በአንድ ራስ ሁለት ምላስ – እኝህ አቢይ አህመድ የፖለቲካ ሞተራቸው ነክሶባቸው ይሆን እንዴ?

የተከበሩ አቢይ አህመድ ሁለት የተለያዩ አስተሳሰቦችን ባንድ ጊዜ፤ ሁለት አይነት እንቅስቃሴና ለሁለት የተከፈለ ባህርይ የሚያጣምር የአይምሮ ችግር ወይም የመገለልና የማንነት ቀውስ (dissociative identity disorder (DID)) ይኑራቸው አይኑራቸው በእርግጠኝነት መናገር አልችልም:: ነገር ግን ካስተዋልኳቸው ነገሮች በእርግጠኝነት በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ወይም ድርብ ተፃራሪ አስተሳሰብ ባለቤት መሆናቸውን እረዳለሁ::
ታላቁ ጆርጅ ኦርዌል 1984 በተሰኘው መፅሃፉ “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ወይም መንታ ተፃራሪ አስተሳሰብን ሲገልፀው ‘ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦችን በአንድ ጊዜ መያዝና ሁለቱም ተፃራሪ ሀሳቦች እውነት ናቸው ነው ብሎ ማመንና አመራርንና ህዝብ ስነልቦናዊ መጠቀሚያ በማድረግ የሚከወን የፕሮፖጋንዳ አካል ነው” ይላል:: በመቀጠልም “በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) አስተሳሰብ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ እንደ ፓርቲ ህዝቡ የራሱን ግንዛቤ እንዳይጨብጥ ህሊናውን የሚቆጣጠርበት ዘይቤ ወይም ብልሃት ነው:: በተጨማሪም ህዝቡን ለማሳመን ህዝቡ እውነትነቱን ከሚያውቀውን ጉዳይ ተቃራኒውን በማስቀመጥ እውነትን መበረዝና ማዛባትም ነው:: በአንድ ራስ ሁለት ምላስ (Doublethink) ማወቅና አለማወቅን በጥንቃቄ የተቀመሩ ውሸቶችን በመደርደር አስፈላጊ የሆኑ መዘንጋቶች እንዲሰፍኑ ማድርግ እንዲሁም አስፈላጊ ሆነው ሲገኙ እንደገና ለትውስታ ማብቃት እንደገናም ማስረሳት ነው::” ሲል የዘረዘረው የድርብ አስተሳሰብ ይዘትን ያሰፈረበት ዝነኛ መጣጥፉ አሳምሮ በሚገባ ይገልፃቸዋል::
ይሄው ነው!

Hailu AT

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠ/ሚ አብይም ፤ ታጋይ ዘመነ ካሴም ወደ ጦር ሜዳ የወረዱት ሃገር ለማዳን ነው ! - መስከረም አበራ

1 Comment

  1. ኦርዌላዊ

    ከአብዮቱ በፊት (እኛ ሳንወለድ) በእንግሊዝ የኖረ

    ኦርዌል የተባለ ደራሲ ነበረ

    ገና ስለሚመጣው የጭቆና ዓለም

    በትንቢታዊ መልክ ያልጻፈው ጉድ የለም

    ሰውን ከብት አድርጎ በእሺታ ለመግዛት

    የኅሊናን ሚዛን ምኅዋሩን ማዛባት

    ገልብጦ ማሳመን ታቹን ብሎ ላይ

    ምድርንም ሰማይ

    ይሆናል አላማው

    የመጭው ቀን ገዢ ሲቀመጥ በማማው

    ብሎ ነበር ኦርዌል

    ዋዛ በሚመስለው የዚያኔ ድርሰቱ

    እንዲህ ሊያስደምመን

    ዛሬ በኛ ጊዜ ኦርዌላዊ ዐለም ፈጥኖ መከሰቱ

    እናማ

    ቀን ቀንን አራውጦ

    ባሕሩን ተሻግሮ አህጉርም አቋርጦ

    የኦርዌልም ትንቢት በኛ ደረሰና

    ጦርነት ሰላም ነው ውድመት ብልጽግና

    (እስር ነጻነት ነው ቅሌት ሥልጣኔ

    መፍረስ መገንባት ነው ብክነትም ምጣኔ

    ማነስ መደመር ነው

    አርበኛ ሲሳደድ ባንዳ ሆኖ አለኝታ

    ሌሊት ንጋት ተብሏል ውርደትም ከፍታ።

    አሁንገና ዓለማየሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share