ከሚኒያፖሊስ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ምእመናን የተላለፈ መልእክት

 

በቤተክርስቲያናችን ውስጥ መከፋፈልና ሁከት እንዲፈጠር አንፈቅድም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንንም ለማዳከም ከሚሰሩና ከሚያሴሩ አካላት ጋር አንድነትና ኅብረት የለንም።

Read Full Story in PDF

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ትህነግ”: በሞተ ርዕዮተ-ዓለም የሚመራ፣ ለውጥን የሚፈራ ድርጅት - ስዩም ተሾመ

9 Comments

  1. እኛ አሁን ያለነው ከቤተክርስቲያን ጋር ነው። አዎን ከአቶ ስብሐት ጋር አይደለንም አዎን ከአቶ አባይ ጸሐዬ ጋር አይደለንም አዎን በእነዚህ ሰዎች ከሚመሩና ለእነርሱ ካጎበደዱ ጳጳሳት ጋር አይደለንም አዎ ቤተክርስቲያንን ከሚያዳክሙና ከሚያቃጥሉ ምእመናንን ከሚያሳርዱ ከሚያሳድዱ ጋር አይደለንም! እኛ ከቤተክርስቲያን ጋር ነን። ከቤተክርስቲያን ጋር ለመሆን መገለጫው ምንድነው? ከላይ ከተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ጠላቶች፣እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን ሳይሆን ምድራዊ ባለስልጣናትን ከሚያገለግሉ ጋር መወገን ነው ወይ? ከቤተክርስቲያን ጋር መሆን ማለት ከእደነዚህ አይነቶቹ አጥፊዎች መለየት ሥራቸውን መቃወም ነው እነደ ደብረሰላም ቤተክርስቲያን። ስለቤተክርስቲያን ታሪካዊ ጠላቶች ሰብከው ወይንም ተናግረው መልሰው ደግሞ ከእነሱ ጋረ እናብርና ቤተክርስቲያንን እንውጋ ማለት ነው ከቤተክርስቲያን መገለል መለየት ማለት። ከቤተክርስቲያን የተገለለች ቤተክረስቲያን ቤተክርስቲያንም አትባል! ምእመኑም እንዲህ አያጨናንቃትም ነበር። ዋናውን ችግር በማጣመምና ምእመኑን በማስደንበር እንኳን ለቤተክርስቲያን አንድነት ሊመጣ ይቅርና ለራስም ሰላም አይገኝም። በተረፈ ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት እንደሆነች በቅጡ መረዳትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።

  2. Aba ****** is the engine of this movement @ DSMA; he might be the first to fill the burn if he doesn’t cease playing with the fire. When his immigration status was in jeopardy the congregation was in the front line to fight for him and stop his deportation, he should have known better that his current immigration status was/is in a political asylum, seeking a political asylum and supporting the government in home is too contradictory. Aba you need to walk the walk

  3. አንዳንድ ካህናቶቻችን እና ዲያቆን ***** ወያኔ ወያኔ እየሸተታቸሁ ነው, እባካችሁን እንዳትገሙ ልምከራችሁ፥ ዋልደባ ሲታረስ, ዝቋላ ሲጋይ, መናንያን ሲደበደቡ, ከገዳማቸው ሲሳደዱ, ገዳማችሁ ከምትመለሱ እናታችሁ ማሕጸን ብትመለሱ ይቀላችኋል ሲባሉ,…. የት ነበራችሁ
    ለማንኛውም የታሪክ ዝቃጭ እና አተላ ከመሆን ተቆጠቡ, ደሞዛችሁን የሚከፍላችሁ ወያኔ ሳይሆን መዕመኑ መሆኑን ዘነጋችሁት ይሆን?????

    ጥላሁን ነው … ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም ያለው .. ነፍሱን ይማረው እና

  4. Well i have a lot of thing to say about the planer for all this problem in DSM. THIS MASSAGE IS GOING TO BE FOR ABA DO YOU KNOW OR FORGET YOUR POLTICAL ASSYLEM???? ABA STOP STOP! BE A FATHER YOU HAVE TO STAND FOR TRUTH ON FOR DOLLAR DOLLOR;.. FOR THE OTHER HODAMS LIKE AHDU, SENTAYO, LEKE TEGUAH GETUNE.WE HAVE A LOT EVEDENCE HOW YOU KESES ARE PLAN TO DESTROY DSM.

    STOP STOP. WE ARE NOT POLTICAN WE ARE eTHIOPIAN

  5. Some of the church problems you see here in America is aggitated by priests and
    fanatic youth choirs driven by ambition to control the church. Members unquivocally
    must stop them or purge them out. Yes keep away from mahebire Kidusan

  6. Board members are the BIG problems. I don’t think this has anything to do Aba & Board members are the one who is turning the side on the wrong side. They are selfish and thieves. Board members are the one who decided not to say or do anything while Weyane is burning churches. Were were you? you can ;t ignore that and call your self church/Board member. They all need to GO and we will be one and have peace.

  7. መልእክቱ ጥሩ ነው። አንዳነድ አስተያየት ሰጪዎች ግን የመልእክቱ ሃሳብ በውል የገባቸው አይመስልም። የሰው ስም እያነሱ የማይገባ ቃላት ከመጠቀምና ከመሳደብ መልእክቱ ላይ ብቻ አተኩራችሁ አስተያየታቸሁን ብትሰጡ የተሻለ ነው።ጽሑፉን ያዘጋጁት አካላት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እየተካሔደ ያለውንና የታሰበውን ሁኔታና እንዲሁም በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን ጥቃት በደንብ የተገነዘቡ ይመስላል። የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አካል መሆኗ አያጠራጥርም። ሆኖም ስልጣን ላይ ባለው የወያኔ መንግስት ጣልቃ ገብነት የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር መከፋፈሉ የታወቀ ነው። ይህ ማለት ግን በስደትም ያሉትም ሆነ ባገር ውስጥ ያሉት ቤተክርስቲያናት ከእናት ቤተክርስ አናቸው ተለይተዋል ወይንም ተገልለዋል አያሰኛቸውም። የየትኛውን አባት አመራር እንከተል? በኢትዮጵያ ያሉት በመንግስት የሚደገፉና ቀኖና ቤተክርስቲያንን አፍርሰው ነው የተቀመጡት እየተባለ ስለሚከሰሱ በውጪም ያሉት አባቶች መፈናቀላቸውና መሰደዳቸው የታወቀ ቢሆንም የቤተክርስቲያኗ ማእከልም ከእኛ ጋር ተሰዷል ማለታቸው ምእመኑን ግራ ስላጋበው ከሁለቱም አመራር ተገልለን እርቀ ሰላም እስኪወርድ ድረስ የአባ እገሌንም የአባ እገሌንም ስም አንጠራም በማለት በውጪው አለም የሚገኙ ብዙ አብያተ ቤተክርስቲያናት ተቋቋሙ። በውጪው አገርም ከሚገኘው አማኝ በአብዛኛው በእነዚሁ ቤተክርስቲያናት እየተገለገለ ይገኛል። ይህን በመንግስት ጣልቃገብነት የተከሰተውን የአስተዳደር መለያየት እንደ ቤተክርስቲያን መከፋፈል መቁጠር በርግጥም ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳመለከቱት ስለቤተክርስቲያን መከፈል በቂ እውቀት አለመኖር መይንም ሆን ተብሎ ምእመናንን በማደናገር የራስ ጀሌ ለማድረግ የታቀደ ሴራ ነው። ጠበኛ ጳጳሳት ለዛውም በስልጣን ምክንያት በዘመናችን ተፈጠሩብንና ግራ ገባን። ይህም ይህን አሁን ያለውን ዝብርቅርቅ ሁኔታ አስከተለ። አሁንም መላው የቤተክርስቲያኗ ምእመን በአንድነት ሆኖ ጳጳሳቱ እርቅና ሰላምን እንዲያደርጉ በሚችለው ሁሉ ማሳሰብ አለበት ። ቤተክርስቲያኗንም በከፋፈሉትና እያወደሙ ባሉት አካላት ላይም በአንድነት መነሳት አለበት። አንዳድ ሰዎች የህዝቡን የአንድነት ጥማት በመመልከት አንድነትን በተሳሳተ መልኩ ሲተረጉሙት ይስተዋላል። ቤተክርስቲያኗን ከከፋፈሉና እያወደሙ ካሉ አካለት ጋር አንድ እንሁን በማለት ያንኑ አጥፊ ቡድን በመደገፍና በእርሱ በተሰየሙ መልእክተኞቹ አመራር ስር በመሆን የጥፋቱ አካልና ጉዳይ አስፈጻሚና ፈጻሚ ለመሆን ሲጣጣሩ ይታያል። አንድ መሆን የሚገባው ይህንን የአገርና የቤተክርስቲያን ጠላት በመቃወምና በመከላከል ዙሪያ መሆን ይገባዋል። ለቤተክርስቲያንም ዘለቄታዊ የአስተዳደር አንድነት መፍትሔው ይሔው ብቻ ነው። ሃሳቤ ጠበኞቹንና ተከታዮቻቸውን ባያስደስትም እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ብዬ ነው አስተያዬቴን የሰጠሁት። ይቅርታ።

  8. ፈጣሪያችን እስኪገለጽ ድረስ ባለንበት እንጽና
    ለመሆኑ ለወቅታዊው የቤተ ክርስያን ችግር ትክክለኛው መፍትሔ የቱ ነበር? ምንም እንኳ ሂደቱ ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት (ከወያኒ) ነጻ ነው ለማለት ባይቻልም ከላይ እንደገለጽነው የአባቶቻችን ልዩነት ጎልቶ የወጣው መንበሩን ማን ይያዝ በሚለው ጥያቄ እና ምላሹ ሆኖ በቀረበው የፓትርያሪክ ምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ በአንደኛ ወገን ያሰቀመጥናቸው ወገኖች (ሃገርበት ያሉት) እርቀ ሰላሙ እየቀጠለ ነገር ግን ያለምንም መዘግየት የፓትርያሪክ ምርጫ መካሄድ አለበት ሲሉ ሁለተኞቹ የበፊቱ መንበራቸው ይመለሱ በማለት ልዩነታቸውን ቢያስቀምጡም ለጊዜውም ቢሆን የመጀመሪያዎቹ ያሸነፉ በሚመስል መልኩ የብዙዎቻችንን ፍላጎት እነደረመጥ በማዳፈን የምርጫ ሽርጉዱ ተጀምሯል፡፡
    ለመሆኑ የየትኛው ወገን አስተሳሰብ ሊደገፍ ይገባዋል?
    ለቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ይረዳል በሚል የበፊቱ ፓትርያሪክ መንበራቸው ይመለሱ በሚለው ላይ ሁላችንም የምንስማማበት እና የሚገባ ነው ብንልም ድጋፋችንን የሰጠንበት ጉዳይ ሲሆን በታሪክ ሂደትም ሆነ በመጽሐፋዊ መመሪያ ቤተ ክርስቲያን የምታሰቀድመው አንድነትን በመሆኑ ብዙዎቻችን በማያሻማ ሁኔታ ድጋፋችንን መስጠታችን የተገለጠ ነው።ይህንን ማድረጋችን ስለ ሰላም እና እርቅ በማሰባችን ነበር ፦የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን አባቶችም ቅድሚያ ሊሰጡ የሚገባቸው የአባቶቻቸውን አሠረ ፍኖት የተከተለ፤ ቤተ ክርስቲያንን ከሚከፍል አጀንዳ ይልቅ አንድ የምትሆንበትን በመምከር ሊሆን እንደሚገባ ከዚህ መረዳት ለማንም አይከብድም፤ የልብ ክፋት እና ጥመት ከሌለ በቀር። ከታሪክ የምንማር ከሆነና በትውፊተ አበው የምንመራ ከሆነ የቅድሚያ ሁሉ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ብቻ ነው። ይህንን መፈጸም የሚያቅተው ቢኖር እንኳ ወደ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከሚገባ ራሱን እንደ እኛ ማግለል ወይም መገላል ይጠበቅበታል።

Comments are closed.

Share