February 15, 2023
6 mins read

“የካሊፎርኒያ ኆኅተ ሰማይ አርሴማ አንድነት ገዳም ቁልፍ እና አስፈላጊ የሆኑ የግዢ ሰነዶችን ተረክበናል፡፡” ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር)

4544 1

4544 1

ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይህንን የገለጹት በኢ/ኦ/ተ/ቤ በካሊፎርኒያ ሊገዛ የታሰበውን የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም አሁናዊ ሁኔታ በተለጹበት ወቅት ነው፡፡

ብፁዕነታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሁን በዓለንበት ዘመን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ላሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ለሆኑ በእኩልነት የምትሰጠው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ዘመን ተሻጋሪ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ከሐዋርያት የተረከበችውን እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት በመጠበቅና በማስጠበቅ ሁሉንም በእኩልነት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በሰላም በመያዝ ለሀገራችን ኢትዮፕያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነት፣ ህልውናና ክብር እንዲሁም ስልጣኔ ዋና መሠረት እንደሆነች በታሪክ የተጻፈ ከመሆኑም በላይ ዓለም የሚያውቀውና የሚመሰክረው እውነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሆኖም ግን የ2015 ዓ.ም የጾመ ነነዌ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን በውስጥ ጠላቶች የተፈተነችበት ወቅት በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች የደረሰውና እየደረሰ ያለው ፈተና ከባድ ቢሆንም ልጆቿ በእምነት ጸንተው፣ በያሉበት ጥቁር ልብስ በመልበስ፣ በእንባ እና በጸሎት ከኃያሉ ከእግዚአብሔር ፊት የቆሙበት ወቅት መሆኑን ታሪክና ትውልድ የማይረሳው ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ልብ በሚሰብር ፈተና ተስፋ ሳንቆርጥ በእምነት በሚደረግ ጸሎት የበለጠ በእግዚአብሔር ፊት እንድንቆም እንድንበረታ ያስተምረናልና ልንበረታ ይገባናል ብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ አክለው በመካከለኛው ካሊፎርኒያ በተተኪ ትውልድ ላይ ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ እቅዶችን በማዘጋጀት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰሜን አሜሪካ ለትውልድ የሚተላለፍ ርስትና ቅርስ እንዲኖራት ለማድረግ በኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ስም ታሪካዊ፣ ታላቅና ሰፊ ቦታ ለመግዛት እንደታሰበና በግዢ ስምምነት ውስጥ እንደነበረ ከ3 ወራት በፊት ገንዘብ በማሰባሰብ እርዳታ መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም የገዳሙ ግዢ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ቁልፉን እና አስፈላጊ የሆኑ የግዢ ሰነዶችን መረከብ መቻላቸውን በታላቅ ደስታ ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ግዢውን ለመፈጸም 3.5 ሚሊየን ዶራል ከግል ድርጅቶች በወለድ እንዲሁም ከግለሰቦች ያለወለድ 1.9 ሚሊየን ያለወለድ በመበደር የተፈጸመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ስለገዳሙ በተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች በተደረገው ጥሪ መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በገንዘብ፣ በጸሎት፣ በእውቀት፣ በሙያና ውድ ጊዜያችሁን በመስጠት ላደረጋችሁት እርዳታ በእግዚአብሔር ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው አክለው በዚህ ታላቅ የገዳም ቦታ ላይ የተሟላ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጠት እንዲቻልና በጥናት የተዘጋጁ እቅዶችን በአጫር ጊዜ ማሟላት እንድንችል የሁላችሁም አስተዋፆ አስፈላጊ በመሆኑ በጸሎት፣ በእውቀት፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ አስፈላጊውን እርዳታ በማድረግ እንድትተባበሩን ሲሉ መንፈሳዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም ይህንን ታሪካዊ ገዳም ለማስመረቅና ለማስጎብኘት ይቻል ዘንድ ሚያዚያ 14 ቀን 2015 ዓ.ም /April 22, 2023 G.C/ የቅዳሴ ቤቱ የምርቃት መርሐ ግብር እንዲከናወን መወሰኑን በመግለጽ በዓለም ዙሪያ የሚትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በበዓሉ ላይ በመገኘት ከቅዱሳን በረከት እንዲሳተፉና ገዳሙን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መጨረሻም አሁን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከገጠማት ችግር አንፃር ስለገዳሙ ሰፊ ገለጻ ማድረግ አግባብ ባለመሆኑ ወደፊት የግዢ አፈጻጸሙን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ እንደሚሰጡ ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን!

የዩቲዩብ ቻናልን ላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ 2
Previous Story

ዝክረ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ – ቀሲስ አስተርአ

331518137 3672090016351491 3181282135744743509 n 1
Next Story

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በውይይት ተፈታ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop