” የነ ጃሥ ዋር “ታላቁ ሤራ ፤ በኃይማኖት ግጭት ፤ ተጀምሯል። – ሲና ዘ ሙሴ  

” ወደፊት እነ ጃሥ የራሳቸው ኃይለኛ ሤራ እንደሚኖራቸውም ይገመታል  ። ” በጃንዋሪ 11/2022 ዓ/ም በፃፍኩት ነፃ አስተያየት ፡፡ ከሦስት ወራት በሀኋላ ይኸው እንደተፈፀመ አምናለሁ ፡፡

የጎንደሩ ግጭቱ እንዴት ተነሳ? ( ዘገባው የበበሲ ነው ) ” የአማራ ክልል መንግሥት እንዲሁም ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ግጭቱ የተነሳው በሼኽ ከማል ለጋስ ቀብር ወቅት በመካነ መቃብሩ ስፍራ አጠገብ ካለው ቤተ ክርስቲያን ድንጋይ ተነስቷል በሚል እንደሆነ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጎንደር ነዋሪ፣ የግጭቱ መነሻ ለሼኹ ቀብር የወጡ ሰዎች ከመካነ መቃብሩ አጎራባች ካለችና አዲስ ከተሠራችው ቤተ ክርስቲያን ድንጋይ ለማንሳት በመሞከራቸው ነው ይላሉ።

ከቤተ ክርስቲያኗ ድንጋይ ሲያነሱ ለምን ታነሳላችሁ? የሚል ነው የግጭቱ መንስዔ ከዚያ በኋላም ወደ ቡድን ግጭት ተቀየረይላሉ።

ሐጂ ዑስማን በበኩላቸው “ይህ የተሳሳተ ነው። ቀብር ሲፈጽሙ ድንጋይ የሚያነሱት እዛው ቦታቸው ላይ ነው። ከቤተ ክርስቲያን ክልል ውስጥ አይደለም። በሌሎች አካላት የተሰጠው መግለጫ ተቀባይነት የሌለውና ወንጀለኞችንና አጥፊዎችን ላለመያዝና ጥፋተኞችን ወደኛ ለማድረግ የሚደረግ ሙከራ ነውብለዋል።

ለዚህ ግጭት መነሻ ሊሆን የሚችል ጉዳይ የለም ያሉት ሐጂ ዑስማን፣ “አንድ አገር፣ አንድ ሃይማኖት የሚሉ ፅንፈኛ አክራሪዎች የፈጸሙት ድርጊት ነውይላሉ።

ሌላኛው የጎንደር ነዋሪ በበኩላቸው፣ እንዲህ ዓይነት ሃይማኖታዊ ግጭት በጎንደር ተከስቶ እንደማያልቅ ተናግረው “ታላቅ አባት ሞተው በቀብር ድንጋይ ነው ግጭቱ ተነሳ የተባለው። ይህ ምክንያት አይሆንም። በመሃል የገቡ አንዳንድ ችግር ፈጣሪዎች ነበሩአሁን ግን በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሰዶም የከፋ እንዲህ ዓይነት ዘመን!

ሐጂ ዑስማን በትናንትናው ዕለት የተፈጠረው ግጭት አዲስ እንዳልሆነና ላለፉት ሰባትና ስምንት ዓመታት ሲንከባለል የመጣ ችግር እንደሆነ ያስረዳሉ።

በሆደ ሰፊነት ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ በደብዳቤ፣ በአካልም ከሚመለከታቸው የመንግሥት መዋቅሮች ጋር ሰፊ ውይይት ለማድረግ ጥረት አድርገናልየሚሉት ሐጂ ዑስማን፣ “ነገር ግን የመንግሥት አመራሮች ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው የተፈጠረ ችግር ነውይላሉ።

በአሁኑም ወቅት በሕግ አግባብ ችግሮች እንዲፈቱ፣ አጥፊዎች እንዲያዙ፣ ወንጀለኞች እንዲቀጡ፣ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ የማድረግ ሥራዎችን እየሠሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ….

እንደ መግለጫው፥ በጎንደር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎችም በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር የሚጋብዙ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎችም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ ነው ያለው ።

በአንዳንድ አካባቢዎችም የእምነት ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱ ሃገራዊ ቅርጽ እንዲኖረው ሙከራ እየተደረገ ነው ያለው ግብረ ሃይሉ፥ የፌደራል የደህንትና የጸጥታ መዋቅር በድርጊቱ በሚሳተፉት ላይ ብቻ ሳይሆን ከኋላ በመሆን በሚዘውሩት ላይ በቂ መረጃና ማስረጃ ያለው በመሆኑ ተከታታይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋ በየትኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚቀሰቅሱ፥ በተለይም ደግሞ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ሃሰተኛና የጥላቻ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን የጠቆመው መግለጫው፥ በዚህ ህግወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም በጥብቅ አሳስቧል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የገጠማት አንዱ ፈተና ጦስ መውጫ የታጣለት ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› አዙሪት ነው!

ኢትዮጵያውያን ለዓመታት የገነቡት በአብሮነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እኩይ ዓላማ ባነገቡ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሃይሎች እኩይ ሴራ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት በሚፈጥሩት የግጭት አጀንዳ አይሸረሸርም ያለው መግለጫው፥ ህብረተሰቡ ለዘመናት ባዳበራቸው መልካም እሴቶች እንደዚህ አይነት የፈተና ወቅቶችን በውይይትና በሰከነ መንፈስ በመፍታት እንደሚያስመሰክር የጋራ ግብረ ኃይሉ እምነት መሆኑንም ጠቁሟል ፡፡

ዛሬም ኢትዮጵያን ሌላ የግጭት አጀንዳ በመስጠት ለማተራመስ ሙከራ ቢደረግም በደኀንነትና በጸጥታ መዋቅሩ ከፍተኛ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፥ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ችግሩ እንዳይስፋፋ ያደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ነው ያመለከተው ። “

እኔም ብዬ ነበር

  በሤራ ፖለቲካ ፈረሥ እየጋለቡ ፣ እነዚህ  የቢሊዮን ዶላር ባለቤቶች  በታላቅ ጥንቃቄ ና ምሥጢር  ሥራ አጡን ፣ በንቃተ ህሊናው ዝቅተኝነት ተጠቅመው ለጥፋት ዓላማቸው ሊጋልቡት ና  ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ  የአገር አውዳሚነት ተግባር ሊያሠልፉት ይችላሉ ። ምናልባትም ፤በእነሱ ገፋፊነት ፣ የ1969/70 ዓ/ም ቀይ ና ነጭ ሽብርን በሌላ መልኩ ሲደገም እናይ ይሆናል ። ይኽ ከሆነ ደግሞ  ። ” ኢትዮጵያ  ወይም ሞት  ! ”  የምንል ይኽ አገር አጥፊ ድርጊት ሲከሰት እንደ ቀደመው ጊዜ ፣ እጃችንን አጣምረን አንቀመጥም ።

ጉዳዪ የሞት የሽረት ትግል በመሆኑ በተጋድሎ ለመሰዋት ዝግጁ እንሆናልን እንጂ፣   እንደ ቀድሞው የገዛ እጃችንን  አሥረን በማጅራታችን ለመታረድ አናቀላፋም ።

በፍርድ ቤት ደረጃ  ፣ በችሎት ተከራክረው ፣  በወንጀል የተጠረጠሩት “ እነ ጃ – ሥ  “ (  ጃዋርና ሥብሐት )   ከተመሠረታቸው ክስ ነፃ ናቸው ። ” ተብለው ቢፈቱ ኖሮ እንዲህ አይነት ሃሰብ ዜጎች አይኖራቸውም ነበር ። የፍርድ ቤት ውሳኔ በመሆኑ እና በግልፅ ጥፋተኛ አይደለንም ብለው የሚከራከሩበትን ጭብጥ በይፋ ስለሚታወቅ ። የሁን እንጂ ፣ የፍርድ ሂደቱን ፣ ብልፅግናን ለመሪነት ያበቃው ህዝብ በአንክሮ እየተከታተለ ሣለ ና  የጀግኖች ልጆቻችን ደም ሣይደርቅ ፣   በቀጥታ ከጦርነት አውድማ ላይ የተማረኩትን ነፍሰ ገዳዮች ክስ ና በአማራ ደም የተጨማለቀ እጅ ያላቸውን የሰው ጭራቆች ክሥ  ማቋረጥ ፣  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንድ ና ሴትን የወለዱ  እናቶችን ልብ ሰብሯል ። ዛሬም ሰው መሆንን በካዱ   የእንስሳ ጭንቅላት ባላቸው ፣ ደንቆረዎች አያሌ ንፁሐን ዜጎች እንደ በረሮ እየተቆጠሩ እየሞቱ ነው    ። ጠ/ሚ አብይ አህመድ  የሰጡት ምላሽም የጲላጦስን ያህል አያረካም ።

በነገራችን   ላይ ጲላጦስ  ኢየሱስ ክርስቶስን ለመልቀቅ ይፈልግ ነበር ። ህዝቡ ግን “ ሥቀሎ ! ሥቀሎ ! ይሳቀል ! ይሰቀል ! “  ብሎ በመጮሁና ወንበዴውን ፣ ጨካኙን ባርባን እንዲፈታ በመጠየቁ  ባርባንን ፈቶ ኢየሱስን ለእነሱ ለማሥረከብ ወሰነ ። ሆኖም እኔ ከደሙ ንፁነኝ ። ለማለት እጁን በአደባባይ ታጠበ። እናም እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው ። ይኽ እውነት የሚያሥተምረን መሪ ምንጊዜም የህዝብን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ዝግጁ ካልሆነ ፣ ህዝብ ቢሳሳት እንኳን ከጎኑ ከልቆመ አወዳደቁ የከፋ እንደሚሆን ነው ።  ህዝብ ከጫፍ እሥከጫፍ ግልብጥ ብሎ ከሥልጣን ውረድ ቢልህ ምን ታደርጋለህ ?  ከሥልጣን ከመውረድ በሥተቀር ። ይልቁኑስ ማረኝ ፣ በድዬሃለሁ ። እምነትህን በልቻለሁ ። ብሎ በአደባባይ ይቅርታ መለመን ያዋጣል ። እንደ እውነቱ ከሆነ ፣ ጠለ/ሚ ክስ ማቋረጥ ብቻ ሳይሆን በፍፁም ምህረት ከእሥር ቤት መፍታት ያለበት ፣ ለሰዎች ሰብአዊ መብተ ና ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ተሞጋቹን  ጋዜጠኛ እሥክንድር ነጋን ብቻ ነበር ። ከእርሱ ጋር በርባኖችን ደባልቆ መፍታቱ ጠ/ሚ አብይን ጲላጦስ አያሰኘውም ።  …( ህዝብ ይፈቱ ብሎ አልጠየቀማ ! )

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፖለቲካ ማንነት በዛሬዋ ኢትዮጵያ - አንዱዓለም ተፈራ

ከዚህ አንፃር ክስ የተቋረጠላቸው የተፈቱበት ግልፅና አሳማኝ አይደለም ። ይላል ህዝብ ። ጠ/ሚሩም የሰጡት ምላሽ   እጅግ የተምታታ ነው ። ወንጀለኛ በዕድሜው ና በጤና ችግር  የተነሳ ይፈታ ከተባለ በሺ የሚቆጠሩ እሥረኞች ከኦቦይ ጋር መፈታት ነበረባቸው ። …

ደሞም አንዳንድ የምናከብራቸው ምሁራን እንደሚሉት ፣ ይኽ የንግድ ወይም የፖለቲካ ቢዝነስ ጉዳይ አይደለም ። “ እናተርፋለን ። እንከሥራለን ።  “ የሚባል ጉዳይ እዚህ ላይ አይሰራም ። ወዳጄ በህይወት ጉዳይ ውሥጥ ቃላት ሥንጠቃ ና አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁም ቦታ የላቸውም ። ጉዳዩ እኮ  ፣ ህይወታቸውን ገብረው የአፋርና የአማራን ህዝብ ነፃ ያወጡ  ፣ የመከላከያ ሠራዊት  አባላት ጉዳይ ነው ። የጥቃቱ ሰለባዎች  የአፋርና የአማራ ልዩ ኃይል ጉዳይ ነው ። የአማራ ፋኖ ና የአፋር ወጣት አርበኞች  ጉዳይ ነው ።ይኽ ጉዳይ  የኢትዮጵያ ፍቅር የሚያንገበግባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የእሸቴ ሞገሶች ጉዳይ ነው ። ይኽ ጉዳይ የጥቂት ተሸላሚ ጀግኖች ጉዳይ ብቻም አይደለም ። ጉዳዩ ልጥቂት ከሞት የተረፉ ጓዶቻቸው የጦር ሜዳ ጀብዷቸውን የሚመሠክሩላቸው  በይፋ ያልተሸለሙ ፤ በይፋ ሥማቸው ያልተጠራ ፤ የአያሌ የጦር አመራሮች ፣ የአያሌ መሠረታዊ ወታደሮች ደም ና አጥንት ጉዳይ ነው ። ይኽንን መሠዋትነት ያቃለለ መሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም ።   ማንም ከኢትዮጵያ በላይ አይደለምና !!!!!!!!!!    )

በነገራችን ላይ ኦቦይ በግል   አብይን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው  ። ዶክተሩም ፣ ይቅር ለእግዜር  ሊሏቸው ይችላሉ ። ዶ/ር አብይ በኦቦይ ሥብሐት በግልፅ ተሰድበዋል ። የጨዋነታችን ሥነ ምግባር ሥለማይፈቅድልኝ የኦቦይን  ሥድብ አልደግመውም ።  በዚህ ሣቢያ ግን ዶ/ር አብይ   በኢትዮጵያ ጠ/ ሚኒሥተርነታቸው   ፣ የአውሬ ና የጭራቅ  ድርጅትን ደግፈው ፣ ዘግናኝ ድርጊት በመከላከያ ላይ  ” ሀ ”  ተብሎ የፈፀም ዘንድ አባሪ ና ተባባሪ ሆነው መቀሌ ከተማ ሰዘባነኑ  እና ውሥኪ ሲራጩ  የነበሩትን ፣ ሰውነትና የሰው ክብር ምን እንደሆነ የማይገነዘቡ  ደናቁርታት ክስ እንዲቋረጥ  ማድረግ ግን አይችሉም ።

አይ ! ነገሩ ወዲህ ነው ። አሜሪካ  በምላሹ ፣ ኢትዮጵያን ወደ  አገዋ   ( AGWA ) መልሳ በማሥገባት  እንደ መንግሥት ከተደቀነባት ዘርፈ ብዙ ችግር አንዱ ና ዋንኛውን እቀርፍላቸዋለሁ ፣ ብላ ቃል በመግባቷ ነው ። ” ከተባለም ፣ እርሱ ሱሚ ነው ። አሜሪካ የደርግ ጀነራሎችን በፎርጅድ ዶላር ሣይቀር ገዝታቸው እንደነበር አሥታውሥ !? ሲአይ ኤ  እንደ ኬጂቢ በራሱ ሰው አይንቀሳቀሥም ። እንቅሥቃሴው በራሳችን ሆዳም ምሁራኖች ፊት አውራሪነት የሚታገዝ ነው ። ይኽም ከቅኝ ገዢነት ና ተገዢነት ልምድ የተወሰደ አሠራር ነው ። ቅጥረኞችም    ዶላር ና ምቾት አምላካቸው የሆነ   ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው   ። የልጆቻቸውና የሚስቶቻቸው የእረፍት ጊዜ  ፣ አሜሪካና ዱባይ  እንዲሆን የሚሹ   ።በጥቂት ወራት ቢሊዮነር ለመሆን የሚፈልጉ  የሲአይኤ ልጆች ናቸው የአሜሪካ መንግሥትን ግብ የሚያቁት ።

የሲአይኤ ቲያትር ዛሬ ለተርተው ህዝብ ጭምር ግልፅ ሆኗል ። ይኽንን ቲያትር አሣምረው የሚያውቁት እነሥብሐት ብቻ ነበሩ ፡፡ በአሜሪካ ሚሥጢራዊ ሠራተኞች ( ተላላኪዎች ) በታላቅ ምሥጢር በመጠቀም ከእሥር እነደሚፈቱ አስቀድመው ያውቁ ነበር ።

እንደምታውቁት    ከአሸባሪ ድርጅት ጋር አሜሪካ አትደራደርም ። እነስብሃት ግን ቢሊዮን ዶላራቸው አሜሪካን ያለ ቱጃሮች እንደሆነ አትዘንጋ ! አሜሪካ የእኛን ህግ ና የፍትህ መንገድ ፈፅሞ አትቀበልም ። አሜሪካ ሁሌም የምታየው ጥቅሟን ሥለሆነ ሆዳም ና ደንቆሮ በለሥልጣናትን ( ከጥበብ የራቁ ለማለት ነው ።) በገንዘብ ና በጥቅማ ጥቅም በመግዛት ፣ የብዝበዛ መንገድ ለማግኘት ብርቱ ጥረት ታደርጋለች ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ። የሚለውን ጥቅሥ እዚህ ላይ አምጣው ። ከመጣኸው ዘንድ የነሥብሐትም እሥር ከጅምሩ ድራማዊ ነበር ። ሾ ! ነበር ። እንዴት ብትል ፣  ለሽብር ተሠልፈው ፣  ለጥፋት ሠራዊቱ ለትህነግ ወታደራዊ ክንፍ ፣  የሞራል ሥንቅ በመሆን ፣ በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ  ከፍተኛ ጥፋት ካደረሱ በኋላ ፣ ለዘላለም ለመኖር አቅደው እኮ ነው ፤  ከገቡበት ዋሻ ለመውጣት የፈለጉት  ። ከቢሊዮን ያላነሰ ብር እያለኝ እዚህ ዋሻ ውሥጥ በችግር ና በችጋር ለምን እሞታለሁ ብለው ፤  የነገ መውጫቸውን በማሥላት እኮ ነው ፣ እጃቸውን የሰጡት ።  በብር ወደ ጥልቁ ታዝለው ገቡ በዘዴ ከጥልቁ ብእንኮኮ ወጥተው በቂሊንጦ ሆቴል በታላቅ እንክብካቤ ኗረው ፣ ዛሬ፣ ወደ  ተንደላቀቀ ቪላቸው በክብር ተሸጋገሩ  ። …

በሚገረም  መልኩ ፣ ከምቾትና ከመድሃኒት አቅርቦት አንፃር ፣  ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ ፣ ራሳቸው ያሉበትን ቦታ እንዲጠቆም በመፍቀድ መልክተኛ ልከው   ፣ በታላቅ ጥንቃቄ በመከላከያ ሠራዊታችን  ፣ ” ከጥልቁ ምሽግ ”  ታዝለው   በመውጣት  ፣ ለፖለቲካ  ትርፍ ሲባል ፣ ድራማዊ   በሆነ መልኩ ፣   እጃቸው በሰንሰለት ታሥሮ ካየን በኋላ ፣ ወዲያው ደግሞ  ቁጭ ብለው እየሳቁ ቁርጥ ሥጋ ሲበሉ በኢቲቪ  ያየነው እውነታ እዚህ ላይ አክለህ ፣ እውነቱን ተረዳ ።  ተረዳህ ? ግባልኝ  !!

እናም የኢትዮጵያ መሪዎች  እራሳችሁ ተሞኝታችሁ እኛን አታሞኙ ።  የአሜሪካ መንግሥት የሚፈልገው ፣ በእፍኝ  ሰጥቶ በቁና መቀበልን ነው ። እናም በሰፊው ለመበዝበዝ ፍቃደኛ ሁኑ ። ቻይናንን ፊት ንሱ  ። የአሜሪካ ካምፓኒዎችን በከርሰ ምድርህ ሀብታችን ላይ አሰማሩ ። ለ1% ቱጃሮች ቢዝነሥ ዋሥትና ሥጡ ። በመንግሥት  ሁሉም ፖሊስ ላይ ፣ ፈላጭ ቆራጮቹ እነሱ እንዲሆኑ አድርጉ ። ይኽንን ካደረጋችሁ ዓለም በጎናችሁ ታልፋለች ።  ( ጥቂቶቻችሁ አሜሪካና አውሮፓ ለዘር ማንዘራችሁ የሚሆን የግል ትውልዳችሁ ሳይለፋ ፣ ሳይጥር ና ሳይግር ተደላቆ የሚኖርበት ቢሊዮን ዶላር ይኖራችኋል ።) ሲአይ ኤ ለራሱ ከምፓኒዎች ጥቅም ሲል  መከላከያን  ያዘምናል ። በአፍሪካ  ከግብፅ ቀጥሎ ፈርጣማ ጡንቻ ያለን ተከባሪ ና ተፈሪ   ጦር እንድንገነባ ያግዛል  ። ከኤርትራ ጋርም በኮንፊደሬሽን ማዋሃድ ለእርሱ ቀላል ነው  ። ሁሉን በነሱ ቁጥጥር ካደረግህ ፣ ሁሉን እንደሚሰጡህ  ዕወቅ ። እነሱ ናቸውና  የባህር በር ያሳጡህ ፤ መልሰው ራሳቸው የሚቆጣጠሩት የባህር በር  ያሰጡሃል  ። በአፍሪካ ውሥጥ የትኛውም የባህር በር የእንግሊዝ ፣ የፈረንሳይ የአሜሪካ ና የጀርመን ጥቅም ማግኛ መሣሪያ ነው ። ደግሞም  በሤራ ቲዎሪ ራሻና  ቻይና ጫፍ አይደርሱም ። ….

የአሜሪካ  ሤራ ደግሞ ከሁሉም የላቀ ነው ። በቢሊዮን ዶላር  የሚታገዝ ከመሆኑም በላይ እጅግ የረቀቀ  ነው ።  ሤራው  ከላይ  ባነሳሁት ” የቢሆናል ሃሳብ ”  ብቻ የሚቋጭ አይምሰልህ ። ሌላም የቢሆን ሃሳብ አለኝ ።

አሜሪካኖቹ በሲአይኤ አማካኝነት  አንድ ሺ አማራጭ ፣ የሤራ ረቂቅ  ይዘው ነው የሚደራደሩት ። የሤራ ረቂቅ ንድፉም  ፣ በየጊዜው የሚከለሥ ነው ። እቅዱም  ራሱን የቻለ ቡድን ና አሥፈላጊ የሆነ የሎጀሥቲክ  ድጋፍ ያለው  ነው  ። ዋና መሪው ደግሞ ሲአይኤ ነው ። ( መአከላዊው   የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ) እንበልና   ፣ ከሲአይኤ  ከአንድ ሺ አንድ እቅዱ አንደኛው ዕቅድ ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድን በቅጥር ነፍሰ ገዳይ ማሥገደል ና   ፣ ሁነኛ የአሜሪካ መንግሥት ሎሌ ወይም በሪሞት ኮንትሮል የሚያንቀሳቅሱት  አሻንጉሊት  መንግሥት  በመንበሩ ማሥቀመጥ ቢሆንስ … ”

ዛሬስ አንድ የቢሆን ሃሰብ ሰጥቻችሁ እሰናበታለሁ ፡፡ ( ተመስገን ጥሩነህ ባይከፍለኝም )

ሌላው የቢሆን ሐሰብን እንካችሁ ፡፡ እንጀዋር ምርጥ የሲአይ ኤ ወኪሎች እንደሆኑ ይጠረጠራል ፡፡ የአሜሪካ መንግስት መሪዎች ፤ ኢትዮጵያን አሜሪካንነ  ለሚመሯት በጣት ለሚቆጠሩ ቱጃሮች ብዝበዛ ለማመቻቸት ( ፍርስርሷን በማውጣት የራሳቸው አገር ቱጃሮች መፈንጫ ለማድረግ ) መንጋን የመንዳት አቅም እነ ጃሥ – ዋር  እንዳላቸው አሳምረው ያውቃሉ ፡፡ እናም ከእስር እንዲፈቱ እንዲህ በማለት አሜሪካኖቹ ወተወቱ ፡፡ ” ሥብሃት ነጋን እንደ ሽፋን አድርጋችሁ እነ ጃዋርን ፍቷቸው ፡፡ ሰው የስብሃትን የወያኔ መስራችነትን በማየት እሱ ላይ ያተኩራል እንጂ እነሱን አያይም ፡፡ በአጋጣሚውም እናንተ ለሰላም ምን ያህል እርቀት እንደምትሄዱ በተግባር በማሳየት ከአውሮፓና አሜሪካ ትልቅ ድጋፍ ታገኛላችሁ ፡፡ ይሄ የዲፕሎማሲ ድልም የሀውሃትን ግብአተ መሬት ያፋጥናል ፡፡ ” የሚል ዋና “ጃስ ዋራቸውን ” የሚስፈቱበትን መላ ቀየሱ ፡፡ እናም ተሳካላቸው ፡፡

ከዚህ የቢሆን ሃሰብ የምንገነዘበው እነ ጃስ ዋር ዛሬ ትልቁን ፤ በቀላሉ ሊበርድ የማይችለው የሃይማኖት ግጭት በረብጣው የሲአይኤ -ዶላር (  በሱዳን በኩል በኮንተሮባንድ  እነ ግብፅ እንደሚስገቡ አትጠራጠር ፡፡ ) በየከተሞቹ ላሰማሯቸው የጥፋት ኃይሎች በመርጨት በመላው ኢትዮጵያ የእሳት ቃጠሎ እዛና እዚህ በማስነሳት ( መስጊድና ቤተክርስትያናትን በማቃጠል ) ፍፁም ያለመረጋጋት እንዲሰፍን እንደሚጥሩ የአሁኑ ድርጊታቸው ያሳብቃል ፡፡ እናም ጠንካራ የደህንነት ( የመረጃ ስራ ) ጠንካራ ክትትል በመላ ኢትዮጵያ  በአስቸኳይ መዘርጋት አስፈላጊ ነው ፡፡

ይህ የደህንነት ልዩ ኦፕሬሽንም በጎሰኝነት ፤ በኃይማኖት ካባ በሁለቱም ታላላቅ እምነቶች የተሸፈኑትን የጃስ ዋር ወኪሎች መንጥሮ ማውጣት ይጠበቅበታል ፡፡

ይህ መንግስት ላይ የተቀናጀ ሤራ እየተደረገበት ነው ፡፡ ቀኙን ሲመቱት ግራዬን ድገሙኝ በማለት ( ያውም ዘረኞች እብድ እብድ በሚጫወቱበታ አገር ) እያሳየ ያለው የዋህነት የትም አያደርሰውም ፡፡ ዛሬ ሤይጣን አለምን እያተረማመሳት ነው ፡፡ ሤይጣን ጉንጬን ሲመታኝ በፈጣሬ ሰይፍ በጥፊ የመታበትን እጅ መቁረጥ ኃይማኖታዊ ግዴታዬ ነው ፡፡ የአገሬ ሰው ሲተርት ለባለጌ ፊት አይሰጡም ፡፡ የፍትህን ልምጭ አይምሬነት ያስይዋል እንጂ !

 

2 Comments

  1. ኡስታዝ አቡበከር፤ጁዋር መሃመድ፤አህመዲን ጀበልና ተከታዮቻቸው እያሉ ኢትዮጵያ ሰላም ታገኛለች ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ነው

  2. ጃ ሥ በጣም የምትስማማ ቃል ነች። ቢቢሲን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ካሁን ቡሗላ የዜና ምንጭ አድርጎ ባይወስድ መልካም ነው። አብይ አህመድን በተመለከተ በእሱ ትእዛዝ ወደ መቀሌ የተላኩትን የራሱን ወታደሮች ያረደን አካል መፍታት ማለት ካሁን በሗላ ለአብይ አህመድ የሚታዘዝ ወታደር የለም ማለት ነው ይህ ማለት አብይ ወታደር የሌለው መሪ ነው። የፈለገውን ያህል ለትግሬ ስስ ልብ ቢኖረው ትግሬ ለእሱ ያለውን ጥላቻ ለኢንች አይቀንሰውምና የባሰ ጊዜ አታምጣ ማለት ያስፈልጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share