November 3, 2022
9 mins read

ማይክ  እና  ሐመር – ሲና ዘ ሙሴ

ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም  የፈሰሰው የኢትዮጵያ ጀግና ልጆች ደም የፍትህ ያለ ይላል ። እናም ፡- የማይክን ኃያል ድምፅ ፤

ሐመርን ኃያልነት … ብናውቅም ፤

እጃችን የእሳት ሰደድ ነውና

ፍትህን አስረግጠን

ፈርተን  ዝም አንልም !!

( ሲና ዘ ሙሴ )

“ጦርነት ለወያኔ ዳንስ እንዴት ይሆናል ? ከራስህ አገር ዜጋ ጋር እየተጋደልክ ነው እንዴ ደንስ የሚሆነው ? ይህ ጦርነት እኮ ከውጫ ወራሪዎች ጋር የተደረገ ጦርነት አየደለም ? ” አለች ያቺ ቆንጂዬ ኢትዮጵያዊት ትግራይ ብለው ሰዎች በሰየሙት ክልል የተወለደች የእግዚአብሔር ንፁህ ፍጥረት ። ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እጆን ሰጥታ  ጋዜጠኛ አርያ ተሥፋማርያም  ለጠየቃት ጥያቄ በሠጠችው መልስ  ።

በግድ ፣ በወያኔ ጉልበት ለጦርነት የተሰለፈችው ወጣት ። ጦርነት ዳንስ የሚሆነው ከጠላት ጋር ፣ ከውጪ ወራሪ ጋር ለሀገርህ ሥትዋጋ ብቻ እንደሆነ አሥተምራናለች ። ብራቮ !  “ ንፁሐን እንደ ቅጠል በክላሽና በድሽቃ በሣንጃ እያለቁ ነው እንዴ ? ” ጦርነት የባህል ጫዋታችን ነው ። የምንለወ ? “

ይህ ተደጋግሞ ፣ በገዛ ወንድም ላይ የተፎከረ የወያኔ ካድሬዎች ባዶ ጩኸት ፤ የባዶ በርሜል  ድለቃ ነበር ። እና የገዛ ወገንን ጠልነት ፤ በአቶ  ጌታቸው ረዳ ( ዛሬ ሥራው መርዳት መሆኑ የተገለጠ ። ከከባድ ሚዛኖች ጎን የሚቆም  ። በሞቀበት አፋሽና አጎንባሽ የሚሆን  ። ከአሸናፊው ጎን ተሠልፎ ያሸናፊውን መዝሙር የሚዘምር … መርህ በሌለው ሰው ፣ ተደጋግሞ ሲነገር ነበር።  ከሁሉ የሚያሥቀው ” አብይን ኤርዶጋን አያድነውም ። ሳዳም ሁሴን አያድነውም ። ወዘተ ። ”  ያለው ነበር ። አንድ ጊዜም ተሳስቶ አብይ ፣ አብቹ ። ብሎ እንደነበረ አትዘንጉ ። )

ይህንን ፅሑፍ ሥፅፍ የአሥቴርን “ለመድክ ወይ ”  የሚለውን ዘፈን እያዳመጥኩ ነበር ።

” ለመድክ ወይ  ውጩን ከተማ ደጁን …ለመድከው ሁሉን ከተማ ደጁን …ቻለው ወይ ልብህ  …ያማረጥ ጀመረ ልብህ ሌላ  ቆንጆ …አንደበትህ እኔን አሥሮኝ እየዋለ …እንዴት አሥቻለህ ተፈጥሮ …እንደው ትዝ እያለኝ … ” ወዘተ እያለች የምታጎረጉረውን ። እኔም

” ለመድክ ወይ የማይክ እና ሃመርን ነገር

ለመድክ ወይ ማይኩን እና ሃመሩን

ለመድክ ወይ ተግሣፁን እና ኩርኩሙን

ቻለ ወይ ህሊናህ የማይክን ቀጭን ትዕዛዝ …” እላለሁ ።

በእርግጥ የማይክ ሃመር የነገ ግብ የአሜሪካ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ያውቁታል ። ከኢትዮጵያ ሠላም ያተርፋሉ ወይስ ያከሥራሉ ? ይህ በሚገባ ተገምግሟል ። አሜሪካንን የሚመሯት አንድ ፐርሰንት የናጠጡ ቱጃሮች  አትራፊ እንደሚሆኑ ባያረጋግጡ ኖሮ ወደዚህ ሠላማዊ መንገድ ህውሃት እንዲመጣ አይፈልጉም ነበር ።

እናም ህውሃትን ከተቀበረበት መቃብር እንዲወጣ አድርገውታል  ። ይህ ሰው በላና የጎደኞቹን አንገት የሚቆርጥ እጅግ ጨካኝ ( ከአይሲስ የከፋ ) ወደ ሥልጣን ከተመለሰ ለትግራይ ህዝብ ዳግም ሞት ነው ። የትህነግ ፖለቲካዊ ሃይማኖት ከአይሲሲመንፈሳዊ ሃይማኖት እጅግ የከፋ ሤጣናዊ ነው ።እናም  በጨካኝነቷ የምትታወቀው ወያኔ ተመልሳ ለሥልጣን ከበቃች  ይህ ለትግራይም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ነው ።

ጥንት የፊውዳሎች ጭቆና ባሥመረራቸው   ወያኔ በተባሉ ታጋዮች ሥም የሚጠሩ ሰው በላ ጭራቆች ዳግም ወደ ሥልጣን ወንበር ከተመለሱ ከሞትም ሞትነው ። ዓለም ምንም ፍትህ የሚባል ነገር እንደሌላትም  በዚህ አሥቀያሚ ድርጊት ይገለፃል ። እና ማንም ማይክ እና ሐመር የያዘ ወይም የኒኩለር ጉልበተኛ መንግሥት ፣ ህገወጦችን ፣ ወንጀለኞችን ፣ ንፁሐንን  አራጆችን እየደገፈ ነፃ የሆኑ አገራት መንግሥታትን እያሥፈራራና እጃቸውን እየጠመዘዘ ለድብቁ ብዝበዛው ማመቻቸት እንደሚችል የነቃው ጥቁር ህዝብ ይገነዘባል ።

ዛሬም እነ ማይክ እና ሐመር በንግግራቸው ከፍታ እያሥፈራሩ የአፍሪካን መሪዎች በፈለጉት አቅጣጫ እንዲጓዙ ያሥገድዷቸዋል ። ይህ ግን በኢትዮጵያ እንዲቀጥል ጀግኖች አይፈቅዱም ። የትግራይ ህዝብ ከአንድ ለአምሥት ጥርነፋ መላቀቅ ይገባዋል ። ኢትዮጵያም በካድሬ የማይመራ ፣ በደመነፍሰሰ እና በሥሜት ከጦዘ ኃይማኖታዊ  ፖለቲካ የተፋታ መንግሥት ያሥፈልጋታል   ።

በኢትዮጵያ ውሥጥ ፣  አንድ ሞኝ ሥለጮኸ፣ ሺ ብልጦች አብረውት መጮኽ የለባቸውም ። ሥለሣቀም ፣ ሥለጨፈረም አንዲሁ ። ወይም በተቃራኒው አንድ አሥመሳይ በገሃዱ ዓለም በአደባባይ ሥላለቀሰ  ከእርሱ ጋር ማልቀስ የለባቸውም ። ይህንን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ቆም ብለን ሥናሥብ ነው ።

ቆም ብለን በማሰብ ፣  በዕውቀት ይህንን የሁለት ባለጉዳዮች ( two party’s ) የተሰኘውን የሥምምነት ሰነድ እንፈትሸው  ።  ለመሆኑ የኢትዮጵያን ምርጫ ቦርድ አላውቅም ብሎ ፣ በራሱ ጉልበት በክልሉ ምርጫ ቦርድ አቋቋምኩ ብሎ በጠመንጃው አሥፈራርቶ ከተመረጠና አንገት እየቀላ በማሥፈራራት የትግራይን ክልል በኃይል ከሚያሥተዳድር አረመኔ ጋር ቀድሞውንሥ የአንድ ኩሩ አገር መንግሥት በአንድ ጠረጴዛ ላይ መቀመጥ ነበረበት ወይ ? የሰነዱን ቁንፅል ሃሳብ ብቻ ይፋ በማድረግ ፣ ሙሉውን ሥዕል በመሸፈን ዘላቂ ሠላም ማምጣት ይቻላል ወይ ? ያ ሁሉ መሰዋትነት ከአረመኔ ፣ ከሰው አራጅ እና ለህግ ከማይገዛ ህሊና ቢስ ቡድን ጋር ለመደራደር ነባራዊው ሃቅ  ይፈቅዳል ወይ ?

ኢትዮጵያን  የማይክን ጫጫታ እና የሐማርን ገዳይነት ፈርተን ፍትህ ሥትጨፈለቅ ዝም ብለን እጃችንን አጣምረን ቆመን ማየት አንችልም ።  የራሳችንን ጉዳይ ራሳችን እንፈታለን ። ሥንል ለእኔ ተንበርካኪ አንሆንም ማለት ነው ትርጉሙ ። ጥቅምት 24 ቀን 2013  ዓ/ም ኢትዮጵያን ለገደሉ  ሁሉ መህረት የለም ። ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት ማግኘት አለባቸው  ። በኢትዮጵያ አንደራደርም  ። …

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop