June 4, 2022
2 mins read

እስራአኤል በኢትዮዽያ የሚፈፀመውን አፈና የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ !!

Tana344444
Tana344444ሁለት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላት ካለፈው ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ፤ ማለትም እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የት እንደታፈኑ ማወቅ አልተቻለም።
የታፈኑት ወጣቶች ዘገየ በቀለ እና ዳምጤ ተቃጫ ናቸው። ዘገየ ባለፈው የ2013ቱ ሀገራዊ ምርጫ ባልደራስን ወክለው ለአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከተወዳደሩ ዕጩዎች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ አበባ፤ የካ አባዶ በሚገኘው የአጎቱ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ነው የታፈነው። አጎቱ አቶ ይትረፍ ድንበሩም አብረው እንደታፈኑ የደረሱበት አለመታወቁን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ወጣት ዳምጤ ከ9 ቀናት በፊት ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል።
ቤተሰቦቻቸው አሁንም ድረስ በየፖሊስ ጣቢያው እየተመላለሱ ቢጠይቁም ሊያገኟቸው አልቻሉም።
284717929 598177498540176 2540570790760447041 n
ይህ በአንዲሀ እንዳለ፣ በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮዸያዊያን በኢትዮዸያ የሚፈፀመውን አፈና ፣ ማሳደድድና የዘር ማፅዳት በመቃዎም ዛሬ አርብ፤ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ቴልአቪቭ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ ላይ ነበር።
መፈክሮች ከአማርኛ በተጨማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጭምር ተነግረዋል።
በሀገረ እስራኤል የሚኖሩ ኢትዮዽያዊያን ከዚህ ቀደም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ እስራኤል በሄዱበት ጊዜ፣ ያረፉበት ሆቴል በር ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የስርዓቱን አፈና ማጋለጣቸው ይታወሳል።
ዘገባው—ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

1 Comment

  1. ኑሩልን ወገኖቻችን የእስራኤል ጠላቷ የእኔም ጠላቴ ነው ይል የለ? እናንተ ካላችሁ ወድቀን አንወድቅም ትንሳኤያችን በናንተ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

284122882 569472887876801 316385330156098153 n
Previous Story

የ ኢዜማ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ውጤት ማሳወቅ – ስመራጭ ኮሚቴ

282647322 2336782716478206 4932425828003934178 n
Next Story

ኢትዮጵያ ከህወሓት ጋር እየተደራደረች ነው? ኦቦሳንጆ ትላንት መቀሌ ዛሬ ባሌ ናቸው – መሳይ መኮነን

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop