ከባድ ውሳኔ አዎን! ማይክና ብዕር ሰቅዬአለሁ

June 24, 2022
ከባድ ውሳኔ ነው። በህይወት ዘመኔ እንዲህ ዓይነት የነፍስ ትንቅንቅ የሚጠይቅ ውሳኔ ላይ የደረስኩበት አጋጣሚ የለም። ወደፊትም ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። አሁን ግን ከባዱን ውሳኔ ወስኛለሁ። ከዚያ በፊት ከራሴ ጋር ዝግ ስብሰባ በተደጋጋሚ አድርጌአለሁ። ከነፍሴ ጋር ተሟግቼአለሁ። የሚቀርቡኝን ወዳጆች አማክሬአለሁ። በመጨረሻም መሆን ይኖርበታል ያልኩትን አድርጌአለሁ። ምርጫ የለኝም።
289584179 7631000313607884 4387515658350668255 nአዎን! ማይክና ብዕር ሰቅዬአለሁ። ከእንግዲህ በየትኛውም የሚዲያ መድረክ ላይ አልገኝም። ከምሰራበት EMS መልቀቄን የማሳውቀው በከባድ ሀዘን ነው። ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩኝም የቤተሰቤ ጉዳይ ግን ዋንኛው መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ። ከአራቱ የስንብት ምክንያቶች ሶስቱ ከእኔና ከቤተሰቤ ጋር የተያያዙ ናቸው። ባለፉት 16ዓመታት፣ ከሀገር ቤት አንስቶ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ውስጥ አብራችሁኝ የነበራችሁ፣ በዚህም በዚያም ጩኸት ስንጋራ በጋራ የነበርን ሁሉ ከልብ አመሰግናችኋለሁ።
ባልደረቦቼ በርቱ። በEMS በጋራ የጀመርነውን ራዕይ ከዳር እንደምታደርሱት ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም። አብሬአችሁ እስከ ደሴቲቱ ባለመዝለቄ አዝናለሁ። የተጀመረው መንገድ አባጣ ጎርባጣ ቢበዛውም በኢትዮጵያዊ ጽናት እንደምትሻገሩት እተማመንባችኋለሁ። አንድ ቀን ዳግም እቀላቀላችሁ ይሆናል። ለጊዜው እኔ ሩጫዬን አቁሜአለሁ። እናንተ ግን ጠንክሩ። ግፉበት። ኢትዮጵያ ከእናንተ ብዙ ትጠብቃለችና።
ለሁሉም ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቅልን። ከመጣባት ክፉ አደጋ ይታደጋት ዘንድ ጸሎቴን እቀጥላለሁ። በጥሞና ጊዜዬም ስለኢትዮጵያ ማሰቤን አላቋርጥም። ሀገሬ ልቤ ውስጥ ናትና ሁሌም፣ የትም አስባታለሁ። በተረፈ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ቸር ሰንብቱ!

3 Comments

 1. መሳይን እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው ምን ጉዳይ እንደሆነ የሚያውቀው ራሱ ነው። ግን የሃበሻው ፓለቲካ መገሻለጥ፤ ከእውነት በራቀ መንገድ መራኮት፤ ለዘሬና ለጎሳዬ ሳትዘፍን፤ ሳትጽፍ፤ እኛን ረስተህ እነዚያን የሚል ተልካሻ ህብረተሰብ በመፈጠሩ ፓለቲከኞች፤ ከያኒዎችንና ጋዜጠኞችን ባጠቃላይ ጠቅለል ያለ ከእውነት ጋር የሚቃረብ ሃሳብ ያላቸውን ያለምንም ማስረጃ ያሳድዳል፤ ያስፈራራል፤ የቤተሰብንና የልጆችን ሰላም ይሰርቃል። በማንም ሃገር ሰው በዘሩ፤ በቋንቋው ተለይቶ እንደ እንስሳ እየታሰረ በግፍ አይጨፈጨፍም። ከፍርሃቷ የተነሳ “ወላሂ ከዚህ በህዋላ አማራ አልሆንም” ያለችውን ህጻን ሴት እየሳቁ የሚገሉ አውሬዎች ያበቀለችው የወለጋ ምድር ነገ ዛሬ በኦሮሞነቱ የሚጀነነውን ኦሮሞ ኦሮሞው ሲበላው ማየታችን አይቀሬ ነው። የኢትይጵያ ፓለቲካ የመበላላት ፓለቲካ ነውና! ስሙን እየቀየረ የብሄር ነጻ አውጭ፤ ሶሻሊዝም፤ ኢምፔሪያሊዝም ቢለንም ዞሮ ተመልሶ እንደ ድር አውሬ መጠፋፋት ነው።
  የዛሬ የፓለቲካ አዝማሪዎች የሚሉትን መስማት ያሰለቻል። ፍትህ፤ ህግ በሌለበት ምድር ላይ በልመና፤ በምልጃ ከሰማይ የሚወርድ አንዳች ነገር የለም። መሳይ የጋዜጠኝነት ሙያውን በገዛ ፈቃድ ማቆም በራሱ ፈቃድ እንዳደረገው ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ነገሩ ውስብስብ ነው። ሰው ስንት ጊዜ እንቅልፍ ያጣል፤ ስንት ጊዜስ ቆስሎ ይድናል፤ ስንት ጊዜስ በቤተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ለከፋና ስድብ ይታገሳል? ስንት ጊዜ የለሌ ስም ተለጥፎበት ይዞራል። የሃበሻ ፓለቲካ የተኩላ አስተሳሰብን የሚከተል ነው። Wolf Packs ብዙ ጊዜ ጥላቸው በድንበር ነው። ሲጋደሉም ደንበር ለይተው ነው። አፓርታይዲቱ ኢትዮጵያም በክልል ተሸንሽና ሞት በሩ ድረስ አንኳኩቶ እስኪወስደው ድረስ የሌላው ሞትና ሰቆቃ ምንም የማይመስለው የደነዘዘ ህዝብ በዘር ፓለቲካ ተመርዟል። ሰው በሰውነቱ መመዘኑ ቀርቷል። ባጭሩ የኢትዮጵያ ፓለቲካ በፊት የበላቸውን ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖታቸውን ሳንመነዝር ብናጠና እልፍ ናቸው። የሃገሪቱ ውድ ልጆች የተቀነጠሱት ለሃገር ለወገን እናስባለን በሚሉ ጠበንጃ አንጋቾችና ዘረኞች አለቆቻችን ነው። የሚገርመው አንድ ሊወጣ ከጅሎ ወድቆ በተንኮታኮተበት መሰላል ያለምንም ጥገና ክፋትና ተንኮልን ተላብሶ እንደገና ሊወጣ ሲሞክር ወድቆ መፈጥፈጡ ለቋሚ እንዴት ትምህርት እንደማይሆነው ጭራሽ ሊገባኝ አይችልም።
  50 ዓመት ሙሉ ኡ ኡ ስንዴ አቀብሉኝ ተራብኩ ማለት አያሳፍርም? ነገር ግን ፓለቲካው ውሃ እንደሌለው ደመና ሰውን እያማለለ ምድሪቱን ሰው አልባና የጉንድሾችና የሙታን መቃብር የበዛባት አርጓታል። ይህ ግፍና በደል ብሄርን ሳያማርጥ የሚገታበት ጊዜ መቼ ነው?
  የጋዜጠኛ መሳይ ብዕርም ሆነ ድምጽ ጸጥ በማለቱ ደስ የሚላቸው እንዳሉ ሁሉ የሚያዝኑም ይኖራሉ። የሻገተው የሃበሻ ፓለቲካ የሰዎችን ተሰጥኦና ተሟጋች ሃሳብ ጸጥ ርጭ የሚያደርገው አንድም በማሰር፤ ሌላም በማስፈራራት፤ ሲሞላለትም በመግደል ነው። አርሶ የሚያበላውን ገበሬ እንደ እርድ በሬ አንጋሎ የሚያርድ ድርቡሽ፤ የሚያስቡ ጭንቅላቶችን የሚቀላና የሚያንገላታ መንግስትና ስመ የብሄር ነጻ አውጪ ባርነት አምጭዎች እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ትላንት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም ከማንባት እንዲገቱ የሚደረጉት? ብቻ ሆድ ይፍጀው ይላል የሃገሬ ሰው። አብደናል። ለብሰን ብንሄድም ጤነኞች አይደለንም። የኢትዮጵያ ፓለቲካ ውሃ የጠማው ሰው የጨው ውሃ እንደሚጠጣ ነው። ቢጋትቱ ጥም አይቆርጥም ግን ሰውነትን መርዞ ለሞት ያበቃል። አይ ፓለቲካ ድንቄም ፓለቲካ የወስላታ ክምር። በቃኝ!

 2. Kene hamsa Aleka BaCha Debele iyeteqebelk yebelahew qilTim anqoh kememothi befit nuzaze bitinazez Tiru new. Anetena meselochih nachihu Abiy Ahmed silTanun consolidate indiyaderg ye hizbun andebet yezegachihut. Hizbun silemasastih inna silemachberberih nissiha satgeba yeserahewun bedel satkis aygdelh.

  Zare hullun ber asyizeh tesenabchiyalehu malet mallageT new.

 3. ደረጀ ሃብተወልድ አሁንም በአብይ ይምላል አንተስ ወደራስህ ተመልስሃል ንግግሩ አንጨት እንጨት ብሎኝ ወጣሁ ካልሆነ ወደ ዲሲ ይምጣና ታክሲ ገዝቼ ሰጠዋለሁ የገዳዮች አዝማሪ ከሚሆን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

173465
Previous Story

በቃ በተግባር አዲስ የሽግግር መንግሥት ጥያቄና የተማሪዎቹ ጥሪ

288358186 5211569042256804 2092752397205846827 n
Next Story

“የሰው ዘር የተባለ ሁሉ ይህንን ይስማልን የቀበሌው አስተዳዳሪ እኮ ከላይ በተላለፈልኝ ትዕዛዝ ጭፍጨፋውን አስፈጽሜያለሁ አለ ወላሂ” – የቶሌ ቀበሌ ነዋሪ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop