የአንድ የአሜሪካ ዶላር የባንኮች መሸጫ ዋጋም ከ110 ብር ወደ 115 ብር ጨምሯል – ዋዜማ

ለቸኮለ! ዓርብ የካቲት 24/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች
1፤ የግል ባንኮች በአሁኑ ወቅት ለአንድ ዶላር የሚያስከፍሉት ኮሚሽን ወደ 65 ብር ማደጉን ዋዜማ ተረድታለች። የአንድ የአሜሪካ ዶላር የባንኮች መሸጫ ዋጋም ከ110 ብር ወደ 115 ብር ጨምሯል። የውጭ ምንዛሬ ግብይቱ የሚፈጸመው፣ በባንክ የውጭ ምንዛሬ ባስቀመጡ ግለሰቦችና በውጭ ምንዛሬ ፈላጊዎች መካከል በደላሎች አገናኝነት ነው። አስመጪዎች አገር ውስጥ በብር ክፍያ ፈጽመው ውጭ አገር ባሉ ሰዎች ለሚፈልጉት ዕቃ በውጭ ምንዛሬ ክፍያ ተፈጽሞላቸው ዕቃ ለማስገባትም፣ ለአንድ ዶላር በተመሳሳይ 105 ብር ይከፍላሉ። ባንኮች የሚሸጡት የውጭ ምንዛሬም ከጥቁር ገበያው ጋር ተመሳሳይ እየሆነ መምጣቱን ዋዜማ ታዝባለች። ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ለአንድ ዶላር መሸጫ ያወጣው ዋጋ ግን፣ 54 ብር ከ83 ሳንቲም ነው። ዝርዝሩ- https://bit.ly/3kATBPn

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share