April 6, 2023
1 min read

የበደል ሀገር!! – ከ ያሬድ መኩሪያ

ሚያፈቅርሽን የማታውቂ፣የሌባ መሸሸጊያ ነሽ
ሲግጡሽ ነው ያንቺ ፍቅር፣እያደር የሚብስብሽ::
ፈራርሰን ወላልቀን፣አልፋ ወ ኦሜጋ ሞተን ልንበሰብስ
ስጋን ለማደለብ፣እውነት እየካዱ ዛሬን መተራመስ::
መቼም አያልፍልሽ፣ፈር ስቷል አውራ መንገድሽ
ሚሠራ ሚለፋ ሳይሆን፣መንታፊ በመወሸምሽ
አዎ እናገራው፣ዐይቶ ካዲ ነው ምድርሽ
ሚያስብልሽን ስገፊ፣መች ለከት አለው በደልሽ?::
ምስሽ እንኳን አይታወቅ፣ስውር ነው ያንቺ ገበና
እንኳንስ በሰው ልጅ ዕድሜ፣በአቡሻክርም አይገባ::
ብቻ ለብልበሽ ገደልሽን፣ከስተት ሳትታረሚ
የቆመውን እየቀበርሽ፣መጭውን ስትቀበኢ
“ሽልም ከሆነ ይገፋል፣ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል”
ሚባለው ተረት አልሰራም፣ከቶ በጦቢያ ምድር
ምንም ቢለወጥ ቢቀየር፣በደሉ መልኩን አይቀይር::
         ~***•°•***•°•***•°•***~
ለተዝረከረከና ለተጨማለቀው
አልቦ ከንቱ የጦብያ  ሕይወት
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ጥር ፳፯/፳፻፲፪ ዓ.ም
February 06/2020
ሐሙስ)06:25(ፊትበር
©ያመጌዕ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop