July 26, 2022
3 mins read

ለነፃነታችንና እየተጣሰ ላለው የፍትህ ስርአት ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ 14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት ገለፁ

294705779 637324534625472 2151411374608759883 n
294705779 637324534625472 2151411374608759883 n
ዛሬ ባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤት በነ ዶ/ር ወንድወሰን አስፋው መዝገብ የቀረቡት የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሊወሰዱ መሆኑ ታውቋል።
በዛሬው የባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤት ችሎት ውሎ የፌደራል መሪማሪ ፖሊስ መዝገቡ ተዘግቶ 14ቱ ፋኖዎች ከባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወደ አዲስ አበባ አራዳ ምድብ ችሎት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተላልፈው ይሰጡ ሲል የፌድራል መርማሪ ፖሊስ የባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤትን ጠይቋል።
የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው የመዝገቡን መዘጋት የማይቃወሙት መሆኑን ገልፀው ከባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ት ወደ አራዳ ምድብ ችሎት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሊሄዲ የሚችሉበት ምንም አይነት የህግ አግባብ አለመኖሩን ጠቅሰዋል።
ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩት እዚሁ በባህርዳር ከተማ መሆኑንና ጉዳዩም የፌደራል ሃላፌነትና ውክልና ያለው የባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤት እየተመለከተውና የያዘው ጉዳይ በመሆኑ ወደፌደራል አራዳ ምድብ ችሎት የሚያስኬድ ምንም አይነት ህጋዊ አግባብ የሌለው መሆኑን ገልፀዋል።
አራዳ ምድብ ችሎት የፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤትን የሚያዝበት ህጋውይ መሰረት የለም ብለዋል።
አፋኙ ቡድን ከዚህ በፊት ከሰባትሚት ማረሚያቤት ነፁሃንን አፍኖ አንደወሰድው ሁሉ አሁንም ይሃንኑ ለመድገም ከልሆነ በስተቀር ወደ አዲስ አበባ አራዳ ምድብ ችሎት የሚሄዱበት ምክንያት የለም።
14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባለት በበኩላቸው ከህግ አግባብ ውጪ በማይታወቅ አፋኝ ቡድን ተይዘን የትም የማንሄድ መሆኑን አፋኙ ቡድንም ይሁን ህዝብ ሊይቅልን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ነገር ግን ህግ በመጣስ አፍኖ ለመውሰድ ሙከራ ካለ ግን ለነፃነታችን እና እየተጣሰ ላለው የፍትህ ስራአት ስንል ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል።
ቀን 19/11/2014 ዓ/ም
ባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት
የአማራ ፍኖ አንድነት አመቻች አባላት

1 Comment

  1. ይገርማል አህመዲን ጀበል፤ጁዋር መሃመድ፤አቡ ምናምኖች አልሸባብ ጋር ሁኖ ሱማሌ ወንድሞቻችንን እያስገደሉ በነጻነት ይኖራል እነዚህ የአንድነት ሃይሎች በወከባ መከራቸውን ያይሉ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድ፡፡ ሙስጠፌ ወንድማችን ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Paula Gil
Previous Story

የስፔን ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ጉብኝትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

296150476 1501522863635041 710486661796228725 n
Next Story

የኢትዮጵያ ኤንባሲና አየር መንገድ ባልደረቦች ለአትሌቶቻችን በኒው ዋርክ አይሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበልና ሽኝት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop