February 9, 2023
8 mins read

የጥላቻ ፖለቲካን የፈለፈለው የብሔር አስተሳሰብ ሃይማኖት ውስጥም ገብቶ ሌላ ትርምስ ሲፈጥር ዝም ሊባል አይገባም!

ezema 1 2

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር በአንክሮ እየተከታተለው ይገኛል፡፡ ጅማሬው ካሳደረበት ብርቱ ስጋት አንጻር ፓርቲያችን ታህሳስ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ለማስገንዘብ እንደሞከረው የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች መፈታት ያለባቸው በተቋሙ ህግና አሠራር መሠረት ሲሆን ይህን ውስጣዊ አሠራር አልፈው ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች የሚኖሩም ከሆነ ያለምንም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት በሕጋዊ መንገድ ብቻ ውሳኔ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ የመንግሥት ድርሻ መሆን የሚገባው በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 11 ድንጋጌ መሠረት ፍጹም ገለልተኛነቱን በሚያረጋግጥ መልኩ በእኩልነት መርኅ ላይ ቆሞ ህግና ሥርዓትን ማስከብር ሲገባው በገሃድ ያሳየው ወገንተኝነት በእጅጉ አሳዝኖናል፤ ለተፈጠሩ ቀውሶችም ተጠያቂነት እንዳለበት ማስገንዘብ እንወዳለን።

በተቋሙ የተፈጠረውን ውስጣዊ ችግር ተከትሎ የመንግስት ኃላፊዎች ያደረጓቸው ንግግሮች ሁኔታውን ለተወሳሰበ ችግር ዳርገውታል። ከመንግስት ሃላፊዎች አባባሽ ንግግሮች ባሻገር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የጸጥታ ኃይሉ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በተግባር ካሳዩት ወገንተኝነት እና አድሎ በከፋ መልኩ ባልታጠቁ እና ፈጽሞ የጸጥታ ስጋት ባልሆኑ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው የንጹሐን ዜጎች ሕይወት እንዲቀጠፍ እና አካል እንዲጎድል ምክንያት ሆኗል፡፡

በክልሉ በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የንጹሐን ዜጎችን ሞት፣ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና መፈናቀሎችን ተቆጣጥሮ ሰላምና ደኅንነትን ማስከበር ያልቻለው የክልሉ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ እንደሀገር ያለንበትን ችግር ውስብስብ እያደረገው ይገኛል፡፡ የፌደራል መንግሥቱም ቢሆን ይህን ዐይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት በገሀድ እያየ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዋነኛው ተጠያቂ ያደርገዋል፡፡

በሌላ በኩል የእምነቱ ተከታዮች የሃይማኖት ተቋማቸውን ትዕዛዝ በማክበር ጥቁር በመልበሳቸው ምክንያት በየመንገዱ እና በቤተ እምነታቸው ቅጥር ግቢ መደብደብ፣ ማዋከብ፣ ማሠር እና ማስፈራራት ደርሶባቸዋል፤ በተለይ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ በሚገኙ መንግስታዊ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት ጭምር ተመሳሳይ በደል ሲደርስባቸው ተመልክተናል፡፡

ይኽ የዜጎችን ነፃነት መጋፋት ስለኾነ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። በኦሮሚያ ክልል የእምነቱ ተከታዮች ላይ እና የሃይማኖት አባቶች ላይ የሚደረጉ ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎች አሁንም እየቀጠሉ በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል። ኢዜማ አሁንም የሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ መንግሥት እጁን መክተቱ መዘዙ ከፍተኛ መሆኑን ደጋግሞ ማስገንዘብ ይፈልጋል፡፡

ድርጅታችን ኢዜማም ጉዳዩን በከፍተኛ ትኩረት እና በጥንቃቄ እየተከታተለ መሆኑን እያሳወቀ ለዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ የዳረገን ብሔር ተኮር ፓለቲካ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን አንዘነጋውም፤ የጥላቻ ፖለቲካን የፈለፈለው የብሔር አስተሳሰብ ሃይማኖት ውስጥም ገብቶ ሌላ ትርምስ ሲፈጥር ዝም ሊባል አይገባም እንላለን!

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያሉ ጽንፈኛ የብሔር ኃይሎች ህዝባችን ተረጋግቶ ለችግሮቹ በሰከነ መንገድ መፍትሔ እንዳያበጅለት ባገኙት የልዩነት ቀዳዳ ሁሉ የሚያደርጉትን ግፊት በቅጡ ማስተዋል እንደሚኖርብን ለማሳሰብ አንወዳለን፡፡

ኢዜማ እንደ አንድ ፖለቲካ ተቋም ችግሮቹ ተወሳስበው ወደ አላስፈላጊ መንገድ እንዳይሄዱና ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳያስከፍለን ብሎም እንደሀገር ወደማንወጣው የማያባራ ውጥንቅጥ ውስጥ እንዳያስገባን እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ፓርቲ የምንችለውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማንል ለማሳወቅ እንወዳለን፡

ይህን መግለጫ ባወጣንበት ዛሬ እንኳን በወሊሶ መስመር በወለቴ፣ አለምገና እና ሰበታ ቀውሱ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡

አሁንም በድጋሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረው ችግር በቤተክርስቲያኗ ቀኖና ከዚያም ካለፈ በሕግና በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ እያሳሰብን፤ በአሁኑ ወቅት ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተገንዝቦ ኃላፊነቱ ህግን አክብሮ ማስከበር መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

የካቲት 2/2015 ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

Go toTop