April 10, 2013
6 mins read

(Updated) በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት በቬጋስ ለተቃውሞ ከወጡ ከሺህ በላይ የታክሲ አሽከርካሪዎች 14ቱ ታስረው ተፈቱ

በቬጋስ የሚያደርጉት የመብት ትግል እንዲሳካ በዓለም ዙሪያ ላሉ ወገኖቻቸው የድጋፍ ጥሪ አቅርበዋል

በቬጋስ በሁለቱ ታላላቅ የታክሲ ኩባንያዎች ፍሪያስና የሎ ቼከር ስታር ታክሲ የሚያሽከረክሩ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ከሺህ በላይ የስራ ማቆም አድማ ላይ ሲሆኑ ሰኞ የጀመሩትን ከ96ሺህ በላይ ተሳታፊ ከሚገኝበት የናሽናል ብሮድካስቲንግ ማህበር ኮንቬንሽን በስራ ላይ ያሉ እንዳይጭኑና በስፍራው በመገኘት በከተማው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ በማሳረፍ ጥያቄያቸው ትኩረት እንዲያገኝ ትላንት ለሁለተኛ ቀን ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት የእግረኛ ማቋረጫ መብራት ሳይበራ ተሻግራችሁዋል በሚል ከመሀከላቸው 15ቱ በከተማው ፖሊስ የታሰሩ ሲሆን ድርጊቱ ሆን ብሎ ፍርሃት ለመፍጠር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል።ከታሰሩት 14ቱ ዛሬ ማለዳ 2 ኤ.ኤም ላይ ከሰዓታት እስር በሁዋላ ሲፈቱ አንዱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛል።

የየሎ ቼከር ስታር አሽከርካሪዎች ከማርች 3 ጀምሮ እንዲሁም በፍሪያስ ኩባንያ ያሉ አሽከርካሪዎች ማርች 29 ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ላይ ሲሆኑ በከተማው አስተዳደር፣በኔቫዳ ግዛት ገዢ ብራያን ሳንዶቫል እንዲሁም ከኔቫዳ ለተወከሉት የዲሞክራት የሴኔት መሪ ሴናተር ሔሪ ሪድ በተለያዩ ጊዜያት ጥአቄያቸውን ቢያቀርቡም ከብዙዎቹ ምላሽ ያላገኙ ሲኦን ሴናተር ሔሪ ሪድ ተወካያቸውን ልከው ኸየሎ ቼከር ኩባንያ ጋር ውይይት እንዲጀመር ጥረት ቢያደርጉም ውጤት አልተገኘም።

አሽከርካሪዎቹ ከየኩባንያቸው የቀረበላቸው ኮንትራት ጥቅማቸውን የማያስከብር በመሆኑ እንደማይቀበሉት ደጋግመው የገለጹ ሲሆን በተለይ የየሎ ቼከር ስታር አሽከርካሪዎች ከ95 በመቶ በላይ በድምጽ ኮንትራቱን ጥለው የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ በዩኒየኑ ፈቃድ ያገኙ ሲሆን የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ሲደራደሩበት የነበሩበት ኮንትራት ላይ እነሱ ሳያውቁና ድምጽ ሳይሰጡ ዩኒየኑና ኩባንያው ተፈራርመው ተቀበሉ መባላቸውን በመቃወም ዩኒየኑ ሸጦናል በሚል የወጡት የስራ ማቆም አድማ ነው።

ከላስ ቬጋስ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የታክስ አሽከርካሪዎች ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ከሁለቱ ኩባንያዎች ከሺህ በላይ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ላይ ይገኛሉ።

<<በኔቫዳ ህግ ለሀብታም ነው የሚከበረው !?>> ሲሉ በምሬት የሚጠይቁት ኢትዮጵያውያኑ የከተማው አስተዳደርና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ለጥያቄያቸው ምላሽ አለመስጠታቸው ሰፊ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል።

ከ96 ሺህ ሰው በላይ የሚገኝበትና ከተለያዩ የዓለም ክፍል የመጡ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሚሳተፉበት የሰሞኑ የቬጋስ ኮንቬንሽን ኢትዮጵያውያን የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች አስቀድመው በስራ ላይ ላሉ የታክሲ አሽከርካሪዎች ለሶስት ቀን ከስፍራው ባለመጫን ተጽዕኖ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ነው።

አቶ ሽመልስ ደረሰ ለዚህ ዜና አጠናቃሪ አስቀድመው እንደገለጹት የተጀመረው የመብት ትግል ውጤታማ እንዲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዕውቀት ያለው በዕውቀቱ በተለይ የሕግ ባለሙያዎችን ጨምሮ የቀረውም ወገናቸው የሙያና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የተጀመረውን የስራ ማቆም አድማ ሳይቀላቀሉ በተለይ በሁለቱ ኩባንያ ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚቀርብላቸውን ጥሪ ችላ ብለው እየሰሩ የሚገኙትን በርካቶችን <<ባንዳ ባንዳ !>> ሲሉ በአድማው ላይ ያሉ ሲቃወሟቸው አስተውለናል።ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶች የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ ይገባል እያሉ በአደባባይ ሲናገሩ የነበሩ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

ዛሬም በተመሳሳይ በከተማዋ ላስ ቬጋስ ኮንቬንሽን ሴንተር በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ እና ቤተሰባቸው ወጥተው ተቃውሟቸውን ለማሰማት ወስነዋል።

የከተማው ዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን ጣቢያዎች የተቃውሞ ሰልፉ ከሚደረግበት ቦታዎች ባለመገኘት ተገቢውን ሽፋን ባለመስጠታቸው ተወቅሰዋል።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop