October 10, 2022
3 mins read

ቋቁቻ( pityriasis versicolor)

312345424 164578562843528 6259035810410414919 n

312345424 164578562843528 6259035810410414919 n

ቋቁቻ malassezia በሚባል የፈንገስ(fungus) አይነት የሚመጣ ሲሆን ብዙ ግዜ ወጣቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነዉ።

ይህ የ fungus አይነት በሁላችንም ሰዉነት የሚገኝ ሲሆን ለምን አንዳንድ ሰዎች ላይ ብቻ በሽታዉን እንደሚያመጣ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር የለም።

እሱም ገርጣ ገርጣ ወይም ጠቆር ጠቆር በሚሉ የቆዳ ለዉጥ ይታወቃል።

አብዛኛዉን ግዜ ደረትና ጀርባን የሚያጠቃ ሲሆን አልፎ አልፎ ፊት ፣ እጅና እግርን ልያጠቃ ይችላል።

ቋቁቻ ብዙ ግዜ በሞቃታማ የአየር ሁኔታ የሚከሠት ሲሆን የበለጠ ወንዶችን ያጠቃል።

አብዛኛዉን ግዜ ምልክት ባይኖረዉም አንዳንድ ግዜ ግን ልያሳክክ ይችላል። ይሁንና ቋቁቻ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም።

ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ

ላይ ችግር ነዉ::

ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡

ሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ፣ወዛማ ቆዳ ካለዎት፣· የሆርሞን መለዋወጥ

የበሽታ መከላከል አቅማችን መዳከም ቋቁቻ እንዲከሰት ወይም የሚያደርጉ ነገሮች ሲሆን

ቋቁቻን በተለያዩ የሚቀቡና የሚዋጡ መዳንቶች ማከም ይቻላል።ሆኖም ግን ሁኔታዎች ሲመቻቹለት የመመላለስ ፀባይ አለው።

ቋቁቻ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡

የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡

1.የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት

  1. ኢትራኮናዞል( እንክብል፣ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ)
  2. ኬቶኮናዞል( ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳ ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻሎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡

አንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል( በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡

ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንዴ ወይም ሁለቴ መዉሰድ ሊፈልግ ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

310373593 5553234168094670 5902404330092376771 n
Previous Story

በካይሮ የተዘረጋው ሰሞነኛ ህወሃታዊ ሴራ ከግብፅ፣ ሩዋንዳ እና ሱዳን እስከ ደደቢት በረሃ – በእስሌማን አባይ

military
Next Story

አንድ አፍታ ከኢትዮጵያውያን ወታደሮች ጋር በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል… በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop