February 21, 2023
4 mins read

አባቶች ተክደዋል፣ ሎጆቻቸውን አብይ እያሰረ፣ ከስራ እያባረረ ነው – ግርማ ካሳ

43445555t 1በቤተ ክርስቲያን ላይ፣ በኦህዴድ/ኦነጎች የተከፈተውን ጥርነት ተክትሎ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ ህዝበ ክርስቲያኑ እንዲሁም የኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ በነነዌ ጾም ወቅት ጥቁር በመልበስና ቤተ ክርስቲያናትን በመጠበቅ፡፡ በርካታ የሜዲያ ሰዎችን ፣ የሶሻል ሜኢድያ አክቲቪስቶች ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጎን ቆመዋል፡፡ እውነትን በማቅረብና በመዘገብ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከአብይ አህመድ ጋር ተቀምጠው፣ ስምምነት እንደተደረገና፣ ሌላ ሲኖዶስ ለመፍጠር የተነሱ ከድርጊቶቻቸው እንደተቆጠሩቡ፣ እንደተመለሱ አሳውቀውናል፡፡ ከአብይ አህመድ ጋር የተረደረገውን 10 ነጥብ ያለበት ስምምነት አንሰብበዉናል፡፡

ከዚያ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ አገር ሰላም ብሎ የተቀመጠ ይመስላል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ወገኖች ታስረው፣ አሁንም እየታሰሩ ባለበት፣ ብዙዎች ጥቁር ለበሳችሁ ተብለው ከስራ የተባረሩና እየተባረሩ ያሉ ባለበት፡፡

አባቶች የሚያደርጉት የሚያወቁ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ እስካእአሁን ለነበራቸው ላሳዩት አስደማሚ አምራር፣ ብልህነትቸው፣ አስተዋይነታቸው የሚደነቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የነርሱ ዝምታ ምችት አልሰጠኝም፡፡

አብይ አህመድ፣ በዚህ ስምምነት አድርገባል እያለና አባቱንች በተራቃላት እየሸረደደ፣ በጀርባ ግን ሰይጣናዊ ተግባራቶችን ከአዳነች አበቤና ሺመለስ አብዲሳ ጋር ሆኖ እየሰራ ነው፡፡ ስምምነት ተደረገ ከተባለ በኋላ ብዙዎች እየታሰሩ ነው፡፡ ብዙዎች ከስራቸው እየተባረሩ ነው፡፡ የበቀል እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡ ታዲያ አባቶች ለዚህ ምንድን ነርው ምላሻቸው ? “ክብሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ” ያሉት በዚህ ልክ ክህደት ሲፈጽምባቸው ?

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከአብይ ጋር የተስማሙበት አስር ነጥብ ላይ፣ አብይ አህመድ የታሰሩትን እንደሚፈታ፣ ከሞቱት ካሳ እንደሚከፍል መቀመጥ ነበረበት፡፡ ግን ባይቀመጥም፣ ቢያንስ በቃል ተስፋ እንደገባላቸው መፈጸም ነበረበት፡፡ ያ አልሆነም፡፡ እነርሱም ለዚያ ተጠያቂ አላደረጉትም፡፡ ይሄ ትልቅ ስህተት ነው፡፡

ነገ ቅዱስ ሲኖዶሱ ላያ ሌላ አደጋ ሲፈጸም፣ እነ አብይ እስካሉ ድረስ መፈጸሙ አይቀርማን፣ ሌላ ጥሪ ቢያቀርቡ፣ “ትንሽ ቆይተው ደግሞ ይስማሙና ለኛ ግድ አይሰጣቸውም” የሚል አመለካከት ሊኖር ስለሚችል ፣ ብዙ ድጋፍ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ የነ አብይ አህመድም አላማ ይሄው ነው፡፡ ህዝቡ እንደዚያ እንዲያስብ፣ በህዝቡና በሲኖዶሱ መካከል ክፍተት እንዲኖር ያደርጉና፣ ሲኖዶሱን ከህዝብ ነጥሎ፣ ለብቻቸው ሲያገኛቸው አሁን ያልተሳካላቸውን ያኔ በቀላሉ ያሳካሉ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

4
Previous Story

የከሸፈው የጠቅላዩ ሚስጥራዊ ግድያ   ከ4ኪሎ ተቀምሮ የሾለከው አስደንጋጭ ዕቅድ ! አቢይ እራሱ ያደራጃቸው ሃይማኖታዊ ቡድኖች መልሰው ካዱት ! !

FbaddudXwAEqUNX 3
Next Story

ግርማ የጅብጥላ፤ ስምን ከሲመት መለየት የማይችል ብአዴናዊ እንኩቶ  

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop