“መንኪ ፖክሥ “ ምሥራቅ አፍሪካ ደርሷል ። በቦሌ ባይገባ በሞያሌ ፣ በቶጎ ጫሌ ና በአርት ሼክ ፤ በደሎ መና ፣ ወይም በቦረና ፤ አልያም በሞያሌ ወይም በመተማ ና ሁመራ ፣ በአፋር ፣ በአሶሣ እና በኦጋዴን ወዘተ ። ሊገባ ይችላል ። እናም በቅርቡ በኢትዮጵያም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ ህመምተኞች ሊኖሩን ይችላሉ ። በበኩሌ እንደባለሙያ ትልቅ ሥጋት አለኝ ። ምንም እንኳ ክፉኛ ከታመሙ የቫይረሱ ተጠቂዎች አንዱ ብቻ እንደሚሞት ፣ በጥናት ቢረጋገጥ ና በሽታው ባይካበድም ከወዲሁ ልዩ “ የመንኪ ፖክሥ “ ግብረሃይል ማቋቋም አሥፈላጊ ይመሥለኛል ።
ይኽ በሽታ አንድ ሁለት ቦታ እንደ ብጉር እብጠት አሣይቶ በማግሥቱ ፊትን እና ሰውነትን የሚወሩ እብጠቶች እንደማፈጥር ና እንደሚያሥደነግጥም ከወዲሁ ህዝብ መረዳት አለበት ። ለ21 ቀንም የታገሠ እና በቂ የምልክቶቹን መከላከያ መድሃኒት ያገኘ ህመምተኛ ሁሉ መዳን እንደሚችልም እወቁ ። እናም ለዚህ ለመንኪ ፖክሥ የግል ኳራንቲን ሥለሚያሥፈልግ ለመንግሥት ሠራተኞች ( የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ ) ልዩ የህመም ወይም “ የቀሣ “ ፈቃድ የያዘ መመሪያ ፣ በሚቋቋመው ግብረሃይል በኩል እንዲወጣ ቢደረግ መልካም ይመሥለኛል ። አለበለዚያ በሽታው በቀላሉ ሊዛመት ይችላል ።
መንኪ ፖክሥ ፣ በመባል የሚታወቀውን እና በመላ ሰውነት ላይ የተቀቀለ ማሽላ የመሠሉ ሆኖም ከማሽላ ተለቅ የሚሉ እባጮችን የሚፈጥረውን ቫይረስ በእንሥሣት ላይ በቸደረገ ምርምር ለሠጀመሪያ ጋዜ የተረጋገጠው በመካከለኛውና በምእራብ አፍሪካ በ1958 ዓ/ም እጎአ ነው ። በሽታው በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ግን በቀድሞዋ ዛየር በአሁኖ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፤ በ1970 ዓ/ም እጎአ መሆኑ በዓለም የበሽታ ድርሳን ውሥጥ ተመዝግቧል ። ያውም በቀይ ቀለም ። …
ይኸው በዓለም የበሽታ ድርሳን ውሥጥ በቀይ ቀለም የተመዘገበው ሰበቡ ቫይረሥ የሆነው ህመም እንሆ ዛሬ ና አሁን ከግንቦት 7 ( እጎአ ) ጀምሮ በኢንግላንድ ተከስቶ መላ አውሮፓን እና አሜሪካን እያሥፈራራ አፍሪካ ደርሷል ።
ይህ ኩፍኝ መሠል ሆኖም ከኩፍኝ መጠናቸው የጎላ እብጠቶችን በሰውነት በሙሉ ና በብዛት ደግሞ በፊት ገፅ ላይ የሚፈጥረው እና በትኩሳት ፣ በማንቀጥቀጥ ፣በራሥ ምታት ፣ በጀርባ ህመም ፣ በጡንቻ ህመም ና በጉሮሮ ህመም ፣ ሥሜት የሚታወቀው ወረርሺኝ ይኼን ያህል አሥጊና ለመቆጣጠርም የሚያዳግት መድሃኒት አልባ አይደለም ። ማንም ሰው እውቀትን በእውነት ሊገነዘብ የገባልና ይኽ በወረርሺኝ መልክ የተከሰተው በሽታ ከፈንጣጣ ጋርም የማይመሣሠል ነው ። ፈንጣጣ ወይም “ አንትራክስ “ በባክቴሪያ የሚመጣ ገዳይ በሽታ ነው ። ሃያላኑ አገሮች በላብራቶሪ አባዝተው በባዮሎጂ ጦር መሣሪያነት አከማችተው እንደያዙትም በውሥጥ አዋቂዎች እና በጠርጣሪዎች ይወራል ። እናም ይኽ ፀሐፊ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚባለው ጩኸት በመንኪ ፖክሥ ጩኸት እንዲቀየር ይኽ ፀሐፊ አበክሮ ይጠይቃል ። ጫማና ኩፍያ የሆነ አደናጋሪ ገለፃ ነውና ! ከእውነት የራቀ ትርጉም ይሆናልና !
ይኽ መንኪ ፖክሥ ፣ በተጨማሪ ፣ ዛሬ እና አሁን አሜሪካ፣ ሲውዲን እሥፔን ፣ ፖርቹጋል እና ኢጣሊያ መከሰቱ ታውቋል ። ዛሬ ደግሞ በአፍሪካ ። በድንገት የወረርሽኙ ተጠቂዎች በመከሰቱ ፣ አገራቱ ህመምተኞቹን በየሆሥፒታሎቻቸው አግለው እያከሟቸው ነው ። በሌሎች የአውሮፓ አገሮችም ወረርሽኙ እንደገባ ይወራል ። በአፍሪካችን ግን የቤት ውሥጥ “ ቀሣ “ አሥፈላጋ ነው ። እንደ በለፀጉት አገራት ኢኮኖሚያችን አይፈቅድምና !
የህነው ሆኖ ፤ የወረርሽኙ ዛሬ በአውሮፖና በአሜሪካ መግባት በእግዳነት የሚታይና የሚያሥደነግጥም አይደለም ። ከላይ እንደገለፅኩት ይኽ የዝንጀሮ ኩፍኝ ( Monkey pox ) በማለት ሥም የተሠጠው ወረርሽኝ በ2003 በአሜሪካ ተከስቶ እንደንደነበር ይታወቃል ። በወቅቱ ከ70 የማይበልጡ ሰዎችንም ይኽ መንኪ ፖክስ ይዞ ነበር ።
እናም ፣ ይኽ በቫይረሥ የሚመጣ ኩፍኝ መሠል በሽታ ፣ በቀላሉ በፀረ ቫይረሥ መድሃኒቶች መታከም የሚችል መሆኑ ጥንትም ይታወቃል ። ( ጥንቃቄ አድርጉ እንጂ ፈንጣጣ በማለት አሥፈራሪ ትርጉም በመሥጠት ማካበዱ አለአሥፈላጊ ነው ። )
በቅጡ ለመገንዘብም የዩቲዩቡን ዜና እና የነቢቢሲን ዘገባ መርምሩ ። ይኽ በቫይረስ የሚመጣ በመላ ሠውነት የሚያሥጠለ የትልልቅ ቡገር አይነት እባጭ የሚፈጥር እና በ21 ቀን የሚሰናበት ነው ።በቃ ። በዋነኝነት የሚተላለፈው በአይጥ ፣ በአይጠ መጎጥ ና በፍልፈልና በመሣሠሉት እንጂ በዝንጀሮ አይደለም ። ዝንጀሮ ዋንኛ አሥተላላፊ አይደለም ። ሆኖም የዝንጀሮ ዘመድ አዝማድ ሁሉ በበሽታው ይያዛል ። ያኔም እርሱ ነበር በ1958 ዓ/ም ጥናት የተካሄደበት ።
” በተያዘ ሰው ላይ ጥናት አልተካሄደምን ? ” በማለት ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው ። እንካችሁ መልሱን ።
በመንኪ ፖክሥ የተያዘ ሰው ከ 5 እሥከ 21 ቀናት በበሽታው መያዙ ሊረጋገጥ ይችላል ። ወይም የበሽታዎቹ ሥሜቶች በነዚህ ቀናት ይታዩበታል ። በበሽታው መያዙ ከታወቀ በኋላ ከበሽታው ለመዳን እሥከ አራት ሣምንት ሊፈጅበት ይችላል ።
በመንኪ ፖክስ የተያዘ ሰው ይኽንን ቫይረሥ በሚያሥነጥስ እና በሚያሥል ጊዜ ሊያሥተላልፍ ይችላል ። ከህመምተኛው የተቀቀለ ማሽላ ከመሠሉ ፣ ችምችም ካሉ እባጮቸ ጋር መነካካትም በሽታውን ያሥተላልፋል ። በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜም በሽታው ወደጤነኛ ሰው ይተላለፋል ።
ይኽ እንግሊዝና እሥፔንን ጭምር ያዳረሰው እና ወ አፍሪካ ጎራ ያለው ፣ መንኪ ፖክስ ” አይነተኛው ቫይረስ ” ምንጩ ፣ በመካከለኛውና በምዕራብ አፍሪካ ነው ። ቢባልም ፣ በእንግሊዝ በወረርሽኙ ከተያዙት 8ቱ ወደ ካናዳ እንጂ ወደ አፍሪካ ተጉዘው የማያውቁ መሆናቸው ታውቋል ።
እናም ወደፊት ሣይንቲሥቶቹ ተመራምረው የዚህ ቫይረሥ ምንጭ ፣ የአውሮፖና የአሜሪካ ምሥጢራዊ ላብራቶሪ ነው ። ባይሉንም እኛ ሰው ነን እና መጠርጠራችን አይቀርም ።