀዉ ቀደም ሲል በነበረዉ አቋም ላይ መሆናቸዉን ነዉ

ከሰሞኑ በኢአሀዴግ እና በኦነግ የጦር ተፋላሚዎች ጋር በታንዘኒያ አገር በምትገኝ አገር ለቀናት ተካሂዶ ያለምንም ስምምነት መቋጨቱን እና ይህም ለቀጣይ ጊዜ በይደር መያዙን ይሰማል ፡፡

ሰማን ለማለት ከልምድ መቀበል ስለሚያስቸግር እና ግልፅነት ያለዉ ይፋዉ የመረጃ ልዉዉጥ በአገራችን ባለመለመዱ ነዉ ፡፡

ይሁንና ከአራት ዓመት በፊት ኤርትራ ከነበረዉ ኦነግ ዉስጥ የገጠሩ ክንፍ ከነሙሉ ትትጥቁ  መግባቱ እና ይህም አድማሱን በማስፋት ከምዕራብ ኢትዮጵያ አስከ መኃል አገር መዛመቱን ይነገራል ፡፡

በተጨባጭ እየደረሰ ባለዉ ሠባዊ እና ቁሳዊ ጥቃት እና ዉድመት የተነሳ ንግግር አስፈላጊ መሆኑ እና የሁሉም ሠባዊ ፍጡር ፍላጎት ቢሆንም ስምምነቱ ስለመካሄዱም ሆነ ስለዉጤቱ መተማመን የሚያስችል ስለመሆኑ ተከድኖ ይብሰል ፡፡

ለመሆኑ በሰላማዊ መንገድ መብታቸዉን ፣ ህልዉናቸዉን እና አገራቸዉን ለመከላከል ከፍተኛ ዋጋ የለፈሉትን ኢትዮጵያዉያንን በመዘንጋት እና በተለያየ መንገድ በመጉዳት በመጠመድ ከዚህ በተቃራኒ አስቀድሞ ከነሙሉ ትጥቅ ወደ አገር ቤት የገባን ኃይል  በስምምነት ተቀብሎ ዛሬ ኢህአዴግ ለመስማማት ቢራመድ ሰዶ ማሳደድ እና እንዲሁም የፖለቲካ ስልጣን ጉዳይ ካልሆነ የአገር እና የህዝብ ጉዳይ መሆኑ ሌላዉ ተጠባቂ እና ተጠያቂ ወቅታዊ ጉዳይ ነዉ ፡፡

ለዓመታት እንደ ጂረት የሚወርደዉ የዜጎች ዕንባ እና ደም ሲፈስ ፣ ህዝብ ሲፈናቀል ፤ ዜጋ ሲበደል ፣ ፍትህ ሲጓደል አንድም ስለ ህዝብ እና አገር ለመናገር ሀነ ለመዘከር ፍላጎት የሚያሳይ አካል ባለመኖሩ

ዛሬ ላይ ከብሄራዊ ደህንነት እና የህዝብ አንድነት ስም ድርድር ማለት በአሁኑ ጊዜ ለብሄራዊ አንድነት  ቀናኢ ከሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ  ህዝብ እና የዓማራ ብሄራዊ ነፃነት ትግል (አብነት) ኃይሎች ላይ በአገራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ መታማት  ከተለያዩ ኃይሎች ጋር ለሰላም እና ለአገራዊ አንድነት ስለመሆኑ አጠያያቂ መሆኑ ከግምት በላይ ዕዉነት መሆኑን የሚጠራጠር ቢኖር በዕዉነት የማይኖር ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ስለ … ። ሲባል ምርጫ ይቅር” …። ትግልም ይቁም ወይ?

በብዕር እና በተግባር የሚሞግቱ ጉምቱ ኢትዮጵያዉያን በሚገፉበት ምድር ሳይረራቁ የሚታረቁ  ስምምነት ላይ መድረስ አለመድረሳቸዉ ይቆይ እና በቀደመዉ ስምምነታቸዉ ላይ ምን ተካቷል የሚለዉን መጠርጠር ሳይሻል አይቀርም ፡፡

በታንዛኒያዉ የኢህአዴግ እና የኦነግ ወታደራዊ  ክንፍ  ጋር ታንዛንያ ላይ የተካሄደዉ ንግግር የቀደመዉን የአስመራ ስምምነት ለማደስ እና በአገሪቷ ላይ ለደረሰዉ የሠላሳ ዓመታት ሠባዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ተጠያቂዉ ማን ይሁን የሚለዉን አሁንም ቢብራራ እና ህዝብ እንዲያዉቀዉ ቢሆን በጎ ነገር ነበር ፡፡

እናም ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ  እንዲሉ አለመስማማት የሚለዉን ይቅር እና የተስማሙበትን ሁለቱ “ተስማመተዉ ያልተስማሙበትን ነገር “ ስለ አገር እና ህዝብ ቢናገሩ ፤ቢኖሩ ሁሉም ደስ ይሰኛል ፡፡

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Allen

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share