የታከለ አስደንጋጭ ዝርፊያ ሲጋለጥ! – እናኑ ጥላሁን

February 1, 2023

takeleለማመን_የሚከብድ ለምስኪን ኢትዮጵያዊ የማይገባ ኔክስት ሌቭል ዘረፋ የሰማሁት ከኤርሚያስ አመልጋ ቀጥሎ በታኬ እኮ ነው እህእ የመጀመሪያ ታኬ እንደመጣ ያደረገው የሼኩን መሬት መቀማት ነው። 11 መሬቶች ወደ መሬት ባንክ አስመለስኩ ብሎ ጀግና ጀግና ሲጫወት ሰዉም የአብይ ፍቅር ትኩስ የነበረበት ስለነበር አብሮ ተንጫጫ (የዚ ውጤት በኋላ እመለሳለሁ) ሁለተኛው ዙር ቅርጠፋ የተማሪዎች ምገባ ና ዩኒፎርም ተባለ። በዚህም ለአራት ድርጅቶች ዩኒፎርም አድቫንስ ሲከፈል አንዱ ድርጅት አድቫንሱን 75 ሚል ሙሉ በሙሉ ተከፋፍለው እጄ ላይ የቀረው 16 ሚል ነውና መስሪያ ስለሌለኝ ዩኒፎርሙን ማስረከብ አልችልም የምታስገድዱኝ ከሆነ የወሰዳችሁበትን አወጣለሁ ብሎ ሽምግልና ተልኮ እንደነበር ስንቶቻችሁ ታስታውሳላችሁ

ወዲያው የኮተቤ መንገድን መጨረስ ተብሎ የኮተቤ መንገድ ፀሀይ ከጠለቀበት ተክለብርሀን ላይ ተወስዶ ለድሪባ ደፈርሻ (ግማሹን ጀምሮ ስለነበር ያለጨረታ) ጀባ ቢባልም በአገር ልጅነት ተቀባበለ ግን እንዳሰበው ብሩ አልሆነምከዛ የሀገር ቤት ኮንትራክተር በዶላር ለአሁኑ የአሜሪካ ጉዞ እንደማያዋጣ የገባው ታኬ የመስቀል አደባባይን ፕሮጀክት ለቻይኖቹ በ2.5 ቢል እና የቄራን መንገድ በኪሜ 400 ሚል ለ4 ኪሜ 1.6 ቢል ያለጨረታ ከፍሎ አስጀመረ (በኢትዮ ታሪክ ውዱ መንገድ የቦሌ መንገድ ሲሆን እሱም በኪሜ 60 ሚል ነበር የወጣበት) ይህም ከጫማና ከቺክ ያልዘለለ ብር መልሶ ወደ አንደኛው ደንበኛው ወደ ሚድሮክ ፊቱን መልሶ መሬቶቹን በድርድር ግማሹን በአብነት ግማሹን በሚድሮክ ስም በአብዛኛው እንዲመለስ ሆነ። (የአሁኑ የሼኩና የአብነት ክስ ወሎ ሰፈር ጋር ያለውን ማየት ነው) ይህ በዶላር ጉቦ መቀበል ያስጀመረው የመጀመሪያው የመሬት ኬዝ ሙሉ በታኬ ጊዜ የተሰጡ ትልልቅ ካሬዎች ኒዮርክ ብር የገባባቸው ናቸው። (የሸገር ታይምስን ዶክመንተሪ እዩአቸው)

በዚህ የጀመረው የታኬና የአብነት እከክልኝ የወርቁን መሬት እኮ ማስመለስ እችላለሁ በሚል ሚድሮክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ሹም ሽር አስነስቶ አረጋን ወደ ዩኒቲ ታከለን ወደ ማእድን አብነትን ወደ ሸራተን የወሰደ ጉዞ ነበር። (ስለ ሚድሮል ካቢኔ ሹም ሽር የአብነት በሼኩ ንብረቶች ላይ ጠቅላይ መሄድና የጀማል ተሽሎክልኮ አለቃውን ማስወጋት ልብወለድ መፅሀፍ የሚወጣው ከአገር መፈንቅለ መንግስት የማያንስ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ይቀመጥልን)

ከዛማ በአመት 600 ሚል ዶላር የሚልከውን የሚድሮክ ጎልድ ንብረት ከጃዋርና ከድንቁ (የጃዌ ባንክ ሮለር በገንዘቡ ጃዌ በአክቲቪስትነቱ ያንን ማእድን ማዘጋቱ ይታወሳል) አፍ ላይ ታኬ ወደ ሼኩ፣ ሼኩም በዱባይ ወደ ታኬ የመጀመሪያው ትራንሳክሽን ተጀመረ። እንደው ሰው ከከንቲባነት ወደ ማእድን ሲመደብ እንዴት እንዳንል (በሲቪል ተመርቆ የመጀመሪያ ስራ ያገኘ የሚል ሚም አስታውሳለሁ) ያኔ በጊዜው አበቤ ከንቲባ ካልሆንኩ ብላ አብይን አስቸገረች ተብሎ አይኑ ከታኬ ላይ ተነሳለት።

ይህን የለመደው ታኬም ከዚ በኋላ 38 የማእድን ፈቃዶችን ልክ እንደ መሬቱ በመሰረዝ መልሶ መውሰድ የፈለገ ደጅ እንዲጠና በማረግ ያቺኑ ስልቱን ተጠቅሞ ስራውን ጀመረ። አሁን በቅርብ እንኳን የእንግሊዙን ከፊ ሚኒራል ጨምሮ 55 ፍቃዶችን ሰርዞ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ድራማ ሲሰራ ነበር። በወሩ የተመለሰላቸው አየን እንጂ ከዛማ ታኬ ደስ ሲለው ቢሮዬ እየታደሰ ነው በሚል ቢሮውን ሸራተን፣ ደስ ሲለው መንግስት ቢሮ ውስጥ ማማስ ኪችንን በማስገባት የጀመረው ላግዠሪ ታኬ የአራዳ ልጅ የሚል ማእረግ አሰጥቶታል(በ30 ብር ሰብሲዳይዝድ ምግብ የሚበላ የማእድን ሚኒስቴር ሰራተኛን እና ኮንዶ የወሰደ የእግር ኳስ ደጋፊ አባቴ ቢለው አይደንቅም)። በመጨረሻም ሚሊኒየም አዘጋጅቶ የነበረው የማእድን ኤግዚቢሽን ላይ ለሱና ለጓደኞቹ ፋሽን ሾ በፖዲየሙ ላይ በቫዮሊን ታጅበው እያዩ ውጪ 15 ኩንታል ሲሚንቶ በቸርነቱ እያደለ ነጫጮቹ ድንኳኖች ለሊት በተሰለፉ ሰዎች ሞልቶ ያየሁ ግዜ ግን ለመጀመሪያ በባለስልጣን ያዘንኩበት አጋጣሚ ነበር።
_
አፍሪካ ኢዝ ኤ ዱምድ ኮንቲኔንት። የተለየ የሚያረግ የሚሆን የለም። ታኬም አጦዘው እንጂ ከሽመልስ ወይም ከራሱ ከአብይ የተለየ አስተሳሰብ የለውም። አልፈርድበትም ግን በሌብነቱ እኮንነዋለሁ። ደሞም ለዚ ህዝብ ይገባዋል። ብርሀኑ ለምን ተማሪ ጣለ ብሎ የሚኮንን፣ የሚሰራለት እና የሚሰራበት ያልገባው ህዝብ እንደ ታኬ አይነት አክተር ባለስልጣን በጣም ዲዘርቭ ያደርጋል።

2 Comments

  1. “ብርሀኑ ለምን ተማሪ ጣለ ብሎ የሚኮንን፣ የሚሰራለት እና የሚሰራበት ያልገባው ህዝብ እንደ ታኬ አይነት አክተር ባለስልጣን በጣም ዲዘርቭ ያደርጋል” ነው ያልከን? አንተስ ከታከለ በምን ተሻልክ? ወረኛ ነገር ነህ 97% የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ተስፋ ያመከነ ጡረተኛ ላንተ ጀግና ነው ማለት ነው? ብቃቱ ከሌለህ ወደዚህ አትምጣ አምዱ እነ አቻምየለህ ታምሩ፤ዶ/ር ፍቃዱ በቀለ፤ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦን አይነት ምሁራንና የሃገር ፍቅር ያላቸው የኢትዮጵያ ወዳጆች ሃሳብ የሚገልጹበት ነው፡፡ በሃሳብ የተጎዳህ እና ለመገምገም አቅም ያነሰህ ሰው ትመስላለህ ታከለ ሌባ ነው በአንድም ሆነ በሌላ ብርሃኑ ከታከለ የተሻለብት ሁኔታ አይኖርም፡፡ ብልጽግና ሌብነትን ወንጀል አያደርግም ሌሎችንም ጨምራቸው፡፡

  2. ታኬ ወጥተህ ሳታላቅ ዶሲህን ዘረገፉት? በእርግጠኝነት የብልጽግና ሰው መሆን አለበት ሁድ የሚሸፍንህ አይመስለኝም መግቢያም አይኖርህም ክስ እመሰርታለሁ ብለህ እራስህ ላይ ጣጣ ታመጣለህ፡፡ የኢትዮጵያ አናብስት እረፍት የሚሰጡህ አልመሰለኝም ብትችል ፌስ ማስክ አይለይህ አሜሪካ ሁሉም ነገር ሊኖር ስለሚቻል ፍትህንም ማስቀየር አንዱ አማራጭ ነው ያም ካልሆነ ነብስህ ከተጨነቀች እረፍትን ካጣህ እንቅልፍም እምቢ ካለህ ሌላውን አማራጭ ሞክረው፡፡ ፋይልህ ወጥቶ አሜሪካ ክስ ከተከፈተብህ መአዛ አሸናፊ አታወጣህም የእሷንም የሚቆፍሩ አናብስት አይጠፉም፡፡ እንግዲህ ያች ቀን መጣች ቻለው፡፡ ያ ያሳረደክው የተሳለቅህበት ህዝብ ደም መጮህ ጀምሯል ባንተ ብቻ አያበቃም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Dr. Fekadu Bekele
Previous Story

አሁንሞ የሐገርን ኢኮኖሚ እየገደለ ያለው አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ነው

331731119 906223560502555 6913377031752548068 n 1
Next Story

ከታሪክ ማህደር: ሦስተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ – አቡነ ተክለሃይማኖት

Go toTop