የልዕለ-ኃያላኖች ሽኩቻ!!! የማይቌጨው የጦር አበጋዞች የጦርነት ንግድና የደም ገንዘብ የትርፍ አዙሪት!!!

ተስፋ (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
Tesfasays: April 15, 2022 at 5:55 am

ልዕለ-ኃያላን ሃገራት አምርተው የሚሸጡት የጦር  መሣሪያዎች  የሚሞከረው በምድረ ኢትዮጵያ ነው፣ ግማሽ ሚሊዮን  ወጣቶች ሞቱ፣ ስንቶቹስ አካላተ ጎዶሎ ሆኑ!!! የደም ግብራቸው ገንዘብ ነው!!!

በነጮች 1935 አንዲት እጠር ምጥን ያለች መጽሃፍ በአንድ አሜሪካዊ ጄኔራል ተጽፋ ነበር። የዚያች መጽሃፍ አርዕስት War Is a Racket ሲሆን የጻፈው Major General Smedley D. Butler ነው። በመጽሃፉ የጦርነትን ከንቱነትና የመነገጃ ብልሃትነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንዳንድ የኢኮኖሚ ጠበብቶች ደግሞ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ለአሜሪካ ጠቅሟታል። ከነበረው የኢኮኖሚ ድቀት እንድትላቀቅና አርፎ ተርፎም የጀርመን ሳይንቲስቶችን ለቅማ ወደ ሃገሯ በማምጣት ጨረቃን ለመርገጥ ቀዳሚዋ እንድትሆን አርጓታል ይላሉ። የሃበሻው ግብግብ ግን ከዚኛው እይታ በጣም የራቀ የመንደር ባንዲራ እያውለበለቡ የእኔ አመልካች እጣት ከአንተ አውራ ጣት ይበልጣል በማለት የሚሞሻለቁበትና የሚዘርፉበት የዘር፤ የክልል፤ የቋንቋ ስሪት ነው።

የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል እንዲሉ በውጭና በውስጥ ያሉ ጠላቶቻችንም በትንሿ እሳት ላይ ነዳጅ እያርከፈከፉ ይኸው ለዝንተ ዓለም ያጫርሱናል። 300 ሺህ የትግራይ ወጣቶችን ያስጨረሰው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዛሬ በትግራይ ምድር የሚሰራውን ውስጥ ገብቶ ለተመለከተ ልብስ አስወልቆ እብድ ያደርገዋል። ለእርዳታ የተላኩ ቁሳቁሶች፤ የህክምና መድሃኒቶች ሁሉ በግልጽ በገቢያ ላይ የሚቸረቸሩበት አትራፊዎቹ የወያኔ አስታጣቂዎችና ታጣቂዎች ለመሆናቸው ጭራሽ አያጠራጥርም። ነጻ አወጣንህ እየተባለ በስሙ የሚነገድበት የትግራይ ህዝብ ግን የሚበላው በማጣት ያለውን ለወያኔ ባለስልጣኖች በግማሽ ዋጋ እየሸጠ ለመኖር ሲፍጨረጨር ቀሪው መንገድ አዳሪ ሆኗል። ይህ ነው የጎሳ ፓለቲካ ውጤቱ። እንዴት 300 ሺህ የትግራይ ልጆችን አስፈጅተው እንቅልፍ ይወስዳቸዋል? መልሱ የደነዘዘ አዕምሮ ከራሱ ውጭ የሞተበትንም ሆነ ቆሞ የሚሰቃየውን ለማየት ጊዜ የለውም።

ዶ/ር እከሌ እንዲህ ብሎ፤ ፕሮፌሴሩ እንዲህ ተናግረው፤ የክልል መሪው እንዲህ እንዲያ አሉ ስንባል የምንሰማና የምንከተል ጅላ ጅሎች እኛ ነን። ከእነዚህ ይልቅ በገጠር የሚኖር አራሽ ገበሬ የሚሰጠው ፍርድና እይታ ለእውነት ይጠጋል። ግን የተማረ ይግደለኝ ለሚል ህብረተሰብ ይኸው የተማረውንና ተምሮ የደነቆረውን ጨካኝ ጣለበት። መማር ብቻውን ፋይዳ የለውም። ለዚህ ማሳያው የዓለም የጤና ጥበቃው ዳሬክተር መርጦ አልቃሽ መሆን ዋንኛ አመላካች ነው። የስራ ዓላማው ለዓለም ሆኖ እያለ እሱ በመንደር ላይ ቆሞ ያላዝናል። ለትግራይ አያስብ እያልኩ አይደለም። ይገባል ግን ሌላውስ ወገኑ አይደለምን? ወያኔን በመላ ከስልጣንና ከአዲስ አበባ ከገፈተሩት በህዋላ ሆይ ሆይ ማለቱ የተለመደ የፓለቲካ አራጋቢዎች ጉዳይ በመሆኑ በውጭ ነገሩን ገና ከጅምሩ ተመልክቸዋለሁ። ችግራችን አጀማመሩ ላይ አይደለም። መሃሉና ፍጻሜአችን ላይ ነው። ወያኔና ሻቢያ በጥምረት የገፈተሩት ደርግ ራሱ ለውጡን ሲጀምር ” ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” ነበር ያለው። ግን 60ዎቹንና ንጉሱን ከገደለ በህዋላ አፉም እጅም ስለተፈታለት ትውልድን አጥፍቶ ለሌላ በላተኛ ህዝቡንና ምድሪቱን አስረክቦ አወዳደቁ የሮም ሆነ። ወያኔም ወዶም ባይሆን ተገፍቶ መቀሌና በዓለም ዙሪያ ከመሸገ ወዲህ የድሃ ልጅ ማስጨረስ ቋሚ ተግባሩ ሆኗል። በሱዳን የተሰደድ ሳይቀሩ በግድና በውድ እየታፈኑ በሱዳንና በግብጽ ረዳትነት ሃገራቸውን እንዲወጉ እያደረጓቸው ነው። በዚህ ሁሉ አትራፊዎቹ ግን በሰው ደም የሚነግድት የወያኔ ካድሬዎችና መሪዎቻቸው ናቸው። ትርፋቸው እኛን እያባሉ መሰንበት ነው። ወደ ኦሮሞ ተረኞችና አሽቃባጭ የአማራ መሪዎች ስንመለስ ደግሞ ወረፋው የእኔ ነው የሚሉትን ጠባብ ብሄርተኞች በብሄራቸው ሲነግድ ማየት ያንገፈግፋል። ጉቦው፤ እስራቱ፤ ፍቺው፤ መልሶ መታሰሩ፤ ከሥራ መባረሩ፤ ዝርፊያው ወዘተ.. ለውጥ ሳይሆን ነውጥ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። በተለይ ምንም የማያውቁ ገበሬዎችን አማራ ናችሁ በማለት መግደል፤ ማፈናቀል፤ አልፎ ተርፎም ጠልፎ ለሱዳኖች ሰውን እንደ እንስሳ መሸጥ የተለመደ እየሆነ መጥቷል። ወያኔ በከፈተው ጦርነት ወሎን ጎንደርንና አፋርን እያወደመ ሽዋ ድረስ እንዲገባ የተደረገው ለምን ይሆን? ሰው በቁሙ የሚያቃጥል ወገን እንዴት ከእንስሳ ይለያል? የጦርነት ንግድ የጦፈው በሁሉም ክልሎች ነው። ጥይት እንደ ስንዴ ተሰፍሮ የሚሸጥበት ምድር ቢኖር ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ተተኳሽ ይሁን አይሁን ግድ የለውም። ይገዛዋል። በሬውን ላሙን እየሸጠ፤ ቤቱን እያፈረሰ ይታጠቃል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ ወጥመድ ተይዟል!!! ‹‹የጫካው ኢኮኖሚ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣ በፍፁም ሣር አይበላም!!!›› - ሚሊዮን ዘአማኑኤል

በዚህ ሁሉ ግን አትራፊዎቹ እኛን ማገዶ የሚያደርጉት እናውቅልሃለን የሚሉን ሁሉ ናቸው።

በስመ ነጻነት ባርነት የሰፈነባት አህጉር ቢኖር አፍሪቃ ቀዳሚዋ ናት። 30 ዓመት ሙሉ የተለፋበት የኤርትራው ነጻነት ዛሬ ሰው በየት በኩል ልውጣ የሚልባት ምድር ሆናለች። ከበሮ እያስመቱ በየአመቱ ያስጨፍሩ የነበሩት ወያኔዎች ከነጻነት ይልቅ ባርነትና ፍርሃትን በትግራይ ህዝብ ላይ ጭነው እነርሱና ቤተሰቦቻቸው እፎይ ብለው በውጭ ይኖራሉ። ማን እየሞተ ማን እንደሚኖር ዛሬ ብቻ ሳይሆን በፊትም የምናውቀው ነው።

በቅርቡ እንግሊዝ በሃገሯ ያሉ ስደተኛን ሩዋንዳ ወስዳ ለማስፈር መወሰኗን አስታውቃለች። በነገራችን ላይ ከኪጋሌ 50 ኪ.ሜ ወጣ ብሎ ከሊቢያ የመጡ ሃበሾችና ሌሎችም ስደተኞች በአንድ የመንግስታቱ መጠለያ ውስጥ ይኖራሉ። ተስፋቸው ወደ ሌላ ሃገር መሻገር ነው። ወደ ሃገር መመለስ አይታሰብም። አንድ ኤርትራዊ እንዳለኝ ” ከዚህ ደርሻለሁ ከአሁን በህዋላ እንኳን በህይወቴ አስከሬኔ ወደ ኤርትራ አይሄድም” ይህ አያሳዝንም? ያች ውብ ምድር በራሷ ልጆች የመከራ ዝናብና ዶፍ ሲወርድባት። አንዲት ልጅ የያዘች የአዲስ አበባ ወጣት ደግሞ ከኤርትራዊው ጎን ቆሟ እኔም እንደ እሱ ነው ጭራሽ ያቺን ምድር ማየት አልፈልግም። እግዚኦ አሰኝቶ ሱባኤ ያስገባል ሰሚ ከተገኘ። ስለ ረዋንዳ ሁኔታ በቅርቡ የተጻፈ አንድ መጽሃፍ ሳነብ (Do Not Disturb by Michela Wrong) ብዙ ነገር መታዘብ ይቻላል። ባጭሩ የምታየውና እየሆነ ያለው አብሮ አይሄድም። ግራም ነፈሰ ቀኝ የእድሜ ልክ መሪዎች ሲሞቱ ወይም በነውጥ ሲገለበጡ የሚፈርሰው የእነርሱ አገዛዝ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም መሰረታዊ ተቆሞች ናቸው። ሩዋንዳ ምን ኑሯት ነው የአፍሪቃን ስደተኞች ከአውሮፓና ከሊቢያ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነችው? ምን ቢከፈላቸው ነው? ደግሞስ የመንግስት ለውጥ ቢደረግ የእነዚህ ሰፋሪዎች እድል ፈንታ ምን ይሆናል? ይህን ስጠይቅ መልሱን ቀደም ብዬ ካነበብኩት መጽሃፍ ውስጥ አግቸዋለሁ። መጽሃፉ The World For Sale: Money, Power, and the Traders Who Barter the Earth’s Resources by Javier Blas. ሁሉም ሸቀጥ ነው፤ ሸቃጭ ነው። ሰንዴ ሰፈሩልን ትጥቅ ሰጡን በባዶ ሆኖ አያውቅም። የዛሬዎቹ አለቆቻችንም ሆነ መቀሌ ላይ የተወሸቁት አይናቸውን ከፍተው በማየት ለህዝባችንና ለምድሪቱ ቢያስቡ መልካም ነው። ሰው እንዴት ሁሌ በለቅሶና በሃዘን ይኖራል? የሚሰረቀውና በግፍ የሚነገደውስ ለየትኛው እድሜ ነው? ለዚያውም የሃበሻው እድሜ በዛ ከተባለ 70 ከተገባ ነው። ዘር፤ቋንቋ፤ሃይማኖትና የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካን አክ እንትፍ በማለት እይታችን ሃገራዊ፤ አህጉራዊ፤ አለም አቀፋዊ አልፎ ተርፎም ለሰው ልጆች መብት የማይሟገት ከሆነ ሌላው አተላና የሻገተ ፓለቲካ ነው። ወያኔና የብልጽግና (የድህነትና መከራ) አለቆቻችንም ጊዜ እያለ ተስማሙና ህዝባችን እፎይ ይበል። ካልሆነ ልክ እንደ ሊቢያው ጋዳፊ፤ እንደ ሩማኒያው መሪ ህዝብ የተነሳባችሁ ቀን ምንም አይነት የጦር መሳሪያና የሃብት ክምር አያድናችሁም። እብደታችሁ ይብቃ። እኔም በቃኝ! (ትልቅ የስነፁሁፍ ተሰጥኦ አለህና ለወገኖችህ እውቀትህን አካፍል)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወጪ ንግድ በኢትዮጵያ - ክፍል 1 - ክፍል 2

Quotes from book War Is a Racket Smedley D. Butler War Is a Racket is a speech and a 1935 short book, by Smedley D. Butler, a retired United States Marine Corps Major General and two-time Medal of Honor recipient. Based on his career military experience, Butler discusses how business interests commercially benefit, such as war profiteering from warfare. He had been appointed commanding officer of the Gendarmerie during the United States occupation of Haiti, which lasted from 1915 to 1934. …more „

  • War is a racket. It always has been. It is possibly the oldest, easily the most profitable, surely the most vicious. It is the only one international in scope. It is the only one in which the profits are reckoned in dollars and the losses in lives.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) War is a racket (1935) Source: War Is a Racket 0
  • „What business is it of ours whether Russia or Germany or England or France or Italy or Austria live under democracies or monarchies? Whether they are Fascists or Communists? Our problem is to preserve our own democracy. And very little, if anything, has been accomplished to assure us that the World War was really the war to end all wars.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „I spent 33 years and four months in active military service and during that period I spent most of my time as a high class muscle man for Big Business, for Wall Street and the bankers. In short, I was a racketeer, a gangster for capitalism.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „The normal profits of a business concern in the United States are six, eight, ten, and sometimes twelve percent. But war-time profits — ah! that is another matter — twenty, sixty, one hundred, three hundred, and even eighteen hundred per cent — the sky is the limit.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „But what does it profit the men who are killed? What does it profit their mothers and sisters, their wives and their sweethearts? What does it profit their children? What does it profit anyone except the very few to whom war means huge profits? Yes, and what does it profit the nation?“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „For a great many years, as a soldier, I had a suspicion that war was a racket; not until I retired to civil life did I fully realize it. Now that I see the international war clouds gathering, as they are today, I must face it and speak out.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „And what is this bill? This bill renders a horrible accounting. Newly placed gravestones. Mangled bodies. Shattered minds. Broken hearts and homes. Economic instability. Depression and all its attendant miseries. Back-breaking taxation for generations and generations.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „Out of war nations acquire additional territory, if they are victorious. They just take it. This newly acquired territory promptly is exploited by the few — the selfsame few who wrung dollars out of blood in the war. The general public shoulders the bill.“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935) 0
  • „How many of these war millionaires shouldered a rifle? How many of them dug a trench? How many of them knew what it meant to go hungry in a rat-infested dug-out? How many of them spent sleepless, frightened nights, ducking shells and shrapnel and machine gun bullets?…How many of them were wounded or killed in battle?“ —  Smedley D. Butler, book War Is a Racket War is a racket (1935
    Source: https://quotepark.com/works/war-is-a-racket-5894/
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ቀውስና የአይኤምኤፍና የዓለም ባንክ ፕራይቬታይዜሽን ሴራ!!! የብሔራዊ የጋራ ኃብታችን በኦሮሙማ ውርስና ስልቀጣ?

ማስታወሻ፤ከድርገጹን በመክፈት war-is-a-racket ሙሉውን  ፁሁፍ ያንብቡት፡፡ ተስፋን እያመሰገንን መልካም ንባብ ይሁንልን፡፡

1 Comment

  1. ገና ከጅምሩ ጀምሮ ዓለምን ሲያምሱ የኖሩት እነዚህ አፍሪቃን እንደ ቅርጫ ሥጋ የተቀራመቱት የነጭ ሃይል ስብስቦች ዛሬም ከዓመታት በህዋላ ላንድ ጭድ ላንድ ክብሪት እያስታቀፉ እያጋደሉን ይገኛሉ። በተለይም የጥቁሩን ዓለም ልዕልና የማይፈልጉት እነዚህ ስመ ዲሞክራሲ ሃይሎች በጎናቸው ዓረቦችንና መሰል ሃገር በቀል አጥፊ ድርጅቶችን በማሰለፍ ዝንተ ዓለም እያስለቀሱን ይገኛሉ። እኔን ብሽቅ የሚያደርገኝ በውጭ ሃገር ያሉ የዘር ፓለቲከኞች የሚያሰሙት የእብደት ድምጽና ድጋፍ ነው። በተለይ ወያኔን የሚደግፉ ሃይሎች የባሰውን ያሳምሙኛል። የትግራይ ህዝብ መከራ እንዲያባራ ወያኔን ከትግራይ ህዝብ ጀርባ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል እንደመታገል ለማይቀረው ድል ተዘጋጅ ተፋለሙ ከጎናችሁ ነን ሲሉ ተማረ አልተማረ የዘር ፓለቲከኛው ሃበሻ በጠና የታመመ እንደሆነ ያሳያል። በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የዘር ፍጅት ሁሉ ቀዳሚ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን። ሌላው ሁሉ ስንቅና ትጥቅ አቀባይ የራሱን ጥቅም ያነገበ የነጭና የዓረብ ቅይጥ ሃይል ነው።
    ሲለመን አሻፈረኝ ብሎ ለ 3ኛ ጊዜ ጦርነት ውስጥ የገባው ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ደንታ የሌለው የራሱን መኖር ብቻ የሚናፍቅ ሃይል ነው። ወያኔ በታሪኩ ነገርን በድርድርና በሰላም የፈታበት አንድም ጊዜ የለም። ከበረሃ እስከ ከተማ ያለው ታሪክ በደምና በሸፍጥ የተለወሰ ነው። የእውቁ ከያኔ የኢያሱ በርሄ፤ የጄ/ሃያሎምና የሌሎችም ገዳይ ወያኔ ራሱ እንደሆነ ይታመናል። ከሰሞኑ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ነዳጅ መዝረፉን ስሰማና ሳነብ አንድ አሜሪካዊ ከረጅም ጊዜ በፊት ያጫወተኝ ነገር ትዝ አለኝ። ሥፍራው ሱዳን የስደተኞች ጣቢያ በአንድ ነው። በየቀኑ ከትግራይ ወደ ስደተኛ ጣቢያው መንገድ፤ ራሃብና ጥማቱ ከበሽታው ጋር አድክሞ በዚሁ ሥፍራ የተራገፉትን ሟችና ቋሚ ለይተን እርዳታ በመስጠት ላይ እንገኛለን። ወዲያው አንዲት የመድሃኒት ማጠራቀሚያ (እንደ ፋርማሲ ብጤ) ቀልሰናል። ሰው ይሞታል፤ ይታመማል። ሁሌ ሩጫ ነው። አንድ ቀን ጧት ስንነሳ ያቺ ፋርማሲ ቢጤ ተዘርፋ ባዶዋን ሆና አገኘናት። ዘበኞቹ መናገር አልፈለጉም እንጂ ማን እንደዘረፈው አውቀዋል። ቆይተን ስናጣራ ወያኔ ከሱዳን ወታደሮች ጋር ተባብሮ ካርቱም ገቢያ ላይ መድሃኒቶቹ ተገኙ በማለት አጫውቶኛል። ለትግራይ ህዝብ ወያኔ አስቦ አያውቅም። ድሮ በዘፈን ሴቷ የሳመችው ወደ በረሃ እንዲወጣ ያደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁን ደግሞ ባንዲራ ዘርግቶና እና ቁስለኞችን አሰልፎ ጦር ሜዳ ካልሄዳችሁ ትግራይ የእናንተ አይደለችም እያለ ህጻናትን ጦርነት ይማግዳል። ለዚህ ነው በውጭ ያሉ የትግራይ ልጆች በስሜትና በውሸት የፕሮፓጋንዳ ወሬ ከመነዳት ይልቅ ሰብሰብ ብሎ ነገርን መርምሮ እልፍ መከራ በላዪ ላይ ያለማቋረጥ የሚወርድበትን የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ፍትህ እንዲያገኝ መታገል ያለባቸው። ግን ውሻ በበላበት ይጮሃልና የወያኔ ፍርፋሪ ለቃሚዎች ይህ ነገር አይታያቸውም። መኖርን የሚለኩት እነርሱና የቅርብ ዘመዶቻቸው ጠግበው በማደራቸውና በሰላም መኖራቸው ነውና። ጠባቡ ብሄርተኛ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ለሚራቡት ዘመዶቼ ገንዘብ መላኪያ መንገድ አጣሁ ብሎ ከማላዘን ጦርነቱ ይቁም፤ በቃ ማለት ነበረበት። ከዚህም በዘለለ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ነውና አስቸጋሪ ቢሆንም ገንዘብ ትግራይ ውስጥ በመከራም ቢሆን መላክ ይቻላል። እውቁ አሜሪካዊ ገጣሚ Charles Bukowski እንዳለው “We don’t even ask happiness, just a little less pain” መቼ ነው ህዝባችን ያን የሚያገኘው? መቼ ነው ጠበንጃ አንግቶ እንዘጥ እንዘጥ ማለት የሚቀረው? ለእኛ ያሰቡ እየመሰሉ ሲያጋድሉንና መከራችን ሲያራዝሙብን የምንነቃው እና አንፈልግም መገዳደል የምንለው? በዚሁ አሜሪካዊ አንድ ግጥም ሃሳቤን እዘጋለሁ። ፈልጉና ስንኙን እዪት/አዳምጡት። ግጥሙ “The Genius of the Crowd by Charles Bukowski” መገዳደል ይብቃ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share