የአዲስ አበባ መስተዳድር የአውቶቡስ ግዢ በገለልተኛ ኦዲተር ይጣራ። ገለልተኛ አጣሪ ኦዲተር ይቋቋም !!!! (ሙሼ ሰሙ)

February 22, 2023
5 mins read
331296467 669267948335553 3821475095841743190 n 2
ሙሼ ሰሙ
ሙሼ ሰሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዢ የፈጸመባቸው አውቶብሶች ዋጋ እጅግ አወዛጋቢ ከመሆኑ የተነሳ አስተያየት ለመስጠት እንኳን የተጸየፍኩት አጀንዳ ነበር። የአውቶብሶቹ ዋጋ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የከተማዋን ነዋሪ ያስደነገጠ፣ ግራ ያጋባና ዘረፋ ለይቶለት ነፍስ ዘርቶና ስጋ ነስቶ በቅ ብሏል ያሰኘ አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ መሰንበቱ ሳያንስ ጥያቄው ተገቢውን መልስ መነፈጉ አሳፋሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የአውቶቡሰሰ ግዢውን በሚመለከት ከተለያየ ገለልተኛ አካላት በሚቀርብላቸው መረጃ መሰረት የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የመዘረፍና የመነጠቅ ስሜት አድሮባቸዋል። ተመዝብሯል የሚባለው የአውቶብሱ ግዢ የተፈጸመው ላባቸውን አንጠፍጥፈውና ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለጋራ ልማት ከሚገብሩት ግብር ላይ ተዘግኖ ስለሆነ ቁጭታቸው ፍትሐዊና ጥያቂያቸውም መልስ ከገለልተኛ አካል የሚሻ ጉዳይ ነው ።

የከተማዋ አስተዳደርም መረጠኝ ለሚለው ነዋሪ ታማኝነቱ የሚረጋገጠው ከቀረበለት ጥያቄ እራሱን ከመጋረጃ በስተጀርባ ደበቆ ወፈ ሰማይ ካድሬ በማሰማራት ሀቁን በርብርብ በማድበስበስና ሕዝብን ለማሸማቀቅ በመሞከር ሊሆን አይገባም።

ጥያቄው ከሕዝብ የመነጨ የሕዝብ ጥያቄ ነው። ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ የጨረታ ሂደቱ፣ አሸናፊው የተመረጠበት መስፈርት፣ ተገኘ የተባለው የውጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ የአውቶብሶቹ ዋጋና የጨረታ ኮሚቴው ገለልተኝነት ወዘተ ኦዲት ሊደረግ ይገባል። ሂደቱ ኦዲት ተደርጎና ሀቁ ተጣርቶ ውጤቱ በግልጽ ለሕዝብ መቅረብ አለበት።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ መርጦናል የምትሉት ሕዝብ ላቀረበው ፍትሐዊ ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለትና በካድሬ ትርክት ጥያቄውን ለማድበስበስ መሞከር ጥርጣሬውን በሐቅ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ከማረጋገጥና ብሶትና ጥላቻውን ከማባባስ ውጭ ፋይዳ ቢስ ጥረት ነው።

ይህ ደግሞ ለዘመናት የለመድነው “የምን ታመጣላችሁ” ማን አለብኝነት ስለሆነ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ትናንት በሌላው ላይ የጠቆመ ጣታችሁ ተራውን በራሳችሁ ላይ ጠቁሞ በሙስና እንደሚፋረዳችሁና ታሪክ እራሱን እንደሚደግም ጥርጥር የለኝም ?!

adanech Leba thief 2በመሰረታዊነት የሚነሱና ሕዝብን ለበቂና አስተማማኝ ጥርጣሬ ከሚዳርጉ መነሻዎች በጥቂቱ

-ቻይና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባላት ኢኮኖሚያው ትብብርና (Bilateral ) የሁለትዬሽ የንግድ ግንኙነት መሰረት ቀጥታ ከአምራቹ ጋር ተደራድሮ አውቶብሶቹን መግዛት እየተቻለ ከሁለተኛ አቅራቢ መገዛቱ ?

– መንግስት ማቅረብ ያልቻለውን ከ70 ሚሊየን በላይ( በብሔራዊ የምንዛሪ ተመን መሰረት) የሆነ ዶላር የጨረታ አሸናፊው ማቅረባቸው፣ እንደ ብቸኛ አቅራቢ መወሰዳቸውና የዶላሩ ምንጪ አለመጠቀሱ ?

– ከ3.8 ቢሊየን ብር ወይም ከ70 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ የ200 አውቶቡስ ግዥ ዓለም ዓቀፍ ጨረታ አለመውጣቱ፣ ወጥቶም ከሆነ ውጤቱ አለመገለጹ ?

– የተጠቀሱት ዓይነት የከተማ አውቶብሶች አንድ አውቶብስ ብቻ ለመግዛት ለሁለት የቻይና አምራች( Higer, dongfeng,) ላቀረብኩላቸው ጥያቄ የተሰጠኝ ዋጋ ከ 80 ሺህ እስከ 130,000 (ልዩነቱ በሚገጠምላቸው አክሰሰሪና አውቶማቲክና ማንዋል ይመሰረታል) ዶላር የሚደርስ ሲሆን መስተዳድሩ ግን የአውቶብሶቹ ብዛት 200 ስለሆነ የመደራደርና ዋጋ የማስቀነስ አቅም እያለው ገዛኋቸው የሚለው ከ350,000 ዶላር በላይ ወይም ከ3 እጥፍ በላይ መሆኑ ? ወዘተ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

2 Comments

  1. ኮራፕሽን፤ግድያ፤ዝርፊያ ወንጀል አይደለም ወንጀል የሆነው አማራ መሆን ነው፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህ ህዝብ ከሚባላ አንድ አምስት የ DNA ማሽን ተገዝቶ ቢመረመር ከዚህ ጎሳ ነኝ ብሎ ችግርን መጥመቅ እንጀራው ያደረግ ጨካኝ አረመኔ ትክክለኛ ማንነቱ ታውቆ አርፎ ይቀመጥ ነበር፡፡ ይህ ከተደረገ እነ ዲማ ነገዎ፤ብርሃኑ ጁላ፤ በያን ሱጳ የመሳሰሉት ከምባታና ሃዲያ ሲሆኑ እነ በቀለ ገርባ፤ጁዋር መሃመድን የመሳሰሉት ለአረብ የሚቀርብ ቦታ ተፈልጎ ከዚሃ ሲሆኑ ተረቱ ሁሉ ቀርቶ ህዝብን አንድ የሚያደርግ ኢትዮጵያዊነት ያብብ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ የዚህ ጎሳ ተወካይ ነኝ ብለው መተዳደሪያቸውን ያደረጉ ወንጀለኞች ግን ይህ ሃሳብ ስለማይስማማቸው ሳያንገራግሩ የሚቀበሉት አይመስሉም፡፡ እንደ ተባለው ከ10% ኦሮም 200፣000 ኦሮሞ መገኘቱ ስለሚያጠራጥር ኢትዮጵያዊነት ዳግም ያብባል መፍትሄውም ይህ ብቻ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Neamin zeleke 2
Previous Story

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የካቲት 13/ 2015 ያወጣው መግለጫ አሁናዊ የኢትዮጵያን ሁኔታ በትክክል  የዳሰሰ እና ትክክለኛ የትግል አቅጣጫዎችን ያመላከተ ነዉ

arada 1
Next Story

ወይ አዲስአበባ ወይ አራዳ ሆይ !!!- ምህረት ከበደ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop