ከፈሪነት የሚቆጠር ያማራ ሕዝብ አጉል ጨዋነት
ጠላትህን ውደድ የሚለው ብሂል የሚሠራው በመንግስተ ሰማያት ለሚመሰለው ለተምኔታው (utopian) ዓለም ነው፣ እዚያ ዓለም ላይ ማንም የማንም ጠላት አይደለምና፡፡ በእውናዊው (real) ዓለም ግን ጠላት ማለት ስለሚጠላህ ልትጠላው የሚገባ ማለት ነው፡፡ መሪር ጠላትህን አምርረህ ልትጠላ፣ የሕልውና ጠላትህን ደግሞ ሕልውናውን ልትጠላ ይገባል፣ በጽኑ ያልጠላኸውን በጽኑ አትታገለውምና፡፡
ለምሳሌ ያህል የኦነግ መንጋ አማራ ሲያርድ ዶሮ ያረደ የማይመስለው አለቆቹ አማራ አውሬ ነው እያሉ ደጋግመው ስላስተማሩት የማርደው አውሬ እንጅ ሰው አይደለም ብሎ በጽኑ ስለሚያምን ነው፡፡ ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሕልውናውን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱትን አረመኔወች ሳያጠፉት በፊት ሊያጠፋቸው የሚችለው፣ አረመኔነታቸውን በሚግልጹ አጠራሮች እየጠራ አምርሮ ሲጠላቸው ብቻ ነው፡፡
ጥድ አለቦታው ብሰና ይሆናል እንዲሉ፣ ጨዋነትና ይሉኝታ ትርጉም ያላቸው ለሚያውቃቸው ብቻ ነው፡፡ በወያኔና በኦነግ መዝገበ ቃላት ውስጥ ደግሞ ጨዋነትና ይሉኝታ ድራሻቸው የለም፡፡ ከአማራ ሕዝብ ዐብይ ድክመቶች ውስጥ አንዱና ዋናው ደግሞ ጨዋነት ፊረነት ለሚመስላቸው ለወያኔወችና ኦነጎች አጉል ጨዋ ለመሆን አጉል መጣሩ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ወያናዊና ኦነጋዊ የሕልውና ጠላቶቹን እኩይነታቸውን በሚገልጽ አጠራር አለመጥራቱ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል የኦነግ ኦቦወች አጤ ምኒሊክ መሪር ጠላታችን ናቸው ብለው ስለሚያምኑ፣ ኦነጋዊ መንጋቸው እንደነሱ አጤ ምኒሊክን አምርሮ ንቆ አምርሮ እንዲጠላ ለማደረግ፣ አጤ ሚኒሊክን ሁልጊዜም የሚጠሯቸው በስድብ፣ በማብጠልጠል፣ በንቀትና በማዋረድ ነው፡፡ በተለይም አጤ የሚለውን የከበሬታ ቅጽል ላለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ጥረታቸው ደግሞ አመርቂ ውጤት አግኝተውበታል፡፡ ባሁኑ ጊዜ አጼ ሚኒልክን እያሳነሰና እያኮሰሰ በማዋረድ እንጅ በክብር የሚጠራ ኦሮሞ የለም ከሚባልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
ያማራ ሕዝብስ፣ የኦነጉን ጠቅላይ ሚኒስትርና ኦነጋዊ ሠራዊቱን ምን ብሎ ይጥራቸው?
ዐብይ አሕመድ ወይስ ጭራቅ አሕመድ?
በመጀመርያ ደረጃ የኦነግ አለቃ የሆነውን የአቶ አሕመድ ልጅ ነኝ የሚለውን የሰው ባሕሪ የሌለውን እኩይ ፍጡር እንውሰድ፡፡ ይህ የሰው ባሕሪ የሌለው እኩይ ፍጡር አማራን ቆረጣጥሞ በልቶ ካልጨረሰ የማይጠረቃ በላዔ አማራ ጭራቅ ለመሆኑ ከተግባሩ በላይ ምስክር የለም፡፡ ስለዚህም የአማራ ሕዝብ በዚህ ኦነጋዊ ጭራቅ ተበልቶ እንዳያልቅ እታገላለሁ የሚል ማናቸወም ግለሰብ፣ ቡድንም ሆነ ሚዲያ ይህን ጭራቅ መጥራት ያለበት ጭራቅነቱን በማጉላት ብቻ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ይህን ኦነጋዊ ጭራቅ አንቱ፣ እሳቸው፣ እርስወ እያለ አክበሮ በመጥራት የአማራን ሕዝብ ልብ መክፈል፣ መከፋፈል የለበትም፡፡ ጭራቅን የሚያከበር ጭራቅ ወይም የጭራቅ ተቀጣሪ ወይም ደግሞ ጭራቅ ወዳድ ብቻ ነው፡፡
ይህ ኦነጋዊ ጭራቅ ላማራ ሕዝብ ጠቅላይ ወንጀለኛ (prime criminal) እንጅ ጠቅላይ ሚኒስቴር (prime minister) አይደለም፡፡ ስለዚህም ይህን ኦነጋዊ ጭራቅ በማዕረግ መጥራት ካስፈለገ መጠራት ያለበት ጠቅላይ ወንጀለኛ ጭራቅ አሕመድ ተብሎ እንጅ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ ተብሎ አይደለም፡፡ የሰው ማዕረጉ ምግባሩ እንጅ መንበሩ አይደለም፡፡
ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት የቻለው የሕልውና ጠላቱ እሱና እሱ ብቻ መሆኑን የአማራ ሕዝብ በጽኑ ተረድቶ፣ በጽኑ ጠልቶት፣ በጹኑ ስላልታገለው ብቻ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ወያኔም ኦነግም ሳይሆኑ ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ሲሞት ወያኔ እንደተፍረከረከ፣ ጭራቅ አሕመድም ሲወገድ ከመሬት አንስቶ ሰማይ ያደረሰው ኦነግና፣ ከሞት አፋፍ አንስቶ እንዲያንሰራራ ያደረገው ወያኔ ሁለቱም ይፍረከረካሉ፡፡
ግራኝ አሕመድ ዛንተራ ላይ ወደቀ፡፡ ጭራቅ አሕመድስ የሚወድቀው የት ይሆን? ሰንጋተራ?
ኒወርከኛ (The New Yorker) የተሰኘው ያሜሪቃ መጽሔት ጭራቅ አሕመድን በተመለከተ በዘገበው ዘገባ ላይ (September 28, 2022) እኔ ስልጣን ስለቅ ሚሊዮኖች እንደሚያለቅሱ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ ማለቱን ጽፏል፡፡ (“When I leave office, I am one hundred percent sure – one hundred percent sure – that millions of Ethiopians will cry”). ውነት ተናግሮ የማያውቀው ውሸታሙ ጭራቅ አሕመድ እዚህ ላይ ግን ውነት ተናግሯል፡፡ ጭራቅ አሕመድ ሲወገድ ሚሊዮኖች እንደሚያለቅሱ መቶ በመቶ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ለቅሷቸው ግን የሐዘን ለቅሶ ሳይሆን፣ ትልቁ ፀራማራ ጭራቅ ስለተወገደ የደስታ ለቅሶ ነው፡፡
የሀገር መከላክያ ሠራዊት ወይስ የጭራቅ አሕመድ ጭራቅ ሠራዊት?
መከላከያ ማለት የሚከላከል ማለት ነው፡፡ ለስሙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚባለው ደግሞ ካማራ ገዳዮች ጋር በቀጥታና በተዛዋሪ እየተባበረ አማራን ሲገደልና ሲያስገድል እንጅ ሲከላከል ታይቶ አይታወቅም፡፡ ስለዚህም፣ ያማራን ሕዝብ በተመለከት ይህ ሠራዊት ገዳይ እንጅ ተከላካይ አይደለም፡፡ ባለመሆኑም ያማራ ሕዝብ ይህን አማራ ገዳይ ሠራዊት ሊጠራው የሚገባው ጭራቃዊ ተግባሩን በሚገልጽ አጠራር የጭራቅ አሕመድ ጭራቅ ሠራዊት ብሎ ነው፡፡ ይህን አማራ ገዳይ ሠራዊት መከላከያ ብለው መጥራት ያለባቸው አማራ አራጅ ኦነጎች ብቻ ናችው፣ የሚከላከለው እነሱንና እነሱን ብቻ ነውና፡፡
ይህ አማራ ገዳይ ሠራዊት እንደ ስሙ ያገር መከላከያ ሠራዊት ቢሆን ኖሮ፣ አጣየ ዐመድ ስትሆን የት ነበር? ከዋና መሥርያ ቤቱ እፍንጫ ሥር ቡራዩ ላይ አማሮቸና ጋሞወች በመቶወች ሲታረዱ የት ነበር? የቢዛሞ (ወለጋ) አማሮች በሚሊዮኖቸ ሲታረዱና በሚሊዮኖች ሲፈናቀሉ የት ነበር? የመተከል (ቤንሽንጉል) አማሮች በግሬደር ሲቀበሩ የት ነበር? የሱዳን ወታደር የጦቢያን መሬት ወርሮ ሲቆጣጠር የት ነበር? ሀገር የሚከላከሉትን ያማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ለመውጋት ግን ወፍ አልቀደመውም፡፡ ስለዚህም ሥራው ያገር ተከላካዮችን መውጋት ብቻ የሆነ ሠራዊት፣ ያገር መከላከያ ሠራዊት የሚባለው በምን እሳቤ ነው?
መስፍን አረጋ